Bonga Town Communications
Here we provide updated governmental and public news and information to any concerned body.
01/06/2026
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሕይወት አሰግድ በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ድምፅ ሰጡ።
ምርጫው እስካሁን ከነበሩት የምርጫ ሂደቶች በተሻለ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ምርጫ ሴቶች በነቂስ ወጥተው ይበጀናል የሚሉትን ለመምረጥ የተዘጋጁበት ሁነት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
መራጩ ህዝብ በጊዜ ወጥቶ በመምረጥ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
01/06/2026
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው አበበ ድምፃቸውን ለመስጠት በምርጫ ጣቢያ ተገኝተዋል።
አቶ ፍሬው አበበ በማለዳው በምርጫ ጣቢያው የተገኙ ሲሆን፥ እንደማንኛውም ዜጋ ሰልፍ በመያዝ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ተራቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ።
በቦንጋ ከተማ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ጠዋት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ድምፅ ለመስጠት በነቂስ ወጥቶ በሰላማዊ ሁኔታ ሰልፍ ይዞ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የከተማው አስተዳደር የምርጫው ሂደት በሰላም፣ በዲሞክራሲያዊና በነፃነት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ መደረጉንና ሂደቱም በሰላም እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
ቦንጋ ከተማን በጋራ እናልማ ❗️
✍ተጨማሪ መረጃዎቸን ✍
በቴሌግራም 👉 t.me/BongatownGCAO
በፌስቡክ 👉 https://www.facebook.com/BTGCA
በቲውተር 👉 https://twitter.com/BongaTown?t=1Hfq-1TmjDHkrNlWUiPA7g&s=09 ተወዳጅተው ይከታተሉን፡፡
🙏ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bonga Town
Bonga