Kuukisa Media Network

Kuukisa Media Network

Share

Kuukisa media network

31/01/2020

♣♣♣ሲዳማ ክልል ከሆነ ቆይቷል!!♣♣♣
* የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊም ሆነ ፓለቲካዊ ውሳኔ ተወስኖበት ያለቀ ጉዳይ ስለሆነ ለላ ውሳኔ ለመወሰነ ማሰብ አንደኛ ቅዤት ነው አልያም ደግሞ ለህዝብ ድምፅና ለጋራ ውሳኔ ታማኝ ያለመሆን የተደበቀ የአስመሳይነት ባህርይ ምልክት ነው።
የሲዳማ ሕዝብ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ እጅግ በጣም አስፈላግ መሆኑን አሮገውን ክልል በህዝብ ተመርጦ ያስተዳድር የነበረው "ደኢህደን"ከመሞቱ በፍት በተለያዩ አደረጃጀቶቹ አማካይነት ጠንካራና የማይቀለበስ (irreversebile) ውሳነዎችን አስተላልፏል። በደኢህደን ስራአስፈፃም፥በደኢህደን ማስከላዊ ኮሚቴ፥በደኢህደን ጠቅላላ ጉባኤ እንድሁም ደግሞ በመጨረሻም በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ይነሳ የነበረውን የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በሳይንሳዊ ጥናት መመለስ አለብኝ ብሎ ያደራጃቸው የምሁራን ቡድን ግኝትም የሲዳማ ህዝብ "በክልል ሊደራጅና እራሴን በራሴ ላስተዳድር" ብሎ የጠየቀው ጥያቄ በሳይንሳዊ ጥናትም ትክክል መሆኑን አረጋግጧል። ይሁንታዉ በደኢህደን ደረጃ ብቻ አላበቃም በሀገር ደረጃም በምርጫ አሸንፎ ሀግርቷን እያስተዳደረ ያለው ድርጅት በወቅቱ ኢህአደግ በአሁኑ ብልፅግና ፓርቲም ግልጽ ውይይት አድርጎ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ተገብ መሆኑን ፓርቲው ተቀብሎ መንግስት እንድያስፈፅም ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በመሆኑም የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ተገብና ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑንና በአፋጣኝ መመለስም እንዳለበት አሮገውን ክልል ሲያተዳድር የነበረው ድርጅትም ሆነ ኢህአደግ(ብልፅግና ፓርቲ) የማይወላዳ አቋም ይዞ መወሰኑ በሀገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ ሀቅ ነው። ታድያ የቱ ጋ ነው እኛ አልወሰንም የምል ክህደት እየመጣ ያለው? ይህማ ጭራሽ ቅዤት ነው።
ሁለተኛው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ህጋዊና ህገመንግስታዊ በመሆኑ ህገ መንግታዊና ህግዊ ውሳኔ አግንቶ ተግባራዊ መልስም ተንገንቶ ያለቀ ጉዳይ ነው። ማስረጃውም ግልፅ ነው። የደቡቡ ክልል መንግስት ም/ቤት የጥያቄውን አስፈላጊነት አምኖ በሙሉ ድምፅ አፅድቆ ፣ውሳኔውም በፁሑፍ ለምርጫ ቦርድ ቀርቦ በሪፌረንደም ምላሽ ተሰጥቶ እንድጠናቀቅና ጉዳዩን ለማስፈፀም ይረዳ ዜንድ ከ 75 ሚሊ. ብር በላይ ወስኖ የጥያቄውን አንገብጋብነትን በዝህ መልኩ አምኖ ተቀብሎ ታርካዊ ውሳኔ ወስኗል።ምርጫ ቦርድም በህዱቱ ላይ ከፍተኛ እንዝላልነት ቢታይበትም በመጨረሻ ላይ አስደናቅ ሥራ ሰርቶ ህገ መንግስታዊ ግዴታውን በጥንቃቄ ፈፅሞ ለህገ መንግስታዊ ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ምላሽ በመስጠት ሲዳማ በሪፌረንደም ክልል መሆኑን ወስኗል።ከወሰነም ከሦስት ወራት በላይ አስቆጥሯል። ታድያ ይህ ሁሉ ህጋዊ አካሄድ በመንግስት ውሳኔ አይደለ የተፈፀመው? ከዚህ ሁሉ ህጋዊ አካሄድ በኃላ እኛ አልወሰንም ማለት ለራስ ውሳኔና ለሕዝብ ድምፅ ታማኝ ያለመሆን ግልፅ ማሳያ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ የመጭው የምርጫ ተዓማንነት አስጊ ነው። ለማንኛውም ሕጋዊና ሕገመንግስታዊ ሂደትን በሚገባ ተፈፅሞበት የተጠናቀቀውን ስልጣን የክልሉ ም/ቤት ለሲዳማ ህዝብ በአስቸኻይ ያስረክብ ያስረክብ!!!!!

10/01/2020

በሞቃዲሾ በተፈፀመ ጥቃት 4 ሰዎች ተገደሉ...

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ መሃል ከተማ መኪና ላይ በተጠመደ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ፣ ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ።

ሌሎች አስራ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን ዕማኞች እና የህክምና አገልግሎት ሰራተኞች ገልጸዋል። ፍንዳታው የደረሰው ሳይዲካ መንገድ መጋጠሚያ ላይ ተሽከርካሪዎች በተኮለኮሉበት ወቅት መሆኑ ነው የተገልጸው።

መስቀልኛው መንገድ ከሀገሪቱ ፓርላማ እና ቤተመንግሥቱ አቅራቢያ መሆኑም ተጠቁሟል። የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

VOA

Want your business to be the top-listed Media Company in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Sidaama
Awassa