Dalgadessie83.blogspot.com
To learn good things around the world vai social media and to inform our society! Dessie Ethiopian Facebook Fans Page
15/09/2025
እንኳን ደስ አለህ ኻሊድ በሽር!
ከ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ
591 ነጥብ በማምጣት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ኻሊድ በሽር ነው።
ኻሊድም ይህን ውጤት በማምጣት ከኢትዮጵያ ብቁ ተማሪዎች አንዱ መሆኑን አሳይቷል።
ይህ ስኬት ለሌሎች ተማሪዎች ትልቅ ማበረታቻ ሲሆን፣ ታታሪነትና ትጋት ምን ያህል እንደሚክስ የሚያሳይ ነው።
ወደፊት በከፍተኛ ትምህርት ዘመንህም በዚሁ ትጋትህ እንድትቀጥል እንመኝልሃለን።
ፈተናውን ለወሰዳችሁ ተማሪዎች ሁሉ
ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች ተስፋ እንዳትቆርጡ።
የሕይወት መንገዶች ብዙ ናቸው። ይህ አንድ የትምህርት ምዕራፍ እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ አይደለም።
ሌሎች አማራጮችን በማየት ለወደፊት ህይወታችሁ የሚያግዝ ምርጫ ማድረግ ትችላላችሁ።
ለወላጆች
የልጆቻችሁን ውጤት በመልካም መንፈስ ተቀበሉ። አሁን ላይ የተፈጠረውን ነገር በመልካም ሁኔታ ለመረዳት ሞክሩ።
ቀለሙ ከደረቀ በኋላ የሚቀየር ነገር ስለሌለ በምክርና በፍቅር ልጆቻችሁን ተቀበሉ።
ለሚቀጥለው ሕይወታቸው ትክክለኛውን መንገድ እንዲመርጡም እርዷቸው።
መልካም ለሁላችሁም።
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Wolaita S**o
S**o
50MI