Soddo Christian Hospital

Soddo Christian Hospital

Share

Soddo Christian Hospital is located in southern Ethiopia where there is limited healthcare available for a population of more than 10 million people.

18/05/2026

ማስታወቂያ
ቀን፡ 10/09/2018
የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኃላ.የተ የግ ማሀበር የጠቅላላ ሐኪም ባለሙያን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለው ፍላጎት በቁጥር SCH-586-10-18 በቀን 30-8-2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት የተመዘገባችሁና የጽሑፍ ፈተና የተፈተናችሁ፡-

የጽሑፍ ፈተና ውጤት 20 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች ዛሬ በቀን 10/09/2018 ክቀነ- 08:30 ሰዓት ላይ ለቃለመጠይቅ ፈተና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያና ቀደም ሲል ያቀረባችሁትን ዶክሜንት original copy በመያዝ ወደ ሆስፒታሉ አስተዳደር ሕንፃ እንድትቀርቡ ማስፈለጉን እያስታወቅን መታወቂያ ሳይዝ የሚቀርብ ተወዳዳሪ ለፈተና መቅረብ የማይችል መሆኑን ጭምር በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ !

Photos from Soddo Christian Hospital's post 23/04/2026

አራት ህፃናት በአንድ መሃፀን

የምሰራዉ የማህፀን እና የህፃናት ህክምና ክፍል ተናበዉ እና ተነጋገረዉ በሚሰሩበት ሆስፒታል ነዉ ። በእለቱ ተረኛ ሁኘ በጣም የታመመ ጨቅላ ህፃን ለማትረፍ ደረቱን በመጫን እና በማስክ ኦክሲጅን እየሰጠሁ በአለበት ሰዓት ከማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪሙ ስልክ ተደወለልኝ ፤ በመድማት ላይ ያለች እናት 29ሳምንት የሆናቸዉ መንታ እንዳረገዘች ከሚገልፅ የሪፈራል ወረቀት ጋር እንደመጣች እና የሶኖግራፊ ምርመራ ለማድረግ ጊዜ እንደለለዉ ቀጥታ ወደ ኦፕሬሽን ክፍል እየተወሰደች እንደሆነ ህፃኖች ያለድሚያቸዉ የሚወለዱ ስለሆኑ እገዛ እንዳደርግ ኦፕሬሽን ክፍል በፍጥነት እንድሄድ ጠራኝ ።

መንታ በሚወለድበት ጊዜ አንድ ሰዉ ህፃኖችን ለማገዝ በቂ ስላልሆነ እኔ ብቻ ሌላ የህፃናት ሃኪም እንዲያግዘኝ ጠርቸ በሞት መካከል ያለዉን ጨቅላ ለሌላ የህፃናት ሃኪም እገዛ እንድታደርግለት አስረክቤ ወደ ኦፕሬሽን ክፍል በቻልኩት ፍጥነት ለመድረስ ሮጥኩ። ኦፕረሽን ክፍል ከደረስኩ በኋላ ሁለት ህፃናት ለማገዝ የሚችል neonatal corner አዘጋጀን። ሁለት የኦክሲጅን ሶርስ ፣ሁለት ህፃናት የሚያስተኛ የማሞቂያ ቦታ። የማህፀን ሀኪሙ ኦፕሬሽን ጀመረ። እኔ የመጀመሪያ የሚወለደዉን መንታ (twin A) ጓደኛየ ሁለተኛዉን መንታ (Twin B) ለመቀበል ተዘጋጀን።

የመጀመሪያዉ ልጅ ተወለደ አያለቅስም አይተነፍስም ተቀበልኩ እርዳታ ማድረግ ጀመርኩ። ሁለተኛዉ ልጅ ተወለደ ጓደኛየ ተቀብላ እገዛ ማድረግ ጀመረች። ነገር ግን የማህፀን ሀኪሙ ሌላ ሶስተኛ ልጅ አለ ተቀበሉኝ አለ። ለሶስተኛ ልጅ ዝግጁ አልነበርነም። መጀመሪያ የተወለደዉን ልጅ ለጠቅላላ ሃኪሙ በመስጠት ሶስተኛዉን ልጅ ሌላ የኦክሲጅን ሶርስ በመፈለግ ማገዝ ጀመርኩ። ሌላ የህፃናት ሀኪም በፍጥነት ለእገዛ እንዲደርስ ተደወለ ።ሶስት የህፃናት ሀኪም ሶስት ህፃናት። ከሰከንዶች በኋላ ሌላ አራተኛ ልጅ እንዳለ የማህፀን እና የፅንስ ሃኪሙ ነገረን። ምንም የማይተነፍስ የልብ ምቱ የቆመ አራተኛ ልጅ ። ኦክስጅን ሶርስ የለም:ቦታም የለም እገዛ ለመስጠት። በዚህ ሰዓት ያደረግነዉ አንደኛዉን እና ሁለተኛዉን ልጅ ጥብቅ የጨቅላ ህፃናት ክትትል ክፍል(NICU) መላክ ነበር። ሶስተኛዉ እና አራተኛዉን ኦፕረሽን ክፍል እየረዳን ቆይተን አራተኛዉን የጭቅላ ጥብቅ ጥንቃቄ ክፍል በመላክ ሶስተኛዉን ለአንድ ሰዓት ያህል ርዳታ ከተደረገለት በኋላ በአርቲፊሻል መተንፈሻ መሳሪያ (Mechanical ventilator ) በማገዝ ወደ ጥብቅ ጥንቃቄ ክፍል መላክ ቻልን። ሁለት ሴት ሁለት ወንድ በሰላም የተገላገለች ሲሆን እኛ የህፃናት ሀኪሞች የተወለዱ የጨቅላ ህፃናት እንዲተነፍሱ የልብ ምታቸዉ እንዲመለስ ስናግዝ የማህፀን እና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪሙ እና ረዳቶቹ ደም የሚፈሳትን እናት ለማዳን የቻሉትን ጥረት አድርገዉ ለማትረፍ ችለዋል።

የተወለዱት ጨቅላ ህፃናት

1ኛዉ 29 ሳምንት , ክብደት 1055ግራም ፆታ ሴት
2ኛዉ 29ሳምንት , ክብደት 1125ግራም ፆታ ሴት
3ኛዉ 29 ሳምንት , ክብደት 1090 ግራም ፆታ ወንድ
4ኛዉ 29 ሳምንት, ክብደት 1075 ግራም ፆታ ወንድ

አባት ልጆች በሂወት ይወለዳሉ የሚል ሃሳብ አልነበረዉም። ብቻዉን ሆኖ ሚስቱ የማትተርፍ ስለመሰለዉ እያለቀሰ ነበር። ለሚስቱ መድሃኒት እንዲያመጣ ተደዉሎለት ከሰመመን ወደ ሚነቁበት ክፍሌ ሲሄድ አንዲት እናት አራት ልጆች ተገላገለች እያሉ እያወሩ ይሰማል። እሱ የሚስቱን በሂወት መትረፍ እንጅ ስለልጆች በሂወት መወለድ አልሰማም/አያሳስበዉም ነበር።

የመተንፈሻ ጡንቻቸዉ ፣ ሳንባቸዉ እንዲሁም ትንፈሳን የሚቆጣጠረዉ የአእምሮ ክፍል ስላለበሰለ ወደ ጥብቅ ጥንቃቄ ክፍል ከገቡ በኋላ የሳንባ ማጠንከሪያ (surfactant ) ተሰጣቸዉ። ትንፈሳ እንዳይረሱ ካፊን እየተሰጣቸዉ በማሽን እየታገዙ በተለያየ ጊዜ ለኢንፈክሽን ታክመዉ ፣ ለደም ማነስ ብዙ ጊዜ ደም ወስደዉ 3ኛዉ መንታ በተወለደ በ6ቀን ሂወቱ ሲያልፍ 3ቱ መንታ ህፃናት ከ98 ቀናት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤት በሰላም ተሸኝተዋል። ወደ ቤት ሲላኩ የነበራቸዉ
ክብደት

1ኛዋ :2040ግራም
2ኛዋ :2065ግራም
4ኛዉ :1925ግራም

ምስጋና
-ወጫቸዉን ለሸፈነልን BF (Benevolence fund)
-ሰርፋክታንት (Surfactat) ላቀረበልን ድርጅት
-በሂወት ተርፈዉ አድገዉ ወደ ቤት እንዲሄዱ ላደረጋቸሁ የጨቅላ ክፍል ሰራተኞች
-ቀን ከሌት ሳተኙ ስተከታተሉ ለነበራቹ የህፃናት ሃኪሞች
ዶ/ር ሚሸል
ዶ/ር ያዴል
ዶ/ር ሀይሌ
-ተጨማሪ የሰዉ ሃይል ሲያስፈልግ ስታመቻቹ የነበራቹ የአስተዳደር ሰራተኞች።

🖋 ዶ/ር ሀበንዮም ተበጀ | የሕጻናት ስፔሻሊስት

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Christian Hospital Street
Sodo