Loma Bossa Woreda Communications

Loma Bossa Woreda Communications

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Loma Bossa Woreda Communications, Government Organization, Awassa.

Photos from Loma Bossa Woreda Communications's post 29/06/2026

የኤላ-ሀልአኒ ጠጠር መንገድ ግንባታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንደሚፈታላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከተሳትፏዊ ግብርና እና የአየር ንብረት ሽግግር (PACT) ፕሮግራም እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ ሎማ ቦሳ ወረዳን ከዛባ ጋዞ ወረዳ ጋር የሚያገናኘውን ኤላ-ሀልአኒ 7 ኪሎ ሜትር ነባር መንገድ ግንባታ አስጀምረዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ጮራሞ የህብረተሰቡ የረዥም ዘመናት ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የኤላ-ሀልአኒ መንገድ ግንባታ በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የመንገዱ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ህዝቡ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

ስራውን በይፋ ያስጀመሩት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በላቸው በበኩላቸው፣ መንገድ የሁሉም ልማት መሠረት በመሆኑ የማልማትና የማስተዳደር ስራ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ሽርኮ፤ በመጠናቀቅ ላይ ባለው በጀት ዓመት ብቻ 2 መንገዶች ግንባታ ተደርጐ ለአገልግሎት የበቁ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዛሬ የተጀመረው 3ኛው የኤላ-ሀልአኒ ጠጠር መንገድ ግንባታ በመልካም አስተዳደር ረገድ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ይረዳል ብለዋል።

አክለውም በዶዘር ከፈታ ከማከናወኑ በተጨማሪ ማቴሪያል የማምረትና ማስገባት፤ በግሬደር የማስተካከል እንዲሁም በRoller compactor (በኡሩሎ) የመጠቅጠቅ ስራዎችንም ያካተተ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

የPACT ፕሮግራም ዓላማው ማህበረሰብ መርህ እና ለምርታማነት ተስማሚ የአየር ንብረትና ስነ-ምዕዳር እንዲሁም በግብርና ልማት ላይ አቅዶ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ አበራ ገልጿል።

ከነዋሪዎቹ አንዳንዶች በሰጡት አስተያየትም፣ በአካባቢያቸው ምቹ የመንገድ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምርታቸውን ለገበያ ለማውጣት እንደሚቸገሩ ገልጸው፣ አሁን ግንባታ ሲጠናቀቅ ይህን ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ተናግረዋል።

ነፍሰ ጡር እናቶችንና ህሙማን ህክምና ለማግኘት በሚያደርጉት ጉዞ ምቹ መንገድ ባለመኖሩ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱንም ይናገራሉ።

በወረዳው መንግስት፣ በPACT ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚገነባው ይህ የመንገድ ግንባታ ዛሬ የወረዳው መንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Awassa