Alte pictures

Alte pictures

Share

Welcome To Our Page. I Like Captures Photo More in Natural Photo. in this page Natural Photos & Othe

Photos from Alte pictures's post 19/02/2026

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት ስብሰባ ጀምረናል።

This afternoon, we commenced the Prosperity Party’s council meetings to deliberate on our strategic priorities.

Photos from Alte pictures's post 17/02/2026

የቱርክዬው "ቶግ" (Togg) የኤሌክትሪክ መኪና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስጦታ ተበረከተ

የቱርክዬው ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በቱርክዬ የቴክኖሎጂ ዕድገት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውንና የሀገሪቱ ኩራት የሆነውን "ቶግ" (Togg) የኤሌክትሪክ መኪና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስጦታ አበርክተዋል።

ይህ ስጦታ ከመኪናነቱ ባለፈ በኢትዮጵያና በቱርክዬ መካከል ያለውን የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ቴክኖሎጂና ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ አጋርነት ማደጉን የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ተደርጎ ተወስዷል።

ስጦታ የተበረከተው መኪና ዝም ብሎ ተራ ተሽከርካሪ ሳይሆን ቱርክዬ በዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ያመረተችው የመጀመሪያው ሀገር በቀል ዘመናዊ መኪና ነው።

መኪናው ሙሉ በሙሉ በቱርክዬ መሐንዲሶች የተቀረጸና የተገነባ ሲሆን የቱርክዬን የኢንዱስትሪ ብቃት ለዓለም ያስተዋወቀ ፕሮጀክት ነው።

ቶግንከመኪናነት ባለፈ እንደ ተንቀሳቃሽ ስማርት መሣሪያ (Smart Device) ነው የሚታየው የላቀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂና የኢንተርኔት ግንኙነት ሥርዓት የተገጠመለት ነው።

ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ በመሆኑ ልክ እንደ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማትንና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለሚያበረታቱ ሀገራት ተመራጭ ያደርገዋል።

የመኪናው ውጫዊ ገጽታ የቱርክዬን ባሕላዊ ቅርሶች (ለምሳሌ የቱሊፕ አበባን) ከዘመናዊ ምቾት ጋር አጣምሮ የያዘ ውበት አለው።

ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ይህንን መኪና ለወዳጅ ሀገራት መሪዎች በስጦታ መስጠታቸው የቱርክዬን የቴክኖሎጂ አጋርነት ፍላጎት ያሳያል።

Want your business to be the top-listed Photography Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


ሂጣታ
Awassa