Guuta Christianawi Ministry
Guuta Christianawi Ministry is religious organizatio founded with the purpose of equipping ministers
19/03/2024
ከዚህ ቀደም የተዘመሩና ቆየት ያሉ ዝማሬዎች በተደጋጋሚ ስትጠይቁ የነበራችሁ ወገኖች ሁሉ በዩቲዩብ እና በቲክ ቶክ ገጼ ላይ እንደምታገኙ እየገለጽኩ አገልግሎቱ ለሌሎችም እንዲደርስ ሳብስክራይብ፣ ላይክና ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።
ኃይሌና ጉልበቴ - ዘማሪ ለገሠ ጂሎ "Hayilena Gulbete" Legesse Djilo - Volume 1, 1985 E.C የለገሠ ጂሎ የቀድሞ እና የአሁን መዝሙሮች ለማግኘት ይሄንን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
ጉታ ክርስቲያናዊ ሚኒስትሪ
ሁለንተናዊ (መንፈሳዊና ማህበራዊ) አገልግሎት በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን ማገዝና በአካባቢው ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተሐድሶ እንዲመጣ የሚሠራ ሃይማኖታዊ ድርጅት ነው።
ዓላማውም:- የክርስቶስን አርአያ የተከተለ ደቀ መዝሙርነት፣ የሥነ-መለኮት፣ የለውጥ አመራር እና የማህበረሰብ ልማት ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት አገልጋዮችን ማብቃትና አስመርቆ ማሰማራት ነው።
17/06/2020
የዘማሪ ለገሠ ጂሎ ቆየት ያለ ሲዳሚኛ መዝሙር
“በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፣ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ” (መዝ. 104፡33)
legesse djillo - ሱ’ሚያ ኡላቴ አ’ኒ የዘማሪ ለገሠ ጂሎን ቆየት ያሉና አዳዲስ የሲዳሚኛና የአማሪኛ መዝሙሮችን በዚህ ዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ያገኛሉ፡፡
05/01/2019
“በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ እግዚአብሔር ልጆች ናቸውና”
ታላቅ የጸሎት ጥሪ!
የእግዚአብሔር መንፈስ ሁላችንም በያለንበት ነእንዲህ እንድንጸልይ ያሳስበኛል፡-
ዛሬ በዓም ሁሉ እየሠራ ያለው የዓመፅ ምስጢር ወይም የ“ምስጢር ማህበርና የኢሚናቲዎች” አሠራር በአገራችን በኢትዮጵያ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ያነጣጠረው ዒላማ እንዳይሳካ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ ይህ አሠራር በአገራችን በኢትዮጵያ ከአፀዎቹ ዘመን ጀምሮ እስከ ህወሓት መራሽ ኢህአዴግ መንግስት ድረስ በምስጢር ሲሠራ የቆየና አሁን ግን በእግዚአብሔር ኃይልና በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን እየፈረሰ ያለ ስለሆነ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ ባለና በሌለ ኃይሉ ተግቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ከእኛ ጋር ያለው ከእነርሱ ጋር ካለው በብዙ እጥፍ ስለሚበልጥና ምሽግን ለመስበር ብርቱ በሆነ መሣሪያችን በጸሎት ሥራቸውን እናፍርስ፡፡ “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” (2ቆሮ. 10፡3-6፣ ሮሜ 8፡37)፡፡
ባሁኑ ጊዜ አገሪቱን እንደተምችና ደጎቢያ እየበላና እየጎጠጎጠ ያለው የሐሰተኛ መንፈስና ነቢያት ሥራ እንዲፈርስ እንጸልይ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር አስከፊ ጭቆና በፀናቸው ክንዱና በተዘረጋቸው እጁ ለማውጣት ሙሴንና አሮንን በላከ ጊዜ በእጃቸው ባለችው በትር ተአምራት ሲሠሩ የግብፅ አስማተኞች ደግሞ በበትራቸው ያን ለማድረግ ሲሞከሩ እንደነበረ ሁሉ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ በሕዝባችን ላይ ለዘመናት ተጭኖበት የነበረውን የግፍና የመከራን ቀንበር በመስበርና ከድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደ ዕድገት ከፍታ ሊያወጣ እግዚአብሔር በተነሳበት ጊዜ በአንጻሩ በሰይጣን መንፈስ የተሞሉና ጣጠቁ ሐሰተኛ ነቢያት ይህን ደሀውንና ጭቁኑን ሕዝብ ዘርፈው እነርሱ እየበለጸጉ ሕዝቡ ግን ከሁለንተናዊ ሕይወት ጉስቁልና እንዳይወጣ እያደረጉት ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ክፉ አሠራር ለማፍረስ በጸሎትና በቃሉ ዕውቀት እንደሙሴ፣ እንደኤልያስና ኤልሳዕ በነፍሳችንም ቢሆን ተወራርደን ሕዝባችንንና አገራችንን ለመናጠቅበት የምንጋደልበት ጊዜ በመሆኑ አሁን እንነሳ፡፡ (ዘጸ. 8፡16-19፣ 1ነገ. 18፡36-40፣ 2ነገ. 2፡14)
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ የ”ዓመፅ ምስጢር” እና የ”ሐሰተኛ ነቢያት” አሠራር በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር እና የሕዝቡ ጠላት የሆነው የሰይጣን ዲያብሎስ ዋና መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የክፋት አሠራሮች የእግዚአብሔር ሕዝብ በቅድስ ሕይወት በመኖርና በቃሉ አውነት ላይ ተመሥርቶ በሚጸልይበት ጊዜ በክፉ ኃይላት ላይ ድልን ሲቀዳጅና ነፃ ሲወጣ ኖሯል፡፡
ስለሆነም አሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በእምነት ሆነን እንዲህ እንጸልይ፡-
አሁን በዚህ ጊዜ በዓለም ሁሉ ላይ እየሠራ ያለውን የዓመፅ ምስጢር ወይም የምስጢር ማህበርና የኢሉሚናቲዎች አሠራር በአገራችን መንግስት መሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንዳይኖራችሁ ሥራችሁን እናፈርሳለን፣ በጌታ በኢሱስ ስም ሥራችሁን እንቃወማለን፣ በጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ በአቶ ለማ መገርሳ፣ በአቶ ደመቀ መኮንን፣ በዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በሌሎችም የመንግስት ባለሥልጣናት ላይ ምንም እንዳትሠሩ በኢየሱስ ስም ሥራችሁን አፈረስን!!!
አሁን በዚህ ጊዜ በአገራችን በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየሠራ ያለውን የሐሰት አሠራርና የሐሠተኛ ነቢያት እንቅስቃሴና ክፉ ለልምምድ፣ የገንዘብ ዘረፋ፣ የርኩሰት ሥራ፣ ቃሉን የሚያጣምም፣ መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን የክፉ መንፈስ አሠራር በጌታ ኢየሱስ ስም የታሰረ ይሁን፤ ሥራችሁን እናፈርሳለን፣ የፈረሰ ይሁን!!!
ባሁኑ ጊዜ በአገራችን በኢትየዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ እያደረገ ያለውን መንፈስ፣ የኦነግ ጦር ሠራዊት እንቅስቃሴ፣ የወደቀው የቀድሞ መንግስት ስግብግብ ባለሥልጣናት የዝርፊያና ሕዝብን የሚከፋፍል መንፈስ የተገታና የቆመ ይሁን፤ የእስራአል አምላክ በኤርትራ ባሕር ውስጥ የፈርዖንን ሠራዊት ሰረገላና መንኮራኩ እንዳሰረ (ዘጸ. 14፡24) የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች እግር በጌታ በኢየሱስ ስም የታሰረ ይሁን!!!
በአጠቃለይ በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ጥልቅ ድህነት፣ ሁለንተናዊ (መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ) ችግሮች፣ የአየር መዛባት፣ የሕዝባችንን ተስፋ የሚያጨልም መንፈስ የሚያመጣው ማንኛውም ተፅዕኖ እና የክፉ አሠራር በሙሉ በሰማይና በምድር ሥልጣን ባለው በጌታችን በኢየሱስ ስምና ሥልጣን የተሰበረ ይሁን!!! አሜን፣ አሜን፣ አሜን፡፡
19/09/2018
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Awassa
1000