EvaSUE

EvaSUE

Share

EvaSUE is a fellowship of Students and Graduates who are dedicated to follow and witness Jesus Christ as Lord and Savior.

23/05/2026

በራልን

እግዜሩ ጋር ንክኪ ያለው ሰው አቤት መታደሉ። ከክንፉ ጥላ ስር ተሸሽጎ በጥበቃው ልቡ አርፎ ይኖራል። ከመረጃ ባለፈ በተጨባጭ ሁኔታ በሒወቱ እውን ለሆነለት አምላክ ፈቃዱን አስገዝቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ራሱን ካልገለጠልን በስተቀር በራሳችን ጥረት ልንደርስበት አንችልም ፤ በሰው ቀመር እና ስሌት አይገኝም ፤ በሰው የአዕምሮ ልህቀት ታስሶ አይደረስበትም። ታዲያ ይህ ረቂቅ እና ምጡቅ አምላክ ራሱን ለሰው ልጆች መግለጥ በጎ ፈቃዱ ሆኖ በልጁ በክርስቶስ በኩል መልኩን፣ ባህሪውን እና ማንነቱን አሳየን። እግዚአብሔር ተገለጠልን በራልን። እርሱን ማወቅ የዘላለም ህይወት ነው። ከእርሱ ጋር ተጣብቆ መኖር የህይወት ትርጉም ነው። ከእርሱ ጋር መወዳጀት የእረፍት አለም ነው። እርሱን ማመን ልብን የሚያረጋ መልህቅ ነው። ታዲያ እግዜሩን ከመረጃ ባለፈ በህይወታችን እውን ይሆንልን ዘንድ ይበራልን ዘንድ የግድ ያስፈልጋል። እንዲበራልን ይበልጡን እንድናውቀው እና እንድንረዳው ደግሞ ወደእርሱ ቀርበን ልንለምነው በፀሎት እንማፀነው ዘንድ ይገባል፤ እንዲሁ በአዕምሮ የምናውቃቸውን የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች መተግበር ይገባናል ። ከትላንቱ ዛሬ ፤ ከዛሬ ደግሞ ነገ እግዚአብሔርን በማወቅ ህይወት እንዲሁም በእውነተኛ መረዳት እና ግንዛቤ እያወቅነው እንኖር ዘንድ ፀጋ ይብዛልን

✍ ካሌብ ካሳሁን

EvaSUE 01/05/2026

ዘፍጥረት || መግቢያ || ዘለለው አርጋው

EvaSUE 1 like. "ዘፍጥረት || መግቢያ || ዘለለው አርጋው"

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Queen Elizabeth II
Addis Ababa
34354