Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harari Regional State Innovation and Technology Agency, Government Organization, Harar.

19/05/2026

መላ: በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያፋጥን ሀገር በቀል የቋንቋ ሞዴል!

19/05/2026

📢 የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል!

ዲጂታል ኢትዮጵያን በሳይበር ደህንነት እና በቴክኖሎጂ እውቀት ለመገንባት ራዕይ ላላቸው ወጣቶች የተዘጋጀው 5ተኛው ዙር የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ የዕጩ ሰልጣኞች ምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል!

ባለፉት ዙሮች በካምፑ አልፈው ዛሬ ላይ የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ስታርት-አፕ የመሰረቱ፣ በድሮን ቴክኖሎጂ፣ በኢምቤድድ ሲስተምስ እና በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ሀገራዊ ችግር ፈቺ ስራዎችን እየሰሩ ያሉ የካምፑ ፍሬዎችን ተመልክተናል።
እርስዎስ የዚህ ጉዞ አካል ለመሆን ምን ይጠብቃሉ?

📅 የምዝገባ ማጠቃለያ ቀን፦ እስከ ግንቦት 17 / 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ!
የቴክኖሎጂ እና የሳይበር ተሰጥኦ ያላቸው፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶች የተራዘመውን እድል ተጠቅማችሁ ፈጥናችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ https://ctc.insa.gov.et/registration
ፈጠራችሁን ወደ ተግባር ቀይራችሁ የሀገራችሁን የሳይበር ሉዓላዊነት የምታስከብሩበት መድረክ ይጠብቃችኋል!


INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

11/05/2026

🚀 የኢመደአ የ2018 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ላለፉት 4 ተከታታይ ዓመታት በሳይበር ደህንነትና ተዛማጅ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በመለየትና በማሰልጠን ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ፣ ወደ ተቋሙ እንዲገቡ እንዲሁም የራሳቸውን ስታርታፕ እንዲጀምሩ አስችሏል።

በ2018 ዓ.ም ደግሞ ከቀደሙት ዓመታት በተሻለ አቅምና ዝግጅት 5ኛውን ዙር የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል። ፕሮግራሙ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ድረስ ያሉ ልዩ ተሰጥኦና ፍላጎት ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች ያካትታል።
📌 ምዝገባው ከሚያዚያ 29/2018 እስከ ግንቦት 10/2018 ዓ/ም ድረስ ይቆያል!
📌 ለመመዝገብ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ያስፈልጋል!

💡 በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ልዩ ፍላጎትና ተሰጥኦ ካላችሁ፦

🔹 ሳይበር ደህንነት

🔹 ዴቨሎፕመንት

🔹 ኢምቤድድ ሲስተም

🔹 ኤሮስፔስ

🔹 ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ

የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ በሚከተሉት ዩኒቨርሲቲዎች ይካሄዳል

1. አዲስ አበባ ሳይንሳን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

3. ጅማ ዩኒቨርሲቲ

4. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

5. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

ይህ እድል ለእናንተ ነው!
📌 ስለ ፕሮግራሙ ዝርዝር መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን ይመልከቱ፦
https://t.me/insactc
📝 ለመመዝገብ፦
https://ctc.insa.gov.et/registration

Want your organization to be the top-listed Government Service in Harar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Harar