HawaiTech
HawaiTech Technology Group, Is Cloud ERP Web Appication and Integration Service.
11/11/2023
በሶሻል ሚዲያ ከሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች እራስዎን ይከላከሉ
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በጓደኞቻችን ላይ የምናያቸው የሳይበር ጥቃት ምልክቶች አሉ፣ እነሱም ከጓደኛ ወይም ከስራ ባልደረባዎች በቴሌ ግራም ወይም በዋትሳብ እንዲሁም በሌሎች የሶሻል ሚዲያዎች አማካኝነት ላኪው ሳያውቅ ወደሌሎች ጓደኞች ወይም የቡድን አላስፈላጊ እንዲሁም ሌሎችንም የሚያጠቃ የማይታወቅ/የተሸፈነ/ ስውር አላማ ያለው ሊክን እየተላከ ይገኛል፣ ይህም ከጓደኛው/ዋ የተላከ ስለሆነ እምነት የሚያሳድርና ሳናገናዝብ ልንጫነውና እኛም ተጠቂ የሚያደርገን ይሆናል
ምልክት
አሁን ላይ ያለው ዋነኛው ምልክት በእንግሊሽ ቋንቋ ለሆነ ጉዳይ ይጠቅማል ይልና ሊንክ/ማስፈንጠሪያ አብሮት ይመጣል፡፡
ማድረግ የሚገባን ጥንቃቄ
ሊንኩን/ማስፈንጠሪያ/ በምንም መልኩ አለመጫን እንዲሁም የምታውቁት/ቋት ከሆነ/ች በመስመር ስልክ ወይም በሌላ መልኩ የሳይበር ጥቃት ደርሶበት እንደሆነና እርምጃ እንዲወስድ/እንድትወስድ/ መንገር፡፡
ለመከላከል
1.በቴሌግራም እና በዋትስ አፕላይ የማናውቀው/የተውነው/ የመጠቀሚያ መሳሪያ ካለ ማስወገድ፣
a.ለቴሌገራም => ትከፍቱትና በግራ በኩል ሴቲንግ የሚለው ውስጥ ዲቫይስ የሚለውን ተጭናችሁ ከምትጠቀሙበት ውጭ ያለውን አጥፋ የሚለውን መጫን
b.ለዋትስአፕ => ዋትሳብ የሚለውን ክፈቱና ሴቲንግ ውስጥ ገብታችሁ ሊንክድ ዲቫይስ ውስጥ ገብታችሁ የማትጠቀሙበትን ዲቫይስ/መጠቀሚያ መሳሪያ/ ማጥፋት
2.የማትጠቀሙባቸውን ወይም የማታውቋቸውን የቴሌገራም ቦት ወይም የዋትሳብ ቻትቦት ብሎክ ማድረግ ወይም ማቋረጥ
3.ኢንተርኔትን በኮምፕዩተር እንዲሁም ሞባይል ላይ በምትጠቀሙበት ግዜ የሚመጡላችሁን አካውንት አስገቡ የሚሏችሁን ማንኛውንም ጥያቄዎች ወይም ኃላፊነት ስጡኝ የሚሉ ጥያቄዎችን በአግባቡ ማየት እንዲሁም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ
4.የማታውቁትን ወይም አላስፈላጊ መረጃ ከሚጠይቁ መተግበሪያዎች እንዲሁም ድህረ ገፆች መራቅ፣ ወይም አለመጠቀም
5.ሳታውቁት የተላከ መልዕክት እንዳለ መመልከትና አጠራጣዊ መልዕክቶች ሲላኩልንም ከራሳችን ወገኖች ቢላኩም ማስፈንጠሪያ በሚኖረው ግዜ ማረጋገጥ ይኖርባችኋል
6.እድል ደርሷችኋል፣ በነፃ ፣ እድሉን ተጠቀሙበት የሚሉ መልዕክሮችን በአንክሮች ማየት ያስፈልጋል፣ ዋነኛ መልክቶች እነዚህ ስለሆኑ
እራሳችንን ከሳይበር ጥቃት እንከላከል
05/08/2022
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ
አካውንትዎን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤
የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤
-ቃልዎ፣ ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤
2. የሚጎበኙትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ
ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤
መረጃ የሚያፈላልጉበት ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤
ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤
ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን
/Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤
ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤
ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት (log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤
4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ
ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ ወዳጅዎ መስለው የጓደኝነት ጥያቄ ሊልኩልዎ ይችላላ ፤
ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤
5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራስዎን ይጠብቁ
ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤
ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤
በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤
6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ
ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ
በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤
ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤
ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤
7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ
አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤
ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
ጀምስ ዌብ ቴሌስኮፕ (James Webb Telescope) ለዲሴምበር 24 ለመላክ ተቀጥሯል
የአለማችንን አፈጣጠር ከቢግ ባንግ በኋላ ምን የመስላል እንዲሁም ፕላኔት እና ስታር አፈጣጠሮችን እንዲሁም የሂወትን መጀመሪያ ለማወቅ ያስችለናል ብለው የተማመኑበት ነው
ይህ ቴሌስኮፕ እጅግ ለየት ያለና 10 ቢሊየን ዶላር የወጣበትና 10 አመት የፈጀ ሲሆን በናሳ፣ ዩሮፒያን ስፔስ ኤጀንሲና ካናዳ ስፔስ ኤጀንሲ ተባብረው የሰሩት ሲሆን ከዚህ ቀደም ይላኩ የነበሩትን የቴሌስኮፕ አይነቶች የተለየና የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች የተካተቱለት ሲሆን ከዚህ ከነበሩት ሀብል ስፔስ ቴሌስኮፕ ( Hubble Space Telescope ) ተብሎ ከሚጠራው ፍፁም የተለየ ነው፡፡
ይህ ቴሌክኮፕ የተሰየመው 1961-1968 የአፖሎ 11 ፕሮግራምን የመራው በነበረው ጀምስ ኤድዊን ዌብ (James Edwin Webb) ሲሆን ፕሮጀክቱ የተጀመረው በ1996 ሲሆን በ2007 ለመልቀቅ ነበር፣ ሲጀመር 500 ሚሊየን ዶላር ብቻ ነበር የተመደበለት፣ በ2005 ዋና ማሻሻያዎች በመደረጋቸው ዘጠኝ አመት ገፍቶ በ2016 ግንባታው ተጠናቋል፡፡ የተለያዩ ፍተሻዎች ሲደረጉለት ቆይተው እንዲሁም በኮቪድ ምክንያት ዘግይቶ የፊታችን አርብ ዲሴምበር 24፣2021 12:20 በአርያና 5 ሮኬት ከ ዩሮፒያን ስፔስ ፖርት የማምጠቂያ ጣቢያ የሚላይ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዊኪፒዲያ እንዲሁም ከናሳ መረጃ ዌብሳይ ማግኘት ትችላችሁ
https://en.wikipedia.org/wiki/James_Webb_Space_Telescope
https://www.youtube.com/watch?v=7nT7JGZMbtM
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል
እንደ እውነቱ ከዚህ በፊት የምንማርበት መፅሀፍ ወይም በኢንተርኔት ላይ የምናገኛቸው መረጃዎች ሁሉም ዋሾች ስለነበተሩ ውሸትን እንደ እውነት ተቀብለን የተከበረውን የሰው ልጅ ከዝንጀሮ ነው የመጣው ከሚለው አንስቶ እራሳቸውን አግዝፈው እኛን ለማሳነት እንዲሁም እራሳችን እንደትንሽ እንድናይ ከባድ እና ተደጋጋሚ እንዲሁም የተቀናጀ ውሸቶችን እየነገሩ ሲያደነዝዙን ኖረዋል፡፡ እውነቱ ግን መውጫው አይቀርምና በየግዜው እየተገለጠ ይመጣል፡፡ ይህ አንዱ ማስረጃ ነው፡፡ ከአገራችን ም ይሁን ከአፍሪካ በቆዳ ስፋት እጅግ የሚያንሱ አገራት/አህጉራት ትልቅነታቸውን ለማሳየት ከሚደልሉባቸው አንዱ ማሳያ አሁን በስራ ላይ ያለው የአለም ካርታ ነው፡፡ ለውጡን ተመልከቱ
ተጨማሩ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለማግኘት
ኮሜንት፣ ሼር ያርጉ ፣ ላይክ ያድርጉ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Addis Abeba