Resilience mind
A resilient mind bends but never breaks; it learns, adapts, and rises stronger every time.
17/02/2026
የጭንቀት በሽታ (Anxiety Disorders)
ጭንቀት ማለት ህይወታችን ላይ አደጋ የሚፈጥር ነገር ሳይኖር አዕምሮሯችን አደጋ እንዳለ ማሰብ ሲጀምር የሚሰማን ስሜት ነው::
ፍርሃት እና ጭንቀት ተመሳሳይነት ሊኖራቸው ይችላል:: ነገር ግን ፍርሃት ስንል ያልጠበቅነው ነገር ህይወታችን ላይ ከውጪ አደጋ የሚፈጥር ሲመስለን የሚፈጠር ስሜት ነው።
ፍርሃት የፈጠረብን ነገር ሲወገድ አብሮ የፍርሃት ስሜቱም ይጠፋና ወደ ቀድሞው ማንነታችን እንመለሳለን
የጭንቀት ስሜት በዛም አነሰ ሁሉም ሰው በየቀኑ ሊሰማው ይችላል:: ነገር ግን የጭነቀት ስሜቱ ተረጋተን ነገሮችን ማድረግ እስኪሳነን ደረጃ ከደረሰ የጭንቀት በሽታ ሊሆን ስለሚችል ቶሎ ስር ሳይሰድ ወደ አዕምሮ ሃኪም በመሄድ እርዳታን ማግኘት ይኖርብናል::
የጭንቀት በሽታ ከሁሉም የአዕምሮ ህመም አይነቶች ብዙ ግለሰቦችን የሚያጠቃ ሲሆን ከመቶ 17.7% የሚሆኑ ግለሰቦች ተጠቂ ናቸው:: ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በይበልጥ በዚህ በሽታ ይጠቃሉ::
የጭንቀት ህመም መገለጫዎች ምንድናችው?
የጭንቀት ህመም በአማርኛው አንድ አድርገን ጠራነው እንጂ የብዙ በሽታዎች ስብጥር ነው:: እነዚህም:-
-የጥቅል ጭንቀት (Generalized Anxiety Disorders)
-ድንገተኛ መሸበር (panic disorder)
-ማህበራዊ ፍርሀት (Social anxiety disorder)
- ፎብያ (specific phobia) እና ሌሎችም
የጭንቀት በሽታ እንዴት ይከሰታል?
- አካላዊ፦ ከቤተሰብ በዘረ-መል አማካኝነት የሚወረስ፥ ከድብርት በሽታ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ተጓዳኝ ህመሞች እና የመሰሳሰሉት
- የተለያዩ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች (መደፈር፣ ወላጅን በሞት ማጣት)
የጭንቀት በሽታ ምልክቶች ምንድናቸው?
እነዚህ ምልክቶች የጥቅል ጭንቀት በሽታ ምልክቶች ናቸው:-
-ስድስት ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ለጥቃቅን ነገሮች አብዝቶ መጨነቅ እና የሚከተሉት ሶስት ምልክቶች ካሉ
- ተረጋግቶ ስራን ያለመስራት
- የማስታወስ ችግር እንዲሁም
-የታሰበውን ስራ በወቅቱ አለመፈፀም
- በቀላሉ መድከም
- ትኩረት መሰብሰብ አለመቻል
- የእንቅልፍ ችግር
የጭንቀት በሽታ ህክምና አለው?
የተለያዩ የህክምና አይነቶች እነዚህን በሽታዎች ለማከም እንጠቀማለን፦
1.የመድሃኒት ህክምና
የጭንቀት ስሜትን ለማጥፋት የሚያስችሉ የተለያዩ መድሃኒቶች በገበያ ላይ ይገኛሉ:: እነዚህ መድሃኒቶች በሃኪም ትዕዛዝ ብቻ ለአጭር ጊዜ እና ለረጅም ጊዜ የሚሰጡ ናቸው::
2. የንግግር ህክምና (pychotherapy)
የጭንቀት ህመም ምንነት ማስተማር
ጭንቀት አምጪ ነገሮችን እንደገና እንዴት መቅረብ እንደሚቻል እና ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት እንዲኖር ማስቻል
🗣ማሳሰቢያ፦ የሚያስጨንቁ ሁኔታዎችን መፍራት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ከመጠን ካለፈ የህመም መገለጫ ሊሆን ስለሚችል ከላይ ከተገለፁት ምልክቶች እርሶ ላይ ከታየ ወደ ህክምና በመሄድ መታየት መልካም ነው::
(ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Hawassa
Awassa
HAWASSA,