Horn Insight
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Horn Insight, News & Media Website, Hawassa.
11/07/2026
ለሲዳማ ቡና ክለብ ሰኞ ዕለት በሀዋሳ የጀግና አቀባበል ሊደረግለት ነው
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ (አሊቶቹ) በ2018 የውድድር ዓመት ላስመዘገበው ታሪካዊ ድል፣ የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የጀግና አቀባበል ሊደረግለት መሆኑን የክለቡ ቦርድ አመራር በመግለጫ አስታወቀ።
የክለቡ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጀጎ አገኘሁ እንደገለጹት፤ ክለቡ በዋናው ፕሪምየር ሊግ እና ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች (U-20) ውድድሮች በአንድ ቀን ሁለት ዋንጫዎችን በማንሳት እንዲሁም በኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ታሪክ ሰርቷል። ይህ ድል በቀጣይ ክለቡ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ለሚያደርገው ጉዞ ትልቅ አቅም እንደሚሆንም ተጠቁሟል።
የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ሰኞ ጠዋት ከ3፡00 ጀምሮ መነሻውን ጥቁር ውሃ አድርጎ በሀዋሳ ጎዳናዎች ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ ማምሻውን የእውቅና እና የምስጋና መርሃ-ግብር ይካሄዳል። የክለቡ አመራሩ ደጋፊዎች በነቂስ ወጥተው ሰላማዊና ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መንገድ አቀባበል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
11/07/2026
የ16 ዓመት ታዳጊን በቡድን አስገድዶ የደፈሩ ሁለት ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ
የቦረዳ ወረዳ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት፣ የ16 ዓመት ታዳጊን በማታለል በቡድን አስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ሁለት ግለሰቦች ላይ የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።
የዐቃቤ ሕግ ክስና የሰነድ ማስረጃ እንደሚያስረዳው፣ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ተበዳይዋ አርሰማ ሽፈራው ከወላይታ ወደ ምዕራብ ዓባያ ዋጅፎ ከተማ ዘመድ ለመጠየቅ በመጣችበት ወቅት፣ ለጊዜው ያልተያዘ ብሩክ ቱሩቆ የተባለ ግለሰብ ከዘመዶችሽ ጋር አገናኝሻለሁ በሚል ማታለያ በሞተር ብስክሌት ወደ ቦረዳ ወረዳ ጎቾ ከተማ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤት ወስዷታል። እዚያም አንደኛ ተከሳሽ መልካሙ አዳኔን በመጥራትና የሞት ዛቻ በመሰንዘር ሌሊቱን ሙሉ ሲደፍሯት አድረዋል።
በማግስቱ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ በሩን በውጭ በመቆለፍ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ልደቱ መሐመድ እና ሌሎች ያልተያዙ ግለሰቦች በመስኮት ገብተው በተመሳሳይ መልኩ ወንጀሉን እንዲፈጽሙ አድርገዋል።
በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ሁለተኛ ተከሳሽ ድርጊቱን በዝርዝር ያመነ ሲሆን፣ አንደኛ ተከሳሽ ግን ክዶ ተከራክሯል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና 620(1)ን መተላለፋቸውን በበቂ ሁኔታ አረጋግጧል።
በዚህም መሠረት ችሎቱ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቅጣት ማክበጃና ማቅለያዎችን በማመዛዘን፣ አንደኛ ተከሳሽ መልካሙ አዳኔ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ልደቱ መሐመድ ደግሞ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።
ግን ቅጣቱን እንደት አያችሁ?
09/07/2026
የዛምቢያዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ከሄሊኮፕተር አደጋ በሰላም ተረፉ
የዛምቢያዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ሙታሌ ናሉማንጎ (Mutale Nalumango) እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በዛምቢያ ከተከሰተ የሄሊኮፕተር አደጋ በሰላም ተርፈዋል። አደጋው የደረሰው የዛምቢያ አየር ኃይል ሄሊኮፕተር በሙቺንጋ ግዛት በምትገኘው ናኮንዴ ከተማ ላይ ለመነሳት ሲሞክር ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው።
አውሮፕላኑ ከመሬት ከተነሳ ጥቂት ቆይታ በኋላ በአስቸኳይ መሬት ላይ እንዲያርፍ የተገደደ ሲሆን፥ በወቅቱ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎችና የበረራ ሰራተኞች በሙሉ ያለምንም ጉዳት ማምለጥ መቻላቸውን የመንግስት ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። ይህ አስደንጋጭ አደጋ ያጋጠመው ሀገሪቱ ለሚቀጥለው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት በተደረገ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ላይ እንደነበር ታውቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa