Computer trick and hacking ethiopia

Computer trick and hacking ethiopia

Share

get latest technology information

18/11/2022

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ማለፉን አስታወቀ።

⚡️ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከወር በፊት በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ማለፉን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። ኩባንያው ባለፉት ሁለት ስምንታት ብቻ 200 ሺህ ደንበኞችን እንዳፈራ የኩባንያው መረጃ ያመለክታል።

⚡️የኩባንያው ተፎካካሪ ኢትዮ ቴሌኮም አለኝ የሚለው የደንበኛ ብዛት 58 ሚሊዮን ነው። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ካለፈው ጥር ወዲህ አዲስ በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት ላይ 300 ሚሊዮን ዶላር ማፍሰሱን እና በጠቅላላው 650 ሠራተኞችን ቀጥሬያለሁ ብሏል።

ለቀለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ🧩🧩 https://t.me/techzoneethio

18/11/2022

የቲውተሩ ባለቤት ኤለን መስክ ሠራተኞቹን አስጠነቀቀ።

⚡️በቅርቡ ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ሠራተኞቹ “ ለረዥም ሰዓት በከፍተኛ ጥንካሬ” ለመሥራት ቁርጠኝነት ከሌላቸው ኩባንያውን እንዲለቁ መናገሩን ሪፖርቶች ይፋ አድርገዋል።

⚡️አዲሱ የማኅበራዊ ድርጅት ባለቤት ለሠራተኞች በላከው ኢሜል ሠራተኞቹ በኩባንያው መቀጠል ከፈለጉ በዚህ ዓይነት አሠራር ለመቀጠል ቃል መግባት እንዳለባቸው ማሳሰቡን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። በኩባንያው አሠራር የማይስማሙ የሦስት ወር የሥራ ስንብት ክፍያ እንደሚሰጣቸው መስክ ተናግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/techzoneethio

06/09/2021

የቻይናው AG600 የተሰኘ አዲስ አውሮፕላን ከመሬት ወደ ውሃ አካላት ማረፍ የሚችልና ከውሃ አካላት መነሳት የሚችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ አውሮፕላኑ በመነሻነት በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ሁኔታዎች ውስጥ በረራዎችን ለማድረግ ታልሞ የተሰራ ሲሆን በቻይና 13ኛው አለማቀፍ የአቪየሽን ኢግዚቪሽን ላይ ከምድር ወደ ውሃ እንዴት ማረፍ እንደሚችል የሚያሳይ ይሆናል፡፡
አውሮፕላኑን ያበለጸገው የቻይይና አቪየሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እንዳወጣው መረጃ አውሮፕላኑ ያለውን እሳት አደጋን የመቆጣጠር ብቃት በበረራው ወቅት ያሳያል ተብሏል፡፡ ለአውሮፕላኑ የተሰጠው የኮድ ስምም በቻይና የአደጋ መከላከል ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ጥቅም ያለውን ቁስ ምክንያት ያደረገ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በዚህም አውሮፕላኑ በእሳት አደጋ፣ የባህር ላይ አደጋ እና ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋ ሲያጋጥም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስችላል፡፡
የመጀመሪያ በረራውን በ2017 በስኬት ያጠናቀቀው አውሮፕላኑ ለግድብ ከተከማቸ ውሃ (a water reservoir) በ2018 አኮብኩቦ መነሳት የቻለ ሲሆን በ2020 ደግሞ መነሻውን ከውቅያኖስ ላይ አድርጎ በረራውን አካሂዷል፡፡ የዚህ አመት የቻይና የበረራ ኤግዚቢሽን ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ በደቡባዊ የቻይና ክፍል ጓንግዶንግ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

ምንጭ Xinhua net

23/12/2020

❓ለመጀመርያ ግዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው❓
የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ውስጥ የሚገኘው "Google" ኩባንያን ለየት የሚያደርገው የቢሮው ሁኔታ እና የሰራተኞቹ የአሰራር መንገድ ነው።

ተቀጣሪዎች "....በዚህ ሰዓት ውጣ፣ በዚህ ሰዓት ግባ ፣ ከዚህ እስከ እዚህ ሰዓት ስራ፣ ፊርማ ፈርም፣ እዚህ ተቀመጥ ፣ ይሄንን አትጠይቅ፣ ይሄንን አትንካ፣ ይሄንን ብቻ ስራ!...." ምናምን መባል የለባቸውም! እንደዚህ አይነት ኃላ ቀር አሰራሮች ለብዙ አመታት ውጤት አላመጡም!፣ ፈጠራን አላበረታቱም!፣ ሰራተኛውንም አሰሪውንም አልጠቀሙም!" ብሎ የሚያምነው የ "Google" ኩባንያ የራሴ አሰራር፣ የራሴ የስራ ፍልስፍና አለኝ ይላል! በዚህም ፍልስፍና እጅግ ውጤታማ ሆኗል!

የመጀመርያው ድርጅቱን ከስራ ቦታ ይልቅ ሁሉም ነገር የተሟላለት መኖርያ ቤት የሚመስልበትን መንገድ ፈጠሩ። የተለመደውን የቢሮ ቅርፅ አስወገዱ! ድርጅቱ ውስጥ የአለቃ እና የሰራተኛ ወንበር የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ቢሮ ክፍት ነው። ሁሉም የፈለገበት ቦታ ላይ ተቀምጦ መስራት ይችላል! የግል ንብረት፣ የግል ኮምፒውተር፣ የግል ወንበር ምናምን የለም! ማንም የምንም ነገር ባለቤት አይደለም! ሁሉም ነገር የሁሉም ንብረት ነው።

የሰራተኞቹን የፈጠራ ብቃት ለመጨመር እና አዕምሯቸው የተፍታታ እንዲሆን በማሰብ የሚዝናኑባቸው እንደ ፑል፣ ቴኒስ፣ ጆተኒ፣ ጎልፍ፣ ዲጅታል ጌም መጫወቻዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች እና የሙዚቃ መሳርያዎች በየቦታው አሉ። አንድ ሰራተኛ በፈለገበት ሰዓት መጫወት እና መዝናናት ይችላል።

ስራህን ስትሰራ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ ውሻህ ወይም ድመትህን ጭምር ይዘህ መሄድ ትችላለህ። ድርጅቱ ገደብ (Limitation) የሰዎችን የመፍጠር "tendency" ይቀንሳል! ብሎ ያምናል።

ውስጡ ከ 25 በላይ ትልልቅ ካፍቴርያዎች እና ሬስቶራንቶች ያሉት "Google" ሰራተኞቹ በፈለጉት አጋጣሚ ያሻቸው ምግብ እንዲቀርብላቸው ያደርጋል። አንድ ሰራተኛ ከ 200 ጫማ (60 ሜትር) በላይ ከምግብ መራቅ የለበትም በሚል ፍልስፍናም ድርጅቱ ያምናል! "የራበው አይሰራም! ሁሉም ነገር የቀረበለት ሰራተኛ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ስራ እና ስራ ብቻ ማድረግ ይችላል!" በሚል አመለካከት ያምናሉ።

ሰራተኞቹ አዓምሯቸው ከተወጣጠረ እራሳቸውን ለማፍታታት በቢሮ ውስጥ ማሳጅ የሚደረጉባቸው ክፍሎች እና የሰለጠኑ እና ፍቃድ ያላቸው የማሳጅ ቴራፒስቶች ዝግጁ ሆነው ይጠብቋቸዋል!

ለአካባቢያዊ አየር ጥበቃ ካላቸው ትኩረት የተነሳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹ ከስራ ቦታ ወደ ቤት/ከቤት ወደ ስራ ቦታ የሚመላለሱት የልቀቅ መጠናቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ባሶች ነው። እያንዳንዱ ሰራተኛ የራሱን መኪና እየነዳ ቢመላለስ በአመት ሊለቀቅ የሚችለውን ከ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ልቀት መቀነስ ተችሏል። ግቢ ውስጥ ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱት በሳይክል ነው! ይህም ልቀትን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል!

👉በቅጥር ግቢው የሚበቅለውን ሳር/አረም ለማስወገድ "Google" ማሽኖችን" ሳይሆን "ፍየሎችን" ነው የሚጠቀመው! በየግዜው ፍየሎችን እየተከራየ በግቢው ውስጥ የሚበቅለውን ሳር/አረም እንዲግጡለት ያደርጋል! አንድ ሰራተኛ እየሰራ በአጠገቡ ፍየል ሲያልፍ አይደንቀውም!😃 ሰራተኞቹ እንደውም እነዚህን ፍየሎች ማየታችን የፈጠራ አቅማችንን ጨምሮልናል ይላሉ።

"Google" ዋናው ኩባንያ አጠገብ ለምትገኘው "Mountain View" ለምትባል አነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ በነፃ ዋይ ፋይ እንዲያገኙ እና ኢንተርኔትን ያለምንም ገደብ እንዲጠቀሙ አድርጓል።

በድርጅቱ የተቀጠረ ሰራተኛ ህይወቱ ቢያልፍ ሚስት ወይም ባል የሟች 50% ደሞዝን ለ 10 ዓመታት እንዲከፈላት/እንዲከፈለው ይደረጋል።

በአጠቃላይ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ላፕቶፓቸውን ይዘው ሸርተቴ እና ዥዋዥዌ ሲጫወቱ ማየት ብርቅ አይደለም።

"Larry page" እና "Sergey Brin" በተባሉ በ "Stanford University" የ "PHD" ተማሪዎች የተመሰረተው "Google" ኩባንያ አሁን ላይ ከ 500 ቢልዮን ዶላር በላይ "worth" የሚያደርግ ሲሆን የዓለማችን "Most Visited website" ነው። የዛሬ 22 ዓመት ሲመሰረት የመጀመርያ ቢሮው የክራይ ጋራዥ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በተከራዩት ገራዥ ውስጥ 16 ሰራተኞች ብቻ ነበራቸው! አሁን ላይ በዓለም የተለያዩ 50 ሃገራት 70 ግዙፍ ቢሮዎች እና በ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉት።

የመጨረሻ!

"Google" በመጀመርያ ስፔሊንጉ "Googol" የነበረ ሲሆን መስራቾቹ የድርጅቱን "Domain" ለማስመዝገብ ሲሄዱ በተፈጠረ የስፔሊንግ ስህተት ነው "Google" ተብሎ የቀረው። በነገራችን ላይ በአማካይ በቀን "1 ቢልዮን" ነገሮች "Google" ላይ "Search" ይደረጋሉ።

⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
1000