Ethio Press
Trusted News where you can find
10/05/2022
በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።
ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9.13 ቢሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ካገኘው 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በሦስት እጥፍ ገደማ ያደገ ነው።
ነገር ግን ድርጅቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ገበያ መውጣቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንዲያጣ እንዳደረገው አሳውቋል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተዳክሞ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ማንሰራራት ሲጀምር የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ እየጨመረ ቢመጣም የቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጣራ እንዲነካ አድርጎታል።
የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ መጨመር ለኢነርጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል።
28/04/2022
ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡
ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡
‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡
አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡
ፑቲን ከዚህ በፊት በለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡
የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ወቅት ነው።
በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት አድርገው ነበር።
በዚህ ጉብኝታቸው ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡
በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡
መረጃው የቢቢሲ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Piasa
Awassa