Addis Belete Fan
about ddis belete daily information
20/02/2021
"ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ"?
ሸዋረገድ ገድሌ የጀግንነት ተምሳሌት በ1935 የኢጣሊያን ወረራ ጊዜ መረጃ ስንቅ በማቀበል ተርፎም መሳሪያ በመያዝ ጠላትን በመጣበት በመመለስ ጀግንነትን ያሳየች ሴት ዕንቁአችን ናት።
በ1935 ጦርነት ጊዜ ወደ ጅማ ሂዳ ከገረ ሱዱኪ ጦር ጋር ተቀላቅላ ተዋግታለች ታላቆ አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ ያን ጊዜ በነበረው ውጊያ ጣሊያኖች ማረኮት በጣሊያኑ ፊት ስትቀርብ በንቀት ነበር ያያት ምክንያቱም ሴት መሆኖና አርበኛ መሆኖን ስላልተቀበለ ጣሊያኑ "ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ?" አላት እንግዲህ ልብ በሉ የጣሊያን ጦር አሸንፎል የእሶ ጦር ከሆላ ተሸንፎል።
ምን ብትል ነፃ ትወጣለች? ምንም አያስቸግርም "አስገዲደውኝ ነው።" ማለት ትችል ነበር።
ኢትዮጲያዊነት ሚስጥሩ ስለገባት "የአንበሶች መኖሪያ ጫካ ውስጥ ስለሆነ" አለቻቸው አያችሁ አርበኞቻችን ስለሀገራቸው ተሰውተው ነው ያቆሞት እነ ባልቻ ሳፎ አጨብጫቢ ሸላሚ በሌለበት ብቻውን ሂዶ የጣሊያንን የጦር መሪውንና ጠባቂዎቹን እረሽኖ የተሰዋ አርበኛ ያሉበት ሀገር ነው ያለነው።
እምየ ሚኒልክ የጊወርጊስን ታቦት አውጥተው በማሪያም ምለው ህዝቡን ቀስቅሰው አድዋ ላይ የነፃነታችንን በር የከፈትንበት ጊዜ ነው።
ኢትዮጲያየ3000 ዓመት ታሪክ ያላት እያልን አንሸወድ የ6000 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ምንጭ መራራ እውነት ከሚለው መፅሀፍ ነው ያገኘሁት ኢትዮጲያ "ታሳልፋለች እንጅ አታልፍም"
ስለ አድዋ በእንግሊዘኛ ከተፃፈው መፅሀፍ ለአድዋ ድል ምክንያቱ አዋሉም የሚባል ለጣሊያኖች የተሳሳተ መረጃ የሚሰጥ ሰው ነው ይላል ግን ፍፁም ስህተት ነው። በጀግና ልጆቾ ነፃነት አግኝተናል። የመለኮታዊ ሀይል(spiritual power) እንዳለ ሁኖ የአርበኞቻችን ክብር መጠበቅ የእኛ ሀላፊነት ነው።
"ክብር ለአርበኞቻችን"
13/06/2013
ወገልጤና
አድስ በለጠ
19/06/2020
ማዕዶት ዘ ኦርቶዶክስ:
ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
ሚካኤል
--------
በዕብራይስጥ: מִיכָאֵל, ሲነበብ፡ ሚካኤል
በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl;
በላቲን: Michahel-ሲነበብ ሚካኤል;
በአረቢኛ: ميخائيل, ሲነበብ፡ ሚካኤል
በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላእክት ተብሎ ይጠራል::
ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ’ ካ-ከመ’ ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡
ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡
•በዛሬውም ዕለት ሰኔ ፲፪ የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት ዕለት በመሆኑ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት ይከበራል::
በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ተመልከቱ:-
•መላእክት ሰውን ይረዳሉ -ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/
•ለመላእክት ስግደት ይገባቸዋል- ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15
•ዛሬ በተጨማሪም የጻድቁ የቅዱስ ላሊበላ በዓለ ዕረፍት ሲሆን ቅድስት አፎምያም በዛሬው ዕለት ትታወሳለች::
ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
20/01/2020
መልካም የጥምቀት በዓል
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Dessie
1234