Dire Tub.com

Dire Tub.com

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Tub.com, Media/News Company, Addis Ababa.

29/08/2022

የደሴ እና የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 23፣ 2014 ዓም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል።
1. ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
2. ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
ደሴ ሸዋሮቢት ከተማ ኮሙኔኬሽን
ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

Photos 15/07/2015

~ኤፍ.ቢ.ሲ ሀምሌ 8/2007
በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን
ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው
ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ
በእስራት ተቀጡ።
በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ
የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት
ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ
ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው
በማዋላቸው ነው።
የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር
በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ
ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር
ያልተፈቀደላቸውን 24 ሺህ ብር ከወጋገን
ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ አውጥተዋል።
ተከሳሾቹ ለአቶ ዮናታን ባልቻ መኪና
በማከራየት የኪራይ ስምምነት ውል ያላቸው
ሲሆን፥ በውላቸው መሰረትም ሚያዚያ 8 ቀን
2005 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ የ4
ሺህ ብር ቼክ ተቀብለዋል።
ግለሰቦቹ ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም
ላይም ከመኪና ተከራዩ አቶ ዮናታን
በተቀበሉት የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት
ለፊቱ 2 ቁጥርን በመጨመር ተጨማሪ 20
ሺህ ብር ከባንክ ቤቱ አውጥተዋል።
በዚህም መሰረት የፌደራሉ አቃቤ ህግ
ተከሳሾቹ የማይገባቸውን ብልጽግና
ለማግኘት በማሰብ በፈፀሙት ወንጀል ክስ
በመመስረት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን
አቅርቧል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል
ችሎትም ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን
ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ
ብሏቸዋል ።
ተከሳሾቹ ወንጀሉን በስምምነት በማበር
የፈፀሙት በመሆኑ ቅጣቱ ከፍ ብሎ
እንዲወሰን አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ
አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ
በኋላ ተከሳሾቹ ያላቸውን የቅጣት ማቅለያ
እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቤዛዊት መስፍን
የዕድሜዋን ወጣትነት፣ ከዚህ ቀደም
በምንም አይነት የወንጀል ድርጊት
አለመሳተፏንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ
መሆኗን በቅጣት ማቅለያነት አቅርባለች።
2ኛ ተከሳሽ አቶ ነቢል ይማም ምንም አይነት
የቅጣት ማቅለያዎችን አላቀረበም።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል
ችሎትም 1ኛ ተከሳሽን በ6 ወር ቀላል
እስራትና በ1 ሺህ 500 ብር እንዲሁም 2ኛ
ተከሳሽን በ1 አመት ከ6 ወር እና በ3 ሺህ
ብር እንዲቀጡ ወስኗል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
242