Mereja Plus
News page
13/07/2025
በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።
_________
በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።
አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
FB: https://www.facebook.com/MerejaPlus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
12/07/2025
“ ቼልሲ ልክ እንደ እኛ ነው “ ኤንሪኬ
___________
የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የነገው የቼልሲ የፍፃሜ ጨዋታ ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል።
ስለ ተጋጣሚያቸው ያነሱት ሉዊስ ኤንሪኬ “ ቼልሲ ሲያጠቃ እና ሲከላከል ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ቡድን ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም “ በአካል ጠንካራ ከሆነ ቡድን ጋር የምናደርገው ከባድ ጨዋታ ይሆናል ቼልሲ የተሟላ ቡድን ነው ጨዋታው ቀላል አይሆንልንም።" ብለዋል።
" አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ እና የቡድኑን አጨዋወት አደንቃለሁ ፣ ትልቅ ቴክኒካል ብቃት እና ጥሩ ተጨዋቾች አሏቸው።" ኤንሪኬ
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
10/07/2025
በደቡብ ኢትዮጵያ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ሕይወታቸው አለፈ
____________
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ተቀብረው ሕይወታቸው አለፈ፡፡ የአፈር ናዳው ዛሬ ጠዋት የደረሰው በወረዳው ዲሜ ገሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡
የናዳ አደጋው የደረሰው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ምሶሶ ተሸካሚ ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮ በማከናወን ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ መሆኑን የሣላማጎ ወረዳ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በናዳው የሦስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ግዳጁ ጨነቀ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የሟቾቹ አስክሬን በቁፋሮ የወጣ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ተጎጂዎች ደግሞ በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ጣቢያ የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አቶ ግዳጁ ተናግዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ባለፈው ዓመት ክረምት ደረሶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸው አይዘነጋም።
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
10/07/2025
ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ለሚገነባው የ3 ቢሊዮን ዶላር ማዳበሪያ ፋብሪካ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጠ
___________
የአፍሪካ ቀዳሚ ባለጸጋና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ፣ በኢትዮጵያ የ3 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው ዘመናዊ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በይፋ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
"ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዚህም ሰርቶ አዳሪ እንጂ አውርቶ አዳሪ አለመሆናችንንም በተከታታይ እያሳየን እንቀጥላለን። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል። " ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የፋብሪካው ግንባታ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ40 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ በተለይም ከሩሲያ እና ከሌሎች የውጭ ሀገራት የምታደርገውን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎለታል።
የማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ ሲጠናቀቅ በአገር ውስጥ የዩሪያ እና ናይትሮጅን ማዳበሪያዎችን ያመርታል፤ ይህም ለኢትዮጵያ ገበሬዎች በቀጥታ ተደራሽ የሚሆን ከመሆኑም በላይ፣ በርካታ የስራ እድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለ 2017 የምርት ዘመን የሚያስፈልገውን 25 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት 1.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት አፅድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።
Source: capitalethiopia
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
09/07/2025
ተጠባቂ ጨዋታ ፔኤስጂ ከማድሪድ
የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ለፍጻሜ ለማለፍ ከስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የሚገናኝበት ጨዋታ ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡
የ15 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ማድሪድ ከወቅቱ የአውሮፓ ምርጡ ቡድን የሚደርገው ትንቅንቅ።
በግሉም በቡድንም ከፔኤስጂ ጋር የተሳካ አመት ያሳለፈው ሌላኛው ፈረንሳዊ አጥቂ ኡስማን ዴምቤሌ ለማድሪድ ተከላካዮች ትልቁ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል ኬይሊያን ምባፔ የቀድሞ ክለቡን ለመጀመርያ ጊዜ የሚገጥምበት ይሆናል፡፡
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Awassa