GREAT Vision College

GREAT Vision College

Share

"Knowledge is Life"
Knowledge for betterment of life, cognitive development, creativity, innovation & technology, sustainable development and economic growth.

Photos from GREAT Vision College's post 06/12/2025

እንኳን ለ20ኛው ብሔር ብሔረሰቦች በዓል አደረሰን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏 GREAT VISION COLLEGE

12/09/2025

Meeting in the Ministry of Education

Photos from GREAT Vision College's post 03/08/2025

ግሬት ቪዥን ኮሌጅ 2017ዓ/ም የምረቃ ፕሮግራም
ወልቂጤ, ኢትዮጵያ
ግሬት ቪዥን ኮሌጅ በሁሉም ካምፓሶች በዲግሪ እና በTVET ያሰለጠናቸውን 654 ተማሪዎች በዛሬዋ ቀን በወልቂጤ ከተማ በሃይርሽ አዳራሽ (በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ) በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
በምረቃ ላይ የክብር እንግዳ የነበሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ አሰፋ ደደቦ ባስተላለፉት መልእክት ግሬት ቪዥን ኮሌጅ ጥራት ያለው ትምህርት በማስተማር ሀገር ተረካቢ ትዉልድ ማፍራት እንዳለበት እና ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ፈጣሪ እንጂ ሥራ ጠባቂ መሆን እንደሌለባቸው አሳስበዋል::
በተጨማሪ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን ሰርገማ የግል ትምህርት ተቋማት በትምህርት ተደራሽነት ረገድ ከፍተኛ እያደረጉ ያሉት አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው, ከትምህርት ጥራት አንፃር ከፍተኛ ሥራ መሰራት እንዳለበት አሳሰበዋል, እንዲሁም ግሬት ቪዥን ኮሌጅ በ5ቱም ካምፓሶቹ ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች በወልቂጤ ከተማ ለማስመረቅ በመወሰናችሁ እናመሰግናለን.... የተንቢ ብለዋል...... በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸዉን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል::
የኮልጁ ኤክስክዩትቭ ም/ፕሬዚዳንት እ/ዶ/ር ታሪኩ ተክለፃድቅ የኮሌጁን አጠቃላይ ሁኔታ ያቀረቡ ሲሆን ኮሌጁ ትምህርት ሚኒስቴር እና ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ባስቀመጡት ስታንዳርድ መሰረት ለመስራት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው, የኮሌጁ ሴኔት እና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ባለቤቶች ኮሌጁን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቁርጠኛ መሆናቸዉን አስረድተዋል::
የምረቃ ፕሮግራም ስነስርአቱን እንኳን ደህና መጣችሁ... የተንቢ... ያሉት ደግሞ የወልቂጤ ካምፓስ ዲን አቶ ድላሞ አበበ... ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የመጣችሁ ተመራቂ ተማሪዎች እና አስመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን ወደ ዉብቷ ወልቂጤ ከተማ ደህና መጣችሁ ብለዋል::
የኮሌጁ የሚዲያ ክፍል
27/11/2017ዓ/ም

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Awassa