Gecho_ICT
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gecho_ICT, Computer Company, 14, Bahir Dar.
09/01/2023
#ብሉቱዝ ( )
ብሉቱዝ በአጭር ርቀት ውስጥ ምንም አይነት ገመድ ሳይጠቀም ዝቅተኛ ፓወር ራዲዮ ቴክኖሎጂ በመጠቀም #ስልኮች፤ #ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ኔትወርክ ዲቫይሶች እንዲገናኙ( ኮሚኒኬሽን እንዲያደርጉ) ያስችላል፡፡ ብሉቱዝ ስታንደርድ 802.15.1 ሲሆን ስሙን የወሰደው 1000 ዓመት በፊት ከነበረ Bluetooth ከተባለ #ዴንማርክ ንጉስ ነው፡፡
#ብሉቱዝ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲዛይን የተደረገው ቀላል ዋየርለስ ኔትወርክ ዲቫይሶችን፤ ስልኮችን እና ዋየርለስ ሄድሴት ሰፖርት ለማድረግ ሲሆን ዋየርለስ ሲግናል ትራንስሚትድ (የሚተላለፈው) በብሉቱዝ በአጭር ርቀት 10 ሜትር ውስጥ ነው እንዲሁም ብሉቱዝ ዲቫይሶች በአጠቃላይ ግንኙነት የሚያደርጉት ያነሰ ነው፡፡
#የብሉቱዝ ኔትወርክ #ፒኮኔት ( ) ወይም ፐርሰናል ኤርያ ኔትወርክ ( ) ሲሆን ፒኮኔት ቢያንስ ቢያንስ 2 እና ከ8 ያልበለጡ ብሉቱዝ ዲቫይሶች የተገናኙበት የብሉቱዝ ኔትወርክ አይነት ነው፡፡ ዲቫይሶች ግንኙነት ሲያደርጉ ፕሮቶኮል ይጠቀማሉ። ብሉቱዝ የተለያዩ ቨርዥን ሲኖሩት እነሱም 1.1, 1.2 እና 2.0 ናቸው፡፡
#ብሉቱዝ በተለያዩ ዲቫይሶች ላይ የምናገኘው ሲሆን ለምሳሌ፡- #በኮምፒውተር፤ #በስልክ፤ #በጌም መጫወቻዎች፤ #ሄድሴት፤ ወዘተ
ብሉቱዝ ዲቫይሶች ለማገናኘት ምንም አይነት ኢንስታሌሽን ወይም ኮንፊገሬሽን (ኔትወርክ ዝርጋታ) አያስፈልግም በቀላሉ ዲቫይሱን ብሉቱዝ ኢኔብል (መክፈት) ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡
👇
https://t.me/gechoICT
09/10/2022
🆙 Telegram Hack እንዳይደረግብን ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነጥቦችን እነሆ ከዚህ በታች አስቀምጬላችኋለው:-
➡️ ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
👉 Telegram እንደ Viber, Whatsapp,imo በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል
👉 ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ .... ነው
👉 በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
👉 Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።
ማሳሰቢያ: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።
👉 ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።
✅ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***** ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።
✅ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።
✅ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
👉 ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
👉 ማንም ሰው ለመግባት በ E-Mail የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።
👉 የሰጠነውን Password እንዳይጠፋን በጥንቃቄ መያዝ ይጠበቅብናል።
https://t.me/gechoICT
05/08/2022
👉 ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
👉ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።
1⃣ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
2⃣ ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
3⃣ ቀጥሎም Device Manager
4⃣ ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
5⃣ ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
6⃣ ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ👍👍👍
🔴 ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!
👍አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።
ወደ ቴሌግራም ይግቡ!
https://t.me/gechoICT
03/08/2022
Firewall ምንድን ነው?
ጥቅሙስ?
ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ
ባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለመበከል ነው።
ማንኛውም የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለቫይረስ ኢላማ ነው። የኮምፕዩተር ቫይረስ በግለሰብ፣ በድርጂቶች፣ በመንግስቶች፣ በነጋዴወች ወዘተ ይሰራል።
የሌላውን አበላሽተው ለመደሰትም ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ። የዚህንም ያህል የታመሙ ሰወች አሉ። ሁሉም የየራሱ አላማ አለው። የኮምፕዩተር ቫይረስ ውስብስብ ግን መጠኑ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጻር በጣም ትንሽ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ክብደቱና ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ግን አደገኛ ነው።
አንቲ ቫይረስ፤ አንቲ ቫይረስ የተሰራው የኮምፕዩተር ቫይረስን ለመከላከል ነው። አሁን ከቅርብ አመታት ወዲህ እራሱ ዊንዶውስ አንቲ ቫይረስ(Windows Defender) በነጻ ለተጠቃሚው ይሰጣል። ሆኖም ግን ሌሎችም የሚሸጡ ነጋዴወች አሉ። ተጠቃሚው እራሱ የትኛውን አንቲ ቫይረስ መግዛት እንደሚፈልግ ይወስናል ማለት ነው። እንደጥራቱ ይለያያል።
የነጻ አንቲ ቫይረሶችም አሉ። በሰፊውና ባይነቱ ለመከላከል ግን የሚገዛው ይሻላል። ለማንኛውም ዊንዶውስ በየጊዜው ስለሚጠቃ አንቲ ቫይረስም ቢሆን ሁሉንም ጥቃት አይከላከልም። አንቲቫይረስ እየሰሩ የሚሸጡ ነጋዴወችም እራሳቸው ቫይረስ ይሰራሉ እየተባለ ይታማሉ።
ፋየርዎል ያልተፈቀደ የኮምፒዩተር ኔትወርክን በመጠቀም ከኮምፒውተር የሚገባንና የሚወጣን ያልተፈቀደ ግንኙነትን ለመከላከል የተነደፈ የደህንነት ስርዓት ነው።
ፋየርዎል ከኮምፒዩተር በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባውን እና የሚወጣውን የኔትወርክ ትራፊክ ይቆጣጠራል።
ፋየርወል በእንግሊዘኛው እሳት የሚከላከል ግድግዳ እንደማለት ነው። ፋየርወል ከውጭ ወደ ኮምፒውተራችን በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባን ቫይረስ መሰል የመረጃ በካይ፣ አጥፊ፣ ሰራቂ፣ ሰላይ ፕሮግራሞች እንዳይገቡ በመጠኑም ቢሆን የሚከላከል ሲሆን በጣም ጠቃሚና ለመረጃ ደህንነት አስፈላጊ የኮምፒውተር ማስተካከያ ነው።
ስለዚህ ኮምፒውተታችንን ከኢንተርኔት ጋር የምናገናኝ ከሆነ የኮምፒውተራችንን Firewall on ማድረግ ይጠበቅብናል ማለት ነው። ስለዚህ ለኮምፕዩተርም መከላከያ የሚሆን ፋየርወል አለ።
ለምሳሌ፣ የእርስዎ የግል ኮምፒውተር ፋየርዎል ከሌለው ወይም ፋየርውሉ ዝግ(Off) ከሆነ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ሰርጎ ገቦች(ሀከር) ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ።
ሁለት አይነት ፋየርወሎች አሉ። አንደኛው ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ጋር አብሮ እዛው ተጠቃሚው ያገኘዋል። (መጨረሻ ላይ ያለውን Step ይከተሉ) ለምሳሌ የዊንዶውስ ኮንትሮል ፓነል ላይ ሄዶ ፋየርወሉን እንደ አስፈላጊነቱ (ከፍተኛ ወይም መካከለኛ) መጠን ላይ መርጦ መቀስቀስ ይቻላል። የሚገዙ አንቲቫይረስ ፕሮግራሞችም የራሳቸው ፋየርወል አላቸው። ሌሎችም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ፋየርወል አላቸው።
የኮምፒውተታችንን ፈየርወል ለማስተካከል ቅደም ተከተል Windows 10, 8, 7: ላይ Control Panel > System and Security > Windows Firewall > Turn Windows Firewall on or off
✅ the bubble next to Turn off Windows Firewall (not recommended) and then select OK.
✅To disable the firewall for private and public networks, select Turn off Windows Firewall (not recommended) in both sections.
Gecho_ICT
https://t.me/gechoICT
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Contact the business
Telephone
Website
Address
14
Bahir Dar