ZimareTube
በየዕለቱ የተመረጡ የንስሐና የዓውደ አመት መዝሙሮች ፣ ዕለቱንና ወቅቱን በተመለከተ ስብከተ ወንጌልና
ትምህርተ ኃይማኖትን፣ ያባቶቻችን ገድልና መንፈሳዊ
18/06/2026
ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!
መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ
በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።
ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።
መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
17/06/2026
ሊቀ መልእክት ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏
የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ሲሆን የ7 ሊቃነ መላዕክት አለቃቸው ነው ቅዱ ሚካኤል። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለት በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡
አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአይሁድ ስራ አዝኖ በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ትዕግስት ተገርሞ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሰቀሉት እያለ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ። ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን አሸንፎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባበት ዕለት ነው። መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል።
“በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ገዳማውያን የሚያደርጉት ጸሎትና የሚያቀርቡት መስዋዕት በእርሱ ምልጃ ያርጋልና ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the place of worship
Website
Address
Addis Ababa