Ware Bariso

Ware Bariso

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ware Bariso, Digital creator, OROMIA, Asella.

Photos from Oromia Communication Bureau's post 03/02/2026
03/02/2026

በውይይትና በዲፕሎማሲ ገበያ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ድርሻ እንዲኖራት እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጦርነት ሳይሆን በውይይት እና በዲፕሎማሲ ገበያ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ድርሻ እንዲኖራት ለማድረግ እየተሰራ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ዲፕሎማሲ እና የቀጣናዊ ትስስር ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ እንዳይለያይ የተጋመደ በትብብር እንዳይሰራ ደግሞ የብሔራዊ ጥቅም ችግሮች፣ ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት እና ፉክክሮች ያሉበት ቀጣና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቀጣናው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ፣ የብዝሃ ቋንቋ እና ባህል ባለቤት መሆኑን ገልጸው÷ ነገር ግን አንዱ ለአንዱ ጋሻ ሲሆን ሌላኛው ጥይት አቀባይ በመሆኑ ተገቢውን ሰላም እና ዕድገት ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አብራርተዋል፡፡

ውጥረቶችን ለማርገብ እና ቀጣናዊ ትስስርን ለማምጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመጥቀስ÷ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሊቀረፉ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ደህንነቷን ለማረጋገጥ የባህር በር ያስፈልገኛል በማለት ጥያቄ ማቅረቧን እና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችም እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታሪክ የቀይ ባህር ባለቤት እንደነበረች አስታወሰው÷ በጦርነት ሳይሆን በውይይት እና በዲፕሎማሲ ገበያ የቀይ ባህር ድርሻ እንዲኖራት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

5 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የቀይ ባሕር ከ20 ሚሊየን የማይበልጥ ህዝብ ባላቸው ሀገራት የተሸፈነ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያ 130 ሚሊየን ሕዝብ ይዛ የቀይ ባህር ድርሻ እንደሌላት ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ ፍትሐዊ ካልሆነ በዓለም ላይ ፍትህ የለም ነው ያሉት፡፡

የባህር በር ጥያቄው እንዳይሳካ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸውን በመጠቆም÷ ኢትዮጵያን ጎድቶ ትርፋማ መሆን አይቻልም ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሚኪያስ አየለ

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-

Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 03/02/2026
08/08/2025
14/04/2025

በአማራ ህዝብ ስም እንታገላለን የሚሉ የሰፈር አለቆች በጥቅም እና በስልጣን ጥማት እርስ በእርስ የተባሉ ይገኛሉ። ይህ የጽንፈኛዉ ቡድን ገና ከጅምሩ በሶስት ተከፍሎ የተመሰረተ ሲሆን፤ አሁን ስንጥቁ ሰፍቶ እርስ በእርሱ ጦር የሚዘማመት፤ እርስ በእርስ በሴራ የሚተላለቅ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ከሆነ ቆየ።

ከሰሞኑ ደሞ ሌላ የዚህን ቡድን ልዩነት የሚያሰፋ በአማራ ህዝብም ላይ ትልቅ መከራን ሊያመጣ የሚችል ክስተት ተፈጥሯል።

በዚህ ክስተት ምክኒያት የዚህ ጽንፈኛ ቡድን #ልዩነቶችን እየሳፋ የመጣበት ምክንያት ከህወሓት ጋር እንሰራለም አንሰራም በሚለዉ ሲሆን ይህም ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ሰፍቶ አመራሮችን ማሳደድ የጀመሩበት ደረጃ ደርሰዋል።

ባሳለፍነዉ ሳምንትም በደቡብ ጎንደር ሲንቀሳቀስ የነበረውን በፋኖ ከፍያለው ደሴ የሚመራውን ቡድን የዘመነ ካሴ ታጣቂዎች እራሱን ፋኖ ከፍያለው ደሴን ጨምሮ መደምሰሳቸዉ የዚህ ክፍፍል አንዱ መዘዝ ነዉ።

14/04/2025

ፋኖ የተባለው አሸባሪ ቡድን ለዝርፊያ ከተቋቋመ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ይሔ ነው የማይባለ በደል እና ሰቆቃ ሲያደርስ እና ሲዘርፍ ቆይቷል አሁን ደግሞ ሌባ ሲካፈል የጣላል እንዲሉ እርስ በእርስ መዋጋት ከጀመሩ ሰበትበት ብሏል።

የውጊያው መነሻ ከህውኃት ጋር እንሰራለን አትሩም ቢሆንም ቁርሾው የተነሳው ቀደም ብሎ ነው የጽንፈኝነት መጨረሻው የራስን ቤት ማፍረስ እንደሆነ በነዚህ ድኩማን መረዳት ይቻላል

ባሳለፍነዉ ሳምንትም በደቡብ ጎንደር ሲንቀሳቀስ የነበረውን በፋኖ ከፍያለው ደሴ የሚመራውን ቡድን የዘመነ ካሴ ታጣቂዎች እራሱን ፋኖ ከፍያለው ደሴን ጨምሮ መደምሰሳቸዉ የዚህ ክፍፍል አንዱ መዘዝ ነዉ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Asella?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


OROMIA
Asella