Ebrahim Mussa
I thank Allah for everything🙏 I Am Muslim
16/04/2024
የኢራን ፕሬዝዳንት ከእስራኤል በኩል ለሚሰነዘር ጥቃት 'ከባድ' ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ቃል ገቡ
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከኳታር አሚር ጋር ሀገራቸዉ በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን የአየር ላይ ጥቃት ስኬታማ እንደሆነ ገልፀው ኢራን ወደፊት በጥቅሟ ላይ ስጋት ካለባት የበለጠ “አሳማሚ” ጉዳት እንደምታደርስ በነበራቸዉ የስልክ ቆይታ ተናግረዋል፡፡
የኢራን የዜና ወኪል እንደዘገበው በኢራን ፍላጎት ላይ የሚወሰደው ትንሹ እርምጃ በእርግጠኝነት በሁሉም አጥፊዎቹ ላይ ከባድ ፣የተስፋፋ እና የሚያሰቃይ ምላሽ ይጠብቀዋል ስንል በግልፅ እንናገራለን” ብለዋል ።የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ ካኒ ለመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ቴህራን ማንኛውንም የእስራኤል አጸፋ ተከትሎ የምትወስደው እርምጃ እንዳሁኑኢራን ተጨማሪ 12 ቀናት ምላሽ ለመስጠት ስለማትጠብቅ በጥቂት ሰከንዶች ልዩነት መልስ እንሰጣለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ በበኩላቸዉ ሀገራት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ አሳስበዋል፡፡የእስራኤል ከፍተኛ ዲፕሎማት "በኢራን ላይ የፖለቲካ ጥቃትን" እየመራሁ እገኛለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ወደ 32 ለሚሆኑ ሀገራት ደብዳቤ ልኬያለሁ እናም በኢራን ሚሳኤል ጥቃት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል እና የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ለመጠየቅ በደርዘን የሚቆጠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እና የአለም መሪዎችን አነጋግሬያለሁ።
ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ ባጋሩት መልዕክት አክለውም ኢራንን አሁኑኑ ማቆም አለብን ጊዜው ከማለፉ በፊት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የእስራኤል ወታደራዊ አዛዥ ሄርዚ ሃሌቪ በኢራን ጥቃት ቀላል ጉዳት በደረሰበት ወታደራዊ ጣቢያ በመገኘት ለወታደሮች እንደተናገሩት የኢራን ድርጊት የአጸፋ ምላሹን ያገኛል ሲሉ ተናግረዋል።ሃሌቪ የኢራንን ጥቃት ለመመከት ለተሰበሰበው ጥምረት ምስጋና ቢያቀርቡም የጥምረቱ አባላትን ግን በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢራን አቻቸው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ “ኢራን ሁኔታውን በጥሩ ሁኔታ መቋቋም እና የራሷን ሉዓላዊነት ስትጠብቅ ቀጣናውን ለተጨማሪ ውጥረት ልትዳርግ እንደምትችል ይታመናል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
28/01/2024
Afar The land of origin ❤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Semera
Awash
7250