BADE HARAR

BADE HARAR

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BADE HARAR, Nonprofit Organization, Harar.

Photos from BADE HARAR 's post 28/08/2024

ዜና ሹመት

✍️የቀድሞዉ የሀረሪ ክልል የልህቀት ማዕከል የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዝግጅትና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጁኔድ ኑረዲን የሐረሪ ክልል መሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል::

تعيين الأخبار

✍️ تم تعيين السيد جونيد نور الدين، الذي كان مديرًا للإعداد والإعداد لمركز التميز في منطقة هراري، كهيئة تطوير وإدارة الأراضي في منطقة هراري.

Photos from BADE HARAR 's post 29/07/2024

ዛሬ ሃያ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎቻችን የትምህርት ጥራትን አስመልክቶ ባካሄዱት የኦን ላይን ስልጠና መክፈቻ ወቅት የትውልድ ቅብብል የተሳካ የሚሆነው እንደነርሱ ያሉ መምህራን በሚወጡት እጅግ ጠቃሚ ሚና መሆኑን ገልጫለሁ።

Leenjii yunivarsiitiiwwan keenya 28 qulqullina barnootaarratti har'a karaa intarneetii jalqaban irratti carraa ergaa dabaruu argadheen walharkaa fuudhinsi dhalootaa kan milkaa'u shoora olaanaa barsiisonni akka isaanii bahaniin ta'uu ibseera.

29/07/2024

በከተማ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስፋት በትኩረት ይሰራል-አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ሀምሌ 22/2016(ሀከመኮ):- በ2016 በጀት ዓመት በከተማ ልማት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረር ከተማን ዕስትራቴጂክ ዕቅድ ለመምራት ከተዋቀረው ግብረሀይል ጋር በክልሉ ተጀምረው በሂደት ላይ በሚገኙ እና በበጀት ዓመቱ ተግባራዊ በሚደረጉ አዲስ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ መክረዋል።

በምክክሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የማህረሰቡን የረጅም ዓመት የልማት ጥያቄ ለመመለስ በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ በመሰረተ ልማት ፣በከተማ ውበት እና ፅዳት ስራ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

በተለይ በበጀት ዓመቱ በኮሪደር ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እና የማህበረሰቡን ይሁንታ ያገኙ ሆናቸውን ገልፀዋል።

በመሆኑም የተጀመሩ ስራዎቸን በፍጥነት በማጠናቀቀ በቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማስጀመር ትኩረት ተሰቶ ይሰራል ብለዋል።

በከተማ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስፋት ለኑሮ ብሎም ለጎብኚዎች የተመቸች ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አዳዲስ የገበያ ሼዶችን በመገንባት በመንገድ ላይ የሚካሄዱ ስርዓት አልባ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ስርዓት ለማስያዝ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በከተማ ውበት እና ፅዳት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታ የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን ክትትል እና ድጋፍ እደሚደረግም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በትራነስፖርት ዘርፍ በተለይ የመንጃ ፍቃድ ፣ ቦሎ እና ታርጋ ቁጥጥርን በማጠናከር በህገ ወጦች ላይ ጠንከር ያለ አስተማሪ የዕርምት ዕርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተስተዋለውን መነቃቃትም እንዲጎለብት አስፈላጊው የድጋፍ እና ክትትል ስራ እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።

Photos from BADE HARAR 's post 28/07/2024

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኝው 6ኛ ዙር 3ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

የካቢኔ አባላት ሹመት በምክር ቤቱ የጸደቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አቅራቢነት ነው።

በዚህ መሰረትም

1ኛ.አቶ ሙክታር ሳሊህ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

2ኛ.አቶ ጌቱ ነገዎ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

3ኛ.አቶ ኢሊያስ ዮኒስ የሀረር የከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ

4ኛ.ወ/ሮ ዚነት ዩሱፍ- የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

በተጨማሪም በክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ አቅራቢነት

ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ- የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው እንዲያገለግሉ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የክልሉ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድው የቆየው 6ዙር 3ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ አጠናቋል።

Photos from BADE HARAR 's post 27/07/2024

ሑስኒዞቤ ዚትከመላ በጀት አመትቤ 8 አልፋዋ 200ቤ ለአይ ዩኹንዛሉ መደኒያችሌ ዋሪ ዲላጋ ነሲብ ተኸለቃ- ሐረሪ ሑስኒ ረኢስ ጌስሲ ኦርዲን በድሪ

ሐረሪ ሑስኒቤ ዚትከመላ በጀት አመትቤ 8 አልፋዋ 200ቤ ለአይ ዩኹንዛሉ መደኒያችሌ ዋሪ ዲላጋ ነሲብ መኽለቅ መፍረክዞው ሑስኒዞ ረኢስ ጌስሲ ኦርዲን በድሪ ገለጡ።

ሐረሪ ሑስኒ ሒርጊ ጋር 6ታኝ ዶር 3ታኝ አመት 6ታኝ ኡርፊ ሶሰምዞው የሚሕሪቤዛል ዚኻነሳ መጅሊስዞቤም ሑስኒዞቤ ዚትከመላ በጀት አመትቤ ዚትሜሐሩ ሊሚ ሊሚ ኢሾታቹ ዪነክዛልቤ ረኢስ ጌስሲ ኦርዲን በድሪ ሒርጊ ጋርዞሌ ሒካሞት አቀረቡ።

ረኢስዞ ዘቀረቦ ሒካሞትቤም 2016 በጀት አመትቤ ሑስኒዞቤ ኣሲማዋ ደርጋቤ ዪትረኸብዛሉ 9 አልፋዋ 760 መደኒያችሌ ዲላጋ ነሲብ መኽለቅሌ ተቦረአማ 8 አልፋዋ 286 ዩኹንዛሉ መደኒያችቹ ዋሪ ዲላጋ ነሲብ ተናፋኢ ሞሻ ተፈረካ።

ዚትኸለቃ ዲላጋ ነሲብ ማቤይነቤም 4 አልፋዋ 938 ኣሲማቤ አዝዞኩትዞም 3 አልፋዋ 348 ደርጋ ሺርቲቤ መኽነዞው አቀነኡ።

ዴይኒ መርገገብ በሕ ዚትላሐደቤም ሑሉፍ ዛያ ዋ ኡርፊ ዴይኒ 67 ኑቅጣ 6 ሚሊየን ብር መርገገብ መትፍረክዞው አቀነኡማ 15 ኑቅጣ 7 ሚሊየን ብር 483 ኢንተርፕራይዛችሌ ዴይኒ መትሲራጫ ዲላጋ ተሜሐራ ባዩ።

መጋላ ቂማ ዲባያው መርገዝ ገረብሌም ሑስኒዞቤ ሺኢሽቲ ደርጋ ወረዳ ሐራሺያች ሰብቲ ዋ አልሐድ መጋላች ለአይቤ ኦሚሻችዚዩው የቀርቡኩት ሞሸቤ ኹድራ ዋ ሙድራ መጋላ ለአይቤ ላቂ ቂማ መርገዝቲ ዲላጋ መትደለግዞው ገለጡ።

ዪቤ ዲባያም ኢስበልበላት ኢንዱስትሪ ዋ ሐራሺነት ኦሚሻች ኪም ሑስኒዞ ዩቡኡኩት ዋ ሰብቲ ዋ አልሐድ መጋለቤ የቀርቡኩት ኻና ባዩ።

አሳሲያ መጣራቹ ተናፋኢ ዳይሐዋዝሌ አቆረሮት ሞሸ ገረብሌም 7 በቅላዋ 76 አልፊ ሊትር ሐንጉር ዜት አዝዞኩትዞም 3 አልፊ ኩንታል ሱከር መትሲራጨዞው ገለጡ።

Photos from BADE HARAR 's post 27/07/2024

#ገቢን በሚመለከት
***********
በክልሉ በ2016 በጀት አመት 4.3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አርዲን በድሪ ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት አመቱ ከ4.3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከክልሉ ውስጥ ገቢ ከ 2 ቢሊዮን 254 ሚሊየን (2,254,391,552 ) ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቁመዋል፡፡

የተሰበሰበው ገቢም ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታከስ፣ ከማዘጋጃቤታዊ ገቢ፣ ከመደመረ ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭ እና ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከቻነናል አንደ ፕሮግራም የተገኘ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የክልሉ የገቢ አፈፃፀምም እድገት እያስመዘገበ የመጣ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኦርዲን የገቢ ማመንጨት አቅምን አሟጦ በመጠቀም የገቢ መሰረትን በማስፋት ረገድ ብዙ ስራ የሚቀር መሆኑንና በቀጣይ በጀት ዓመት ይህንን ከግምት ውስጥ ያስባ ሰራ በትኩረት መሰራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Harar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Harar