EECMY Referal Congregation Hawassa

EECMY Referal Congregation Hawassa

Share

ለወንጌል የምትኖር ቤተ-ክርስቲያን!!

Photos from EECMY Referal Congregation Hawassa's post 24/05/2026

የ"ጉበኛ ለትውልድ" የጸሎት መርሀግብር ለሀገር ሰላምና ለምርጫ ስኬት ተጠናቀቀ::

"ጉበኛ ለትውልድ ዓለም አቀፍ አገልግሎት" በኢትዮጵያ ሰላም፣ ለመንፈሳዊ መነቃቃት እና ለምርጫው ስኬታማነት ሲያካሂድ የቆየውን የ5 ቀናት ልዩ የጾምናጸሎት ኮንፈረንስ በድምቀት አጠናቀቀ።
በኮንፈረንሱም
በግንቦት ወር ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት እና የሀገሪቱን ሰላም በጸሎት አደራ ብለዋል።

በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የመጨረሻው ዘመን ሪቫይቫል እንዲቀጣጠልና አማኞች ክርስቶስን እንዲመስሉ ጥሪ ቀርቧል ::
በሀገራችን የሚታዩትን የሙስና፣ የጥላቻና የደም መፋሰስ ችግሮች እንዲያቆሙ ምልጃ ተደርጓል።
ለወጣቱ ትውልድ፡ 70 በመቶው የኢትዮጵያ ወጣት በሥነ-ምግባር የታነጸ፣ በሳይንስና በፈጠራ የዳበረ አእምሮ ያለው ትውልድ እንዲሆን ተጸልየዋል።
ለኢትዮጵያውያን፡ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ወገኖቻችን ጥበቃና ሰላም እንዲሁም ለእስራኤል ሰላም ልዩ ምልጃ ቀርቧል።
የአገልግሎቱ ባለራዕይ አገልጋይ ነገደ ወልደ ሰንበት፣ አማኞች በጸሎትና በአንድነት ለሀገር ሰላምና ለንጹህ ሕይወት እንዲተጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ኢቫንጀሊካል ዜና ሩት ዋቅጅራ
ዘገባው ዳንኤል አንተነህ ነው

Photos from EECMY Referal Congregation Hawassa's post 19/05/2026

በመጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዋና ቢሮ የወጣ ታሪካዊ ውሳኔ

መካነ ኢየሱስ ራሳቸውን "ሐዋርያት" እና "ነቢያት" ብለው የሚጠሩትን ጨምሮ የሌሎች ቤተ እምነት አገልጋዮች በመድረኬ ላይ እንዲጋበዙም ሆነ አገልጋዮቼ በእነርሱ መድረክ ላይ እንዲቆሙ አልፈቅድም ብላለች። ይህንን በሚያደርጉ እና ውሳኔዋን በሚተላለፉ ቄሶችና ወንጌላውያን ላይ ቅስናቸውን እስከ መግሰስ እና ከወንጌላዊነት መደብ እስከ ማንሳት የሚደርስ የማያዳግም እርምጃ እንደምትወሰድ ጠንከር ያለ መልእክት አስተላልፋለች።

"ብልጥ ልጅ የተሰጠውን ይዞ ለቀረው ያለቅሳል" እንዲሉ፣ ስለዚህ ታላቅና ታሪካዊ ውሳኔ መሪዎቻችንን እያመሰገንን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከካውንስል እና ከሉተራን ዎርልድ ፌዴሬሽን ሕብረት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለቃ መውጣቷን እስክናረጋግጥ ድረስ ቃለ እግዚአብሔርን መሠረት ያደረገ ሙግታችን የሚቀጥል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

Photos from EECMY Referal Congregation Hawassa's post 18/05/2026



‎የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን
‎ ================================
‎ ግንቦት 09/09/2018 ዓ.ም ሀዋሳ

‎መልዕክት አቅራቢ: ፍሬው ሀ/ማሪያም

‎የመነሻ ጥቀስ: መዝሙር ዳዊት 25_3

‎ርዕሰ: ተስፋችንን አጥብቀን እንያዝ ።
‎ -----------------------------
‎ተስፋችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

‎ 1. ተስፋ የሰጠን እርሱ የታመነ ነውና ተስፋችን የሆነውን ኢየሱስን በመከራ ጊዜም ይሁን በደስታ ጊዜ እርሱን ማሰብ ያስፈልጋል።

‎2. በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ያደረገ ሰው ምንም ዓይነት ችግር በሚደርስበት ጊዜ በችግርና በመከራ ውስጥ ሆነው ተስፋው ኢየሱስ እንደሆነ ያስባል አይናወጥም።

‎1. እግዚአብሔርን ተስፋ ያደረገ ሰው ተስፋውን በችግር፣በመከራ እንድሁም በስኬት አይለካም። በሞት ጥላ ውስጥ ሆነው የማይሞት ተስፋ ይጠበቃል።
‎2. ተስፋን አጥብቆ የያዘ ሰው ለቤተክርስቲያን ፣ ለቤተሰበ፣ ለራሱ እና ለሀገር እንደ አብርሃም በረከት ይሆናል። ዘፍ 12፥1

‎ስለዚህ ከሁኔታው፣ ከችግር፣ከመከራ፣ከስኬት እና ካለን ነገር በላይ እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ አያሳፍርም። ተስፋችን በእምነት እና በፍቅር በትዕግሥትም እንያዝ።

‎“አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።”
‎ መዝሙር 25፥3

‎ ኢየሱስ ጌታ ነው!!
‎ 👇
‎ የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ

‎ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Referal Mekanyesus
Awassa
REFERALMEKANYESUS