Zeagelo Page

Zeagelo Page

Share

PEACE AND RESPECT FOR ALL OF US CITIZENS AND THE WORLD Follow

25/03/2026

ሰበር ዜና! ታዋቂዎቹ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ሠራዊት ፍቅሬ፣ መንሱር ጀማል፣ ልጅ ካሊድ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ ይገረም ደጀኔ እና አብርሃም ግዛው በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰሞኑ በፊን ቴክ ኢንቨስትመንት ተጭበርብረናል የሚሉ ግለሰቦች በፍትህ ሚኒስቴር ተገኝተው ባሰሙት አቤቱታ መሆኑም ታውቋል። ፊን ቴክ ኢንቨስትመንት የተሰኘ ድርጅት በታዋቂዎቹ ግለሰቦች በኩል ገንዘብ ለቆጠቡ መኪና እንደሚሰጥ በማስታወቅ ከተለያዩ ግለሰቦች የተለያዩ መጠን ያላወቸውን ገንዘብ ተቀብሎ መጥፋቱን ተከትሎ ገንዘብ መጭበርበራቸውን የሚገልፁ ተበዳዮች ከሰሞኑ መደመጣቸው ይታወቃል።

06/10/2025

የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ አስተማማኝ ደርጃ ላይ ደርሷል

#የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ አስተማማኝ ደርጃ ላይ ደርሷል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናገሩ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

ንግግር ያደረጉት ፕሬዜዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፤ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወደ አለ ደርጃ የተሻገረበት ነው ብለዋል።

የባሕር በር ፍትሕዊ ተጠቃሚነታችንን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በድንበር ተሻጋሪ ሀብት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስተቀበል፤ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ጋዜጣ+

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Jimma?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Jimma
Jimma
1983