Addisout.Com
Ethiopia Related Media. "Architecture is frozen music," Goethe. Environmental & Construction Engineering Works Contact email is Available 👇👇👇
10/05/2026
🏆🏆🏆
ባርሳ ማድሪድን 2-0 በማሸነፍ ሶስት ጨዋታ እየቀረው የላሊጋው ሻምፒዮን ሆኗል። Congrats Barca 🏆... Number 29 🏆
የባርሳው አሰልጣኝ ሃንስ ፍሊክ ዛሬ የተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ነው፣ አባቱ ዛሬ ዋንጫ ባነሳበት ቀን አርፈዋል...😢 RIP
እንኳን ደስ አላችው የባርሳ ደጋፊዎች... Next Year Champions League...
❤️Addis🌕ut Media❤️
09/05/2026
ከኢቶሪካ አልበም ብዙ ያልተወራለት ግን ወቅታዊ ሁኔታችንን የሚገልጸው "የአዞ እምባ ነው".... እስቲ ቴዲሻ በዚ ዘፈኑ ማስተላለፍ የፈለገውን ሃሳብ እንደገባን እናቀርብላችው...🙏🏿
ዘፈኑ ሲጀምር ለ22 ሰከንዶች ያህል ለቅሶና እሪታ ድምጽ ገብቶበታል...😭😭😭
ስሙኝ አቤት ይላል ወይ ሰው
'ሹም ዳኝ' ጆሮ ካላዋሰው....
አንድ ሰው በደል ደርሶበት "አቤት" ቢልም፣ ዳኛው ወይም ባለስልጣኑ (ሹሙ) ጆሮ ሰጥቶ ካልሰማው ፍትህ ሊገኝ አይችልም። እዚህ ጋር ቴዲ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን "ሰሚ ማጣት" እና የተገፋ ሰውን ብሶት እየገለጸ ነው።
በዋዛ መች ይቀራል ፈሶ
የአዞ እምባ ቢባል የኔ ለቅሶ
በተለምዶ "የአዞ እምባ" የሚባለው ለውሸት ወይም ለታይታ የሚፈስ እምባ ነው። ነገር ግን ቴዲ "የአዞ እምባ ቢባል የኔ ለቅሶ" በማለት፣ የእሱ እውነተኛ መከራ እና ለቅሶ በሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ ወይም እንደ ውሸት መታየቱን በምሬት ይገልጽና "በዋዛ መች ይቀራል ፈሶ" አንድ ቀን ፍትህ እንድሚያገኝ፣ፈጣሪ የልቡን አይቶ ጸሎቱን እንደሚሰማው በዋዛ የፈሰሰው እንባና ደም መቆሚያው ቅርብ እንደሆነ ይመኛል።
ሲል ቅሪልኝ ይህ ልቤ ከነፍሱ
ወግድ ሂድልኝ ሰው ነው ወይ መልሱ
ልቡ እና ነፍሱ እየተሰቃዩ ባለበት ወቅት፣ ከሰዎች የሚሰጠው ምላሽ መገፋትና "ሂድልኝ" የሚል መሆኑ የደረሰበትን የሞራል ውድቀት ያሳያል።
በኡታ እያሪኮ ፈርሶ
እስኪዳኝ በራማ እምባ ፈሶ
እነዚህ ስንኞች ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮችን በመጥቀስ የሕዝብን ጭቆናና ፍትሕ ፍለጋ ይተርካሉ። "በኡታ እያሪኮ ፈርሶ" የጭቁን ሕዝብ ጩኸት የኢያሪኮን ግንብ የመሰለውን የክፋት አጥር እንደሚንድ ያመለክታል። "እስኪዳኝ በራማ እምባ ፈሶ" ደግሞ የራሔል ለቅሶን በማንሳት፣ ፍትሕ እስኪሰፍን ድረስ ንጹሐን እምባቸውን እንደሚያፈሱ ያሳያል። በአጠቃላይ፣ ስንኞቹ የጩኸትና የለቅሶ ኃይል በመጨረሻ ፍትሕን እንደሚያመጣ እምነት ይገልጻሉ።
ከዘመን ጋራ ገጥሞ እጣዬ
ሳይ አሳር ይፈሳል እምባዬ
ቴዲ አፍሮ የሚኖርበት ዘመን እጅግ አስቸጋሪና መከራ አሳር የበዛበት መሆኑን ይገልጻል። "እጣዬ ከዘመኑ ጋር ገጠመ" ማለቱ፣ በግል ጥፋቱ ሳይሆን በዘመኑ ክፋት ምክንያት ለስቃይ መዳረጉን ያሳያል።
በመጨረሻም እንዲህ ይለናል...
የአዞ እምባዬ አይደል የኔ
ቢፈስ እኮ ነው ማዘኔ...
"የአዞ እምባዬ አይደል የኔ" የሚለው ቀደም ሲል ለተነሳው ጥርጣሬ መልስ ነው። ሰዎች የእሱን መከራ እንደ ማስመሰል ወይም ተቺዎቹ እንደሚሉት ለገበያ ነው የሚያዝነው፣ እሱ ግን "ይህ እውነተኛ ህመሜ ነው" እያለ ነው።
"ቢፈስ እኮ ነው ማዘኔ" የሚለው ስንኝ እምባው የሚፈሰው እንዲሁ ሳይሆን ከውስጥ ከሚሰማው ጥልቅ ሀዘን መሆኑን ያረጋግጣል።
ይህ ዘፈን በአጠቃላይ ለተገፉ፣ ለልተበደሉና ድምፅ ላጡ ዜጎች ተቆርቋሪነትን የሚያሳይ ሲሆን፣ በኢቶሪካ አልበም ውስጥ ካሉት እጅግ ጥልቅና ቁጭት አዘል ስራዎች አንዱ ነው።
እኛ እንዲ ነው የተረዳነው እናንተስ ⁉️
Via AddisAlem Sherif
❤️Addis🌕ut Media❤️
ፍትህ ለወንድማችን ኦሮሮ! — በሽሮ ሜዳ የተፈጸመው ልብ የሚሰብር ተግባር
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "ሽሮ ሜዳ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልብ የሚሰብር ተግባር ተፈጽሟል።
የቀድሞው የነጠላ ነጋዴ፣ የብዙዎች ደጋፊ እና ለጋስ የነበረው ወንድማችን ተገኝ ባልቻ (ኦሮሮ) በፖሊስ አባል አራት ጥይቶች ተተኩሰውበት ህይወቱ አልፏል።
ኦሮሮ ሽሮ ሜዳ ላይ ታታሪ ሰራተኛ እና ለጓደኞቹም ሆነ ለቤተሰቡ የሚተርፍ መልካም ሰው ነበር። ነገር ግን በልማት ምክንያት ሱቁ በመፍረሱና ንብረቱን በማጣቱ ከፍተኛ ቁጭትና ስሜት ውስጥ ወድቆ ነበር። ከወር በፊት በሞቅታ ከአንድ ፖሊስ ጋር በነበረው አለመግባባት ታስሮ አምስት ቀናት ከባድ ድብደባ ደርሶበታል። የሚገርመው፣ ኦሮሮ በእስር ላይ ሳለ አባቱ የሞቱ ሲሆን፣ ሀዘኑን የጨረሰውም በእስር ቤት ነበር።
ከእስር ተፈቶ በአባቱ ሀዘን ላይ እያለ "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" በሚል በፖትሮል ተጭኖ ወደ ሽሮ ሜዳ 02 ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ። ነገር ግን ጣቢያው በር ላይ ቀደም ብሎ ግጭት የነበረው ያው ፖሊስ ተረኛ ነበር። ፖሊሱ በግል ቂም በመነሳሳት ኦሮሮ ላይ ጣቢያው ደጃፍ ላይ አራት ጥይቶችን በመተኮስ ህይወቱን አጥፍቶ አምልጧል።
በአሁኑ ሰዓት እናቱ በሀዘን ብዛት አእምሮዋን እስከማጣት ደርሳለች። ከአባቱ ሞት በኋላ ገና ሳይቆይ፣ ልጇን የተቀማች እናት ጩኸት የአዲስ አበባ ህዝብ ሊሰማው ይገባል።
Video Source: Gaza(ሽሮሜዳ)19
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Address
Addis Abeba