Yes Moge

Yes Moge

Share

Telecommunications

10/04/2019

Jalad'u

04/04/2019

More learn is better

♥ #ሕግ #እና #ፀጋ♥
♥ ♥

✍️For for righteousness to every one that believeth. Romans 10፡4 (KJV)

♥እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን #እጅግ #ገልጠን #እንናገራለን፥2 ቆሮንቶስ 3 ፡12፤♥

✍️በብሉይ/በአሮጌው ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን
✍️በሙሴ እና በክርስቶስ
✍️በሕግ እና በፀጋ
✍️በእንስሶች ደም እና ክቡር በሆነው በኢየሱስ ደም መካከል ያለውን ልዩነት ያልተረዳ እና ጠንቅቆ የማያውቅ ሰው ብዙ እውነቶችን ያበላሻል። 2ጢሞ 2፡15

♦እግዚአብሔር የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁወች አደረገን።
ፊደል /የሙሴ ሕግ ይገድላል መንፈስ/አዲስ ኪዳን ግን ሕይወትን ይሰጣል። 2ቆሮ 3፡6

✍️ሕግ በሙሴ ዘመን ለእስራኤል ህዝብ የተሰጠ። ዮሐ 1፡17,ሮሜ 9፡4
❤️ፀጋ በክርስቶስ ከዘላለም ዘመናት በፊት የተሰጠ። 2ጢሞ 1፡9-11

✍️ሕግ የሞት አገልግሎት ነው።
❤️ፀጋ የሕይወት አገልግሎት ነው። 2 ቆሮ 3፡7

✍️በሙሴ በኩል የተፈጸሙ ታምራቶች መካከል ውሀን ወደ ደም መቀየር ሲሆን ይህም የሞት አገልግሎትን ሲወክል
❤️ጌታ ኢየሱስ ግን የመጀመርያ ተዐምራቱን ያደረገው ሰርግ ቤት ነው ውሃን ወደ ወይን በመቀየር ሰማያዊና በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ እና ሕይወትን አስጀመረ። ዩሐ 2 ,ዘፀ 7፡14-22

✍️የሕጉ አገልግሎት በመጣበት ጊዜ 3000 ሺ ሰወች ሲሞቱ። ዘፀ 32፡28
❤️የሕይወት አገልግሎት ፀጋ ግን በባለ ሀምሳ ቀን ለ3000ሺ ሰወች ሕይወትን ሰቷል። ሐሥ 2፡1-

✍️ሕግ የኩነኔ አገልግሎት ሲሆን
❤️ፀጋ የፅድቅ አገልግሎት ነው። 2 ቆሮ 3፡9

✍️ሕግ በክብር የነበረ
❤️ፀጋ እጅግ በሚበልጥ ክብር የሆነ። 2 ቆሮ 3፡10

✍️ሕግ እስራኤላውያን እና አባቶቻቸው ሊሸከሙት ያልቻሉት ቀንበር ነው። ሐሥ 15፡10
❤️ፀጋ ቀሊል እና የሚያሳርፍ ቀንበር ነው።
ማቴ 11፡28-30

✍️ሕግን መስበክ እግዚአብሔርን መፈታተን ነው
❤️ፀጋ መስበክ ግን ለእግዚአብሔር መታዘዝ ነው።
ሐሥ 15፡19

✍️ሕግ ልብን የሚያውክ እና የሚያናውጥ አገልግሎት
❤️ፀጋ ከእግዚአብሔር ሰላምን ይሰጣል። ሐሥ 15፡24, ሮሜ 5፡1-

✍️ሕግ የሀጢአት እና የሞት ህግ
❤️ፀጋ የሕይወት መንፈስ ህግ(መመሪያ)።
ሮሜ 8፡1-2

✍️ሕግ በክርስቶስ ፍፃሜ ያገኝ እና በአማኝ ላይ የተሻረ
❤️ፀጋ ለዘላለም ፀንቶ የሚኖር ። 2ቆሮ 3፡11

ሕግ ከሰወች ፅድቅን ይጠይቃል
ፀጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፅድቅ። ሮሜ 10፡3-

✍️ሕግ ትእዛዝ ይሰጣል ነገር ግን ለሃጢያተኛው ሰው አቅም አይሰጥም።
❤️ፀጋ ሲሰበክ ግን ቅዱሳን አቅም ያገኛሉ።

✍️ሕግ አድርግ እና አታድርግ ሲል
❤️ፀጋ ግን ተደርጎልሀል በማለት የምስራች ይናገራል።

✍️ሕግ ራስህን እንድታይ ሲያደርግህ
❤️ፀጋ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን ያሳያል። ገላ 3፡1- ,4፡19

✍️ሕግ ባሪያይቱ አጋር ልጆችንም ለባርነት የሚወልድ
❤️ፀጋ ነፃይቱ ሳራ የሚወረሱ ጨዋ ልጆችን የምትወልድ። ገላ 4፡21-31

✍️ሕግ ወንጌልን ለሚቃወሙ ሰወች የተሰራ
❤️ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑት የሆነ።
1ጢሞ1፡8-11, ሮሜ 3፡24

✍️ሕግ ሰወን በማፅደቅ ደረጃ የምትደክም እና የማትጠቅም
❤️ፀጋ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚሻል ተስፍ።
ዕብ 7፡18-19

✍️ሕግ አሮጌ እና ውራጅ
❤️ፀጋ አዲስ። ዕብ 8፡6-13

✍️ሕግ ሃጢያትን ያስታውሳል
❤️ፀጋ የዘለዓለም ፍፁም ያደርጋል። ዕብ 10

✍️የሙሴ ሕግ ሲሰበክ ሃጢአት አቅም ያገኛል ሰውም የሀጢአት ተገዥ ይሆናል። 1ቆሮ 15፡56, ሮሜ 6፡14
❤️ፀጋ ሲሰበክ ግን ቅዱሳን ሀይል በማግኝት ሀጥያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን በመካድ በፅድቅ እና በቅድስና ነፃነታቸውን ይለማመዱታል ( ቲቶ 2፡11-13, 1ቆሮ 15፡56 )

✍️ሕግንና ኩነኔን አብዝቶ መስበክ ሞትን እንደመስበክ ነው፡፡
❤️ፀጋ ሲሰበክ ግን ሕይወት ይበዛል ።

የጽድቅ አገልግሎት ማለት የተገለጠውን እና የእግዚአብሔር ፀጋ የሆነውን ክርስቶስን አብዝቶ መስበክ ማለት ነው፡፡

2 ጴጥሮስ 3 ፡ 18 ...በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ
Gospel Truth Ministry Jimma

03/04/2019

Nothing is made if you go with Jesus christ.

Want your business to be the top-listed Shop in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Awassa