Ab computer Top learning
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ab computer Top learning, Education, Ab, Hossana.
17/09/2022
🤔Graphics_cards
🤔Nividia
Graphics/Display/Video Card ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/
አሁን አሁን የምንገዛቸው ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የሒሳብ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።
⇒በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት እና ናቸው።
ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።
ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?
( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው።
ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።
ኮምፒዩተራችን Graphics card እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?
👉 የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
👉የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኋላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
👉ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።
❖ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!
❖አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።
የርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?
32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> properties -> system type የሚለውን ይመልከቱ
እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ
ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
ማስታወሻ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች
የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም) 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆ
Top
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Ab
Hossana