Kemal indiris

Kemal indiris

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kemal indiris, College & University, Metu.

21/10/2025

ከቆምን 15 ቀናችን
የተበላሸ ማዳበሪያ ነው
ከጂቡቲ ለደብረ ብርሀን ማዳበሪያ ጭነን ብንደርስም ዩሪያ ማዳበሪያ የተበላሸ ነው አናራግፍም በማለት መፍትሄ የሚሰጠን አካል በማጣት ከቆምን 15ኛ ቀናናችን ሆኗል በማለት መልዕክት አድርሰውናል።

እኛ ከወደብ የጫንነውን ጭነት በሀላፊነት ተረክበን ይዘን ብንደርስም እኛን የማይመለከት ችግር በማንሳት ማዳበሪያ የተበላሸ ስለሆነ አናራግፍም በማለት የባንክ ዕዳ የእቁብ ክፍያ ቤተሰብ የማስተዳደር ሀላፊነት የተጫነበትን መኪና ለ15 ቀን ማቆም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።

ደብረ ብርሀን ስምሪት ተሰጦን ከጅቡቲ የመጣን 35 መኪኖች ስንሆን እስካሁን መፍትሄ የሚሰጥ ባለመኖሩ ለከፋ ጉዳት ተዳርገናል ብለዋል።

ይህ ማዳበሪያ እየተጫነ ባለበት ወደብ ላይ የጥራት ችግር አለበት ብለን መረጃ ስናጋራ ኬሚስት ነን ምናምን የሚሉ ጭፍኖች መገገሩ ችግር የለውም በማለት ሊዘልፉን የሞከሩ አካላት ነበሩ ጭፍኖች ዛሬስ የት ናችሁ ??

የደብረ ብርሀን ግብርና ቢሮ ማዳበሪያውን አስጭኖ ከላከ አካል ጋር በመነጋገር ችግሩን ሊፈታ ይገባል መኪኖችን በዚህ መልኩ ለ 15 ቀን ማቆም በግለሰብም በሀገርም ላይ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ማምጣት መሆኑን ልታውቁ ይገባል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ይህንን ልክ ያልሆነ ድርጊት በመመልከት ለ15 ቀናት የቆሙ መኪኖችን መፍትሄ የሚያገኙበት ሁኔታን ሊያመቻች ይገባል።

18/08/2025

ከመስከረም 2018 ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ይህ የደመወዝ ማሻሻያ በዜጎች የኑሮ ሁኔታ ላይ መሻሻል ለማምጣት ያለመ ሲሆን፣ በሁሉም የመንግስት የስራ ዘርፎች ላይ እንደሚተገበር ተገልጿል።

በተደረገው ማሻሻያ መሰረት፡-

* ዝቅተኛው ደመወዝ ከ4,760 ብር ወደ 6,000 ብር ከፍ ይላል።

* ከፍተኛው ደመወዝ ከ21,492 ብር ወደ 39,000 ብር ያድጋል።

* የዲግሪ ተመራቂዎች መነሻ ደመወዝ ከ6,940 ብር ወደ 11,500 ብር ከፍ ብሏል።

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ለመንግስት ሰራተኞች የሚወጣው ዓመታዊ የደመወዝ ወጪ 560 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ዘገባዋ የፋና ነው::

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

Want your university to be the top-listed University in Metu?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Metu