Halaba People Development Association

Halaba People Development Association

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Halaba People Development Association, Public Figure, Halaba zone, Alaba K'ulito.

Photos from Halaba Tv's post 10/05/2026
Photos from Halaba People Development Association's post 10/05/2026

የሀላባ ህዝብ ልማት ማህበር (HPDA) ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ኑሪዬ፣ የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ “በርበሬዎቹ” ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደጉ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ ለክለቡ፣ ለተጫዋቾች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለአመራሮች፣ ለደጋፊዎች እንዲሁም ለመላው የሀላባ ህዝብ ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
=======================//==============//================

አቶ ጀማል ኑሪዬ በመልዕክታቸው፣ ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀላባ ህዝብ ለስፖርት ያለውን ጥልቅ ፍቅር፣ አንድነትና የማይናወጥ ድጋፍ ያሳየ ኩራት መሆኑን ገልጸው፣ ክለቡ ያስመዘገበው ድል ለመላው የሀላባ ማህበረሰብ የደስታና የክብር ምዕራፍ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተለይም የሀላባ ህዝብ በዚህ ዓመት በራሱ አቅም፣ በህዝባዊ ተሳትፎና በከፍተኛ መስዋዕትነት የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየምን በመገንባት ያሳየው አንድነትና ቆራጥነት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፣ የ“በርበሬዎቹ” ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ ለዚህ ታላቅ ህዝባዊ ጥረት የተገኘ የደስታ ሽልማት እና የህዝቡ ትጋት ፍሬ መሆኑን አስገንዝበዋል።

“የሀላባ ህዝብ ለስታዲየሙ ያደረገው መስዋዕትነትና አንድነት ታሪካዊ ነው፤ የክለቡ ይህ ስኬት ደግሞ ለህዝቡ የተመለሰ ትንሹ የደስታ ስጦታ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም የሀላባ ህዝብ ልማት ማህበር (HPDA) ከክለቡ ጅማሬ ጀምሮ ከቡድኑ ጎን በመቆም የሞራል፣ የማበረታቻና የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው፣ ይህ ስኬት የተባበረ ጥረትና የህዝብ አንድነት ፍሬ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጀማል ኑሪዬ በመጨረሻም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የሀላባ ተወላጆችና የሀላባ ወዳጆች ክለቡን በገንዘብ፣ በሞራል፣ በሀሳብና በማንኛውም አቅም በተባበረ መንገድ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። ክለቡ በፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የሚፈራና የሚከበር ታላቅ ክለብ እንዲሆን የሁሉም ድጋፍና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።

በመጨረሻም ዛሬ በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በሚካሄደው የጀግኖቹ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ መላው የሀላባ ህዝብና የሀላባ ወዳጆች በነቂስ ወጥተው ቡድናቸውን በክብርና በደማቅ ሁኔታ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“በርበሬዎቹ” የሀላባ ኩራት!
ፕሪሚየር ሊግ የሀላባ አዲስ ምዕራፍ! ⚽🔥🏆

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Alaba K'ulito?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Halaba Zone
Alaba K'ulito