Hagere Community Development Association

Hagere Community Development Association

Share

Hagere Community Development Association (HCDA) is an indigenous non-governmental, non-profit, secular, legally registered association.

Photos 28/02/2016

በአሁኑ ወቅት የአፋር ክልል ሁኔታ
ክልሉ በ5 ዞኖች፣ በ32 ወረዳና፣ 407 ቀበሌዎች የተዋቀረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በደረሰው ድርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እየደረሰባቸው ካሉ ክልሎች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡
የዓለም ምግብ ድርጅት ባወጣው መረጃ አንድ ሶስተኛው የአፋር ህዝብ በረሀብ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ እንደ ምግብና የገቢ ምንጭነት የሚጠቀሙባቸው ከብቶቻቸውም በዚሁ ምክንያት እያለቁ ይገኛሉ፡፡
-------------- --------------- ----------------
የአፋር ክልል ህዝብ አብዛኛው አርብቶ አደርና ዘላን የሆነ ህዝብ ነው፡፡ የክልሉ ማህበረሰብም በዋናነት ምግብም ሆነ የገቢ ምንጭ የሚያደርገው የሚያረባቸውን ከብቶች ሲሆን ከቦታ ቦታ በሚዘዋወር ጊዜም እነዚሁኑ ከብቶች በመያዝ ይንቀሳቀሳል፡፡ የክልሉ የአየር ሁኔታ በአብዘሀኛው በረሀማ ከመሆኑም የተነሳ ለእርሻ ስራነት የሚያውለው መሬት ጥቂትና ብዙ ልፋት የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት በአየር መዛባት ምክንያት በሚደርሱ ድርቆች የመመታት እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህ ተጋላጭነቱም ህዝቡ እንዳያገግም አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩልም ክልሉ እጅግ ኋላ ቀር ከመሆኑም የተነሳ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተጋረጠ ነው፡፡
------------ ------------- ----------------------
ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ይህ ድርቅ የተከሰተው፡፡ ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በቦታው በመዘዋወር ያለውን ሁኔታ ለመመልከት ችሏል፡፡ በስፍራው በተደረጉ ምልከታዎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል በተገኙባቸው ክፍሎች መምህራቸውን ከመከታተል ይልቅ ረሀባቸውን እያሰቡ በተጎሳቆሉ ፊቶቻቸው ደርቀው በጉንጮቻቸው የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎችና መላ አካላቸውን ለተመለከተ የሚፈጥረው ስሜት ከባድ ነው፡፡
እናት ልጆቿን ለማባበል በሚል ከለቅሷቸው እንዲታቀቡ ለማድረግ በተጣጠፈ አንጀቷ ስትጥር መመልከት አንጀት ያላውሳል፡፡ አዛውንት በዚያ የጸሀይ ሀሩር ግለት መናገር አቅቷቸው ሀሳባቸውን በእንባቸው ሲገልጹ በቦታው ተገኝቶ ላየ ከአካባቢው ጥፋ፣ ሩጥ፣ ሂድ፣ ጩኽ ያሰኛል፡፡ እዚህም እዚያም የረሀብ ዋይታ ከሚያሰሙ ህጻናት ባልተናነሰ የህይወታቸውን የመጨረሻ እስትንፋስ የሚያጣጥሩ እንስሳትን ድምጽ መስማት ያሳቅቃል፡፡ በየመንደሩ ተዘርረው የሞቱ ሳይሆን ሆን ብለው የተሰደሩ የሚመስሉ አያሌ እንስሳት አስከሬንን መመልከት ብቻ ሳይሆን በዚያ የሚያልፍ የመኪና ተጓዥ እንኳ መስኮቱን የሚያዘጋው ክርፋት የአካባቢውን ችግር በስፋት ያመለከታል፡፡ በቦታው ለተገኘ ከዚህም የከፋ ሁኔታ መኖሩን ሊታዘብ ይችላል፡፡
-------------------- --------------------- ----------------------
የክልሉ ህዝብ በዚህ ሁኔታ እየተራበ እኛ የነዚህ ወገኖች ችግርን መረዳት ካልቻልን ማን ደራሽ ሊኖር ይችላል ብለን ተነስተናል፡፡ ዛሬ በየከተማው ካሉ ምግብ ቤቶች የሚወጡ ትርፈ ምግቦች እንኳን ምን ያክል ረሀብተኞችን መታደግ እንደሚቻል ማሰብ አያዳግትም፡፡ በየከተሞቻችን ከየትም ተብለው በመጡ የምግብ ዓይነቶች መንበሽበሻችን የጠገበ ሰው የተራበ ያለ መሆኑን ይረሳል የሚለውን ብሂል ሊያስታውስ የሚችል ነው፡፡ ከአፋችን ጫፍ ደርሳ የወደቀችዋን ሩዝ ያጡ ወገኖቻችን እንደ ቅጠል ሊረግፉ ጫፍ ደርሰዋል፡፡ ለእጃችን መታጠቢያነት በሳሙና ብዛት የምናባክነውን ውሃ ለጉሮሯቸው ናፍቀዋል፡፡ ተርበዋል፣ ተጠምተዋል፣ ታርዘዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በአፋር ያለው እውነታ፡፡ እናም ለወገን ወገኑ ካልደረሰለት ማን ይደርሳል!!
እናም ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን ይህንን ከግምት በማስገባት ለወገን ደራሹ ወገን ነውና የእርዳታ ድጋፍ ጥሪ ከማድረግም አልፎ በማስተባበር ላይ ይገኛል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
325