Zola Mobile Accessory and Computer Maintenance
You can get Brand Mobiles, accessories and Quality Maintenance of any Desktop, laptop and Mobile with fair prices. We are unique because of our loyalty.
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
""""""""""""""""""ዐ""""""""""""""""""""""
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches (27.94cm-30.48cm)፡ በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡ ከ1.1ኪሎ እስከ 1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፍትዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ (CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Corei5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM):
ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5. የሃርድ ድራይቭ አይነት፡
ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና መገልበጥ (copy) ማድረግ ያስችለናል፡፡
6. የምስል ጥራት (via Resolution)
የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን። Full HD 1080P በመባልም ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡
አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡
የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶች ባሉበት ገበያ የትኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
23/08/2017
የስልክ ስክሪን መጠገን
ስልካችን ከእጃች ላይ ወድቆ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ስክሪኑ ሊሰበርብን ወይም ሊሰነጣጠቅብን ይችላል።
የስልካችን ስክሪን በተሰበረ ቁጥር አዲስ ስልክ መቀየሩም ደግሞ ሊከብደን ይችላል።
ታዲያ በዚህ ጊዜ ያለን አማራጭ ስክሪኑን ጠግኖ መጠቀም ወይም ደግሞ አዲስ ስከሪን በማስቀየር መጠቀም ነው።
የስልክ ስክሪንን ለምን በቶሎ ማሰራት ይኖርብናል?
ስልካችን በድንገት አደጋ ደርሶበት ስክሪኑ የመሰንጠቅ ወይም የመሰበር አደጋ ካጋጠመው በፍጥነት ስክሪኑን ማስቀየር ወይም መጠገን ይኖርብናል።
ምክንያቱም ደግሞ የስከሪኑ መሰንጠቅ እየቆየ በሄደ ቁጥር በመስፋት ሌሎች የስልካችን ክፍሎች ለውሃ እና ለሌሎች ብናኞች እንዲጋለጥ በማድረግ ስልካችንን ለከፋ ብልሽት ሊዳርግ ስለሚችል ነው።
ሌላኛው በቶሎ የተሰነጠቀውን ስክሪን እንድንቀይር የሚያደርገን ነገር ደግሞ የስልካችን ስክሪኖች ከሰውነታችን ጋር ንክኪ ስላላቸው የተሰነጠቀው መስታወት ፊታችን እና ጣቶቻችን ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ነው።
እንዲሁም ስልኩ ሲሰነጣጠቅ የሚፈጠሩት የስክሪኑ ሽርፍራፊዎች እና ሌሎች ስለኩን ሊጉዱ የሚችሉ ነገሮች ስልኩ በተሰነጠቀበት በኩል ወደ ስልኩ በመግባት ስልኩን ለከፋ ብልሽት ሊዳርጉት ስለሚችሉም የተሰነጠቀ የስልክ ስክሪንን በፍጥነት ማስጠገን ይጠበቅብናል።
የስልካችን ስክሪን ከተሰነጠቀ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል፦
የስልካችን ስክሪን ከተሰነጠቀብን እና በቶሎ ማስጠገን የማንችልበት አካባቢ ካለን የተሰነጠቀውን ስፍራ በፕላስቲክ ማሸጊያዎች መሸፈን የመጀመሪያው አማራጭ ነው።
ሌላኛው በአቅራቢያችን ወደ ሚገኙ የሞባይል መጠገኛ ቤቶች በመሄድ የስልኩን ስክሪን ማስጠገን ወይም ማስቀየር ይኖርብናል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)
31/07/2017
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 20:00 |
| Tuesday | 09:00 - 20:00 |
| Wednesday | 09:00 - 20:00 |
| Thursday | 09:00 - 20:00 |
| Friday | 09:00 - 20:00 |
| Saturday | 09:00 - 20:00 |