Hawassa Polytechnic College

Hawassa Polytechnic College

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa Polytechnic College, College & University, Hawassa, Awassa.

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 02/11/2025

በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 ስልጠና ዘመን የገበያ ፍላጎት ቅድሜ ጥናትና Validation እና የኢንድስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ የልምድ ልውውጥ ህደት የመገመበትን Workshop አካሄደ ።

ኮሌጁ በ2018 ሥልጠና ዘመን ገበያው/ ኢንድስትሪው ዬትኛውን ሙያ እና ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ይፈልጋል የሚለውን የጥናት ሪፓርት ባቀረበበት መድረክ
✅የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት
✅የኢንዱስትሪ ባለቤቶች
✅የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2ቱ ዘርፍ ዳይረክተሮይቶች
✅የሀሳ ዩንቨርስቲ የጥናትና ምርምር ምሁራን
✅የኮሌጁ የ2ቱም ዘርፍ ባለሙያዎች
✅የኮሌጁ የየዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የኮሌጅ ም/ዲን እና የሠልጣኝ አሠልጣኝ ልማት ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኢዩኤል ዮኔ እንደ ሀገር የተቀመጡ የሪፎርም አጀንዳዎችን ለማሳካት ኢንድስትሪውን ፍላጎት መነሻ አድርጎ በማሠልጠን የበቃ ዜጋን ለገበያው ለማቅረብ ብቸኛው መንድ የኢንዱስትሪውን የሰው ኃይል ፍላጎት በጥናት መለየት ነው ስሉ አሳባቸውን ገልፀዋል ።

በዚሁ መድረክ የቀረበው ሌላኛው ርዕሰ ጉዳይ የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ አባላት የልምድ ልውውጥ ህደትና ግኝቶች ላይ ሲሆን

የኮሌጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላቱ
👉በELSE Addis/Rider textile factory
👉በMNS textile manufacturing company
👉በFederal Tvet Institute/ በተለይም ምን እንደሚመስል ሰፊ ጉብኝትና ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር ጋር በቂ ውይይት ማድረጋቸውን በኮሌጁ IAB ሰብሳቢ አቶ ወሌ አበጋዝ አንስተዋል።
በዕለቱ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ እና የኮሌጁ አመራሮች ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገሩበት ሌላኛውና ዋነኛው ጉዳይ የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲሱ የTextile and Garment _Factory_Autonomous ሆኖ ወይንም በከፊል ነፃ ሆኖ እራሱን ችሎ ለማሠልጠንና ለማምረት እንድሁም አገልግሎት ለመሥጠት ወደ ሥራ እንድገባ አድቫይዘሪ ቦርዱ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑንም የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሣ አንስቷል።

የኮሌጁ ዲን በገለፃው በልምድ ልውውጥ ካየናቸው የTextile Manufacturing ኩባኒያዎች አንፃር ስታይ የቁጥር ብዛት ልዩነቶች ይኑሩ እንጅ የሀዋሳ ፓሊ አዲሱ Training Factory ሁሉንም ለማሠልጠንና ለማምረት ብቁ የሆኑ ዘመኑ የሚፈልገው ትላልቅ ማሽነሪዎች ያሟላና በአሁን ሰዓት ወደ ስራ ለመግባት የምቸግረው የግብት ችግር አለመኖሩንም አረጋግጠዋል ።

በመጨረሻም የኢንድስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ በኮሌጁ ከሌለው ጊዜ በማካፈል ፣ በዕቀት ፣ በሀሳብና በተለያዩ እያሳየ ላለው አብሮነትና ድጋፍ የኮሌጁ ዲን አመሥግነው የዕለቱን ውይይት አጠቃለዋል ።

ሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

24/04/2025

እንኳን ደስ አላችሁ

የኢንስቲትዩቱ ሀዋሳ ካምፓስ ራሱን ችሎ ISO 900፡2015 የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ሆነ።

ቀደም ሲል የደቡብ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመባል ይታወቅ የነበረውና ከ2016 በጀት ዓመት ጀምሮ ተጠሪነቱ ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሆነው ተቋም በሰራው የጥራት ሥራ አመራር መሰረት ተገቢውን የኦዲት ሂደት አልፎ ተሻላሚ ሆኗል።

የኢንስቲትዩታችን ማኔጅመንት ለካምፓሱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና በሂደቱ አስተዋፆኦ ለነበራቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ግቢ በ2016 ዓ/ም መሰል ሽልማት መሸለሙ የሚታወስ ነው።

ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ዩቲዩብ http://www.youtube.com/fdretvtinstitute
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
ቲክቶክ www.tiktok.com/

Want your university to be the top-listed University in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Hawassa
Awassa