DrGetachew

DrGetachew

Share

Personal blog

21/05/2026

💪አርሰናል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የታሪክ ሪኮርድ ሰባበረ!

❤​መድፈኞቹ የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቃቸውን በታላቅ ድል ካበቁ ማግስት፣ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛውን የገቢ መጠን በመሰብሰብ አዲስ የፋይናንስ ታሪክ አስመዝግበዋል።

❤!ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን 760 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ በሃንጋሪ ቡዳፔስት ከፓሪስ ሳንዠርሜን ጋር በሚያደርገው የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ድል የሚቀናው ከሆነ አጠቃላይ ገቢው ወደ 770 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍ ይላል።

​ይህ አስገራሚ አሃዝ ማንቸስተር ሲቲ ቀደም ሲል አስመዝግቦት የነበረውን የ715 ሚሊዮን ፓውንድ የፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ የገቢ ሪኮርድ በይፋ የሰበረ ነው። ዘ ታይምስ ጋዜጣ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ አርሰናል ይህንን ግዙፍ የፋይናንስ አቅም ሊገነባ የቻለው ከከፍተኛ የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ሽያጭ፣ ከስታዲየም መግቢያ ትኬት እና ከዋና ዋና ስፖንሰሮቹ እንደ ኤሚሬትስ እና አዲዳስ ከሚያገኛቸው የፋይናንስ ቦነሶች የተነሳ ነው።

The gunners

12/05/2026

📶ለአመራር ስኬት የሚረዱ አጫጭር ምክሮች
===================
የአመራር ስኬት የሚለካው በሥልጣን ሳይሆን ሰዎችን በማነቃቃትና የጋራ ራዕይን ወደ ተግባር በመለወጥ ነው። ውጤታማና ስኬታማ መሪ ለመሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ብቃቶች ማዳበር ወሳኝ ነው፦
​1. ግልጽ ራዕይና ግብ (Vision and Goal)
​ስኬታማ መሪ ነገሮች ዛሬ ባሉበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ አስቀድሞ የማየት ችሎታ አለው።
​መንገድ አሳቢነት፦ ተከታዮቹ የት መድረስ እንዳለባቸው በግልጽ እንዲረዱ ያደርጋል።
​ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ፦ ትልቁን ምስል በማየት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ያዘጋጃል።
​2. ውጤታማ ተግባቦት (Effective Communication)
​መሪነት በንግግር ብቻ ሳይሆን በማዳመጥም ጭምር የሚገለጽ ጥበብ ነው።
​ንቁ አድማጭነት፦ የቡድኑን አባላት ስሜትና ሃሳብ በትዕግስት ማዳመጥ።
​ግልጽነት፦ መመሪያዎችንና መረጃዎችን ሳይደበቁና ግልጽ በሆነ መንገድ ማስተላለፍ።
​3. ተዓማኒነትና ታማኝነት (Integrity and Ethics)
​ሰዎች መሪን የሚከተሉት ሲያምኑት ብቻ ነው። ለቃሉ የሚታመንና በሥነ-ምግባር የታነጸ መሪ በቡድኑ ውስጥ ጥንካሬን ይፈጥራል።
​አርአያነት፦ መሪው ሌሎች እንዲያደርጉት የሚፈልገውን ነገር አስቀድሞ ራሱ በተግባር ያሳያል።
​ፍትሃዊነት፦ ለሰዎች አድሎ ሳያደርጉ በእኩልነትና በምክንያት መምራት።
​4. ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)
​የራስን ስሜት መቆጣጠርና የሌሎችን ስሜት መረዳት ለአመራር ስኬት ወሳኝ ነው።
​ትዕግስት፦ በውጥረትና በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይደናገጡ መረጋጋት።
​ርህራሄ (Empathy)፦ የቡድን አባላትን ችግር እንደ ራስ ማየትና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ።
​5. ውሳኔ ሰጪነት (Decisiveness)
​መሪ መሆን ማለት አስቸጋሪ ውሳኔዎችን በወቅቱ መወሰን መቻል ማለት ነው።
​ድፍረት፦ አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ ግን አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን ለመወሰን አለመፍራት።
​ኃላፊነት መውሰድ፦ ለውሳኔዎቹ ውጤት (ለስኬቱም ሆነ ለውድቀቱ) ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ።
​6. ቡድንን ማብቃት (Empowerment)
​ብልህ መሪ ሁሉንም ሥራ ራሱ አይሰራም፤ ይልቁንም ሰዎችን በማሰልጠንና ስልጣን በመጋራት ውጤት ያመጣል።
​ማበረታታት፦ የሰዎችን ጥንካሬ በመለየትና በማድነቅ ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር ማድረግ።
​ተተኪ ማፍራት፦ ከራሱ የተሻሉ መሪዎች እንዲወጡ ምቹ ሁኔታን መፍጠር።
​ለአመራር ስኬት የሚረዱ አጫጭር ምክሮች
​ሁልጊዜ ተማሪ ይሁኑ፦ መሪነት ዘላቂ የትምህርት ጉዞ በመሆኑ አዳዲስ ነገሮችን ከመማር አይቦዝኑ።
​ትችትን በጸጋ ይቀበሉ፦ ስህተቶችን እንደ መማሪያ ዕድል በመጠቀም እራስዎን ያርሙ።
​በትህትና ይምሩ፦ ትህትና የደካማነት ሳይሆን የጥንካሬና የትልቅነት መገለጫ ነው።

Photos from DrGetachew's post 12/05/2026

#ትራምፕ ኤርትራ ለኢትዮጵያ የባህር በር እንድትሰጥ ,ሀገራቱን ለማስማማት እየጣሩ መሆኑ ተነገረ!!!

@ትራምፕ በኢትዮጵያ በኤርትራ ና በግብፅ ዙሪያምን አዲስ ስምንነት ለመፍጠር የእየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለፀ።የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ ላይ የጀመረው አዲስ የዲፕሎማሲ አካሄድ የቀጠናውን ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ እያነቃነቀው ይገኛል።

@ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ በኤርትራ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት መወሰኗ፣ ዋሽንግተን ለአስመራ ያላትን አመለካከት በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ያሳያል። የትራምፕ ዋነኛ ግብ የቀይ ባህርን ስልታዊ ጠቀሜታ እና የቀጠናውን የአሜሪካ ጥቅም ማስከበር ነው።
በዚህም የአሜሪካና ኤርትራን ግንኙነት ማሻሻል, ከኢትዮጵያ ጋር ከሚደረገው አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው።

@ትራምፕ በአንድ በኩል ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በማደስ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር መፈለጉ አሜሪካ በቀጠናው ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምታደርገው ጥረት አካል ነው። በአጠቃላይ፣ የትራምፕ "ጥቅምን መሰረት ያደረገ ዲፕሎማሲ" በቀድሞ የዲፕሎማሲ መሰናክሎች ሳይገደብ በአፍሪካ ቀንድ ላይ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ እየከፈተ መሆኑን ያሳያል።

👉የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነት
" ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታትና ሁኔታዎችን በማርገብ ረገድ የምትጫወተው ቁልፍ ሚና የሚደነቅ ነው " - የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

@የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን (ዶ/ር) ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት የደህንነት አጋርነት እና የንግድ ዕድሎችን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይና በተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

@የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታትና ሁኔታዎችን በማርገብ ረገድ የምትጫወተውን ቁልፍ ሚና እንዳደነቁ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

@በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በትብብር መስኮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ውይይት ማዕቀፍ (BSD) በዋሽንግተን ዲ.ሲ ተፈርሟል።

@ስምምነቱን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የአሜሪካ የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር አሊሰን ሁከር የፈረሙት ሲሆን፤ ማዕቀፉ በዋናነት ፦
- በኢኮኖሚ ብልጽግና፣
- በንግድና ኢንቨስትመንት፣
- በመከላከያና ደህነት፣
- በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ በትኩረት ለመስራት ያለመ ነው።

@አሜራካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ አየሰራች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማስማማት እየጣረች ትገኛለች።

👉አሜሪካ ከኢትዮጵያ ምንድነው የምትፈልገው ?
አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትፈልገው ዋንኛው ነገር ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ለግብፅ ዋስትና እንድትሰጥ ነው , ይሄ የዋስትና ጥያቄ ግብፅ ለዓመታት ከኢትዮጵያ ስትጠይቀው የነበረና በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያ በማስገደድ አስገዳጅ ስምምነቶችን እንድትፈርም ለማረግ ስትጥር የነበረች ሲሆን ኢትዮጵያ ይሄን የግብፅን ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅሜን ይጎዳል በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ ስታደርግ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Esat tv

Want your business to be the top-listed Business in Gondar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


K18
Gondar