Addis Page
20/03/2026
: እስራኤል በኢየሩሳሌም የዒድ በዓልን በሚያከብሩ ፍልስጤማውያን ስገድተኞች ላይ ጋዝ ቦምቦችን (Gas bombs) መተኮሷ ተሰማ !
ምንጭ፦ ብሪክስ ኒውስ (BRICS News)
19/03/2026
ሰበር: ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በሚያልፉ መርከቦች ላይ አዲስ ታክስ ለመጣል እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ተስማ::
ቴህራን — የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ምክር ቤት (መጅሊስ) በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል በሚያልፉ የንግድና የነዳጅ መርከቦች ላይ የአገልግሎት ክፍያና ታክስ ለመጣል የሚያስችል አዲስ የሕግ ረቂቅ እያዘጋጀ መሆኑ ተሰማ።
የቴህራን ተወካይ የሆኑት ሶማያህ ራፌ ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ወሽመጡ ለዓለም አቀፍ የንግድ ፍሰት፣ ለነዳጅና ለምግብ ምርቶች መተላለፊያነት ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ኢራን ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለች ነው።
በመሆኑም አገሪቱ ከዚህ ስትራቴጂካዊ መስመር ተገቢውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታገኝ የሚያስገድድ ሕግ በፓርላማ አባላት ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።
እንደ ኢስና (ISNA) የዜና ወኪል ዘገባ፣ የፓርላማ አባሏ ኢራን በወሽመጡ ላይ ያላትን የሉዓላዊነት ስልጣን በዝርዝር አብራርተዋል። “እስካሁን ጠላቶቻችን ያለ ምንም ጋሬጣ ሲጠቀሙበት የነበረውን ምቾት ነጥቀናቸዋል” ያሉት ተወካይዋ፣ ይህ አዲስ አቅጣጫ ለተቃዋሚ ኃይሎች በቀላሉ የሚዋጥ እንደማይሆንም ጠቁመዋል።
ሶማያህ ራፌ አክለውም፣ ወቅታዊው ቀውስ በኢራን ወሳኝ ድል እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ ከድሉ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፍ ለኢራን ባላንጣዎች ብርቱ ፈተና እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።
ይህ የኢራን እርምጃ በቀጣናው ባለው የንግድ ልውውጥና
በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።
Via BBC
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Debre Birehan
Debre Birhan