Visit Wolaita

Visit Wolaita

Share

Cultural and Historical Adventure ❤💛🖤

10/12/2025

የዚህ ትውልድ በመሆናችን ኩራት ተሰምቶኛል 💪💪

01/11/2025

Visit Wolaita

12/09/2025

ዮ ዮ ጊፋታ!! Yoo yoo gifaata !!

ዮዮ ..."ጊፋታ" .....የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ሲሆን "ጊፋታ" ማለት ባይራ ወይም ታላቅ፣ መጀመሪያ እንደማለት ሲሆን በሌላ በኩል "ጊፋታ" ማለት መሻገር (መሸጋገሪያ) ማለት ነው::

ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል::

የወላይታ ብሔር የ"ጊፋታ"ን በአል ማክበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዓመቱን ሙሉ ለአስራ አንድ ወራት በስራ ካሳለፉ በኋላ ለአንድ ወር ሙሉ በተለይም በዓመቱ መገባደጃ ያለውን ከባዱን የክረምት ጎርፍና ጭጋግ በማለፍ ከክረምት ጨለማ ወደ ብርሃን የተሸጋገርኩበት ነው ብለው ሲያከብሩ ለአዲሱ ዓመት በሠላም ስለ መሸጋገራቸው ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት ክብረ በዓል ነው "ጊፋታ"::

"ጊፋታ" በአል ለወላይታ ህዝብ፣ ለአከባቢውና ለሀገራችን የሚያበረክተው በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖማያዊ፣ ፖሊቲካዊ እና ባህላዊ ፋይዳዎች ይኖሩታል::

የ"ጊፋታ" በአል በወላይታ ማህበረሰብ ዘንድ የአብሮነት ስሜት እንዲጠናከር የሚያደርግ ሲሆን ይህም ማለት አብሮ መስራት፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጫወት፣ ኢኮኖሚዊ ችግሮችን በጋራ መወጣት፣ መተሳሰብና መረዳዳት የሚገለጽበት በዓል ነው "ጊፋታ"

"ጊፋታ" ሲቃረብ በሚውሉ ሶስት ዋና ዋና ገበያዎች አባቶች በአመቱ ውስጥ ያደለቧቸውን በሬዎችን በመሸጥ ኢኮኖማያዊ ጥቅም የሚያገኝበት፣ እናቶች የቅቤ እቁብ ገብተው ያጠራቀሙትን ቅቤ ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ በማስቀረት ሌላውን በመሸጥ ለበዓሉ ዝግጅት የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኙበት ታላቅ በዓል ነው "ጊፋታ"፡፡

ለ"ጊፋታ" በዓል ለእርድ የሚሆን በሬ ለመግዛት በቡድን አስራ ሁለት የሚሆኑ አባዎራዎች በየሳምንቱ ተቀማጭ ገንዘብ ይቆጥባሉ፣ በአሉ ሲቃረብ ከ"ጊፋታ" ገበያ በሬ መግዛት፣ ለልጆቻቸው አልባሳት፣ ለበአሉ ድምቀት የሚውሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ መግዛትና ማሳደስ የአባቶች ተግባር ሲሆን ለ"ጊፋታ" በአል የሚፋቅ እንሰት ከጓሯቸው መርጦ ማሳየት ተግባር በአባቶች ይከናወናል::

ለ"ጊፋታ" በዓል እናቶች በግልና በቡድን በመሆን ቅቤ ያጠራቅማሉ፣ በአባዎራ ተለይቶ የተሰጠውን እንሰት ፍቆ ቆጮ በአይነት ያዘጋጃሉ፣ የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ፣ ሴት ልጃገረዶቹ የሚያጌጡ የመዋቢያ አልባሳት፣ ለእጃቸው ድምቀት እንሶስላ፣ ለደረታቸው ሎሚና ሌሎች ቁሳቁሶችን ከ"ጊፋታ" ገበያ የመሸመት ድርሻ የእናቶች ተግባር ነው::

በ"ጊፋታ" ሹዋ ዎጋ ወይም እርድ እሁድ ለሚለኮስ "ጉሊያ" ማዘጋጀት ተግባር የወጣቱ ሲሆን ከሰኔ ወር ጀምሮ ጥቅም ላይ የማይውሉ እንጨት አይነቶችን ቆርጦ እየጎተቱ ባህላዊ ዘፈን እያንጎራጎሩ በተመረጡ አድባር በእንጨቶች "ጉሊያ" ይሰራሉ ወጣቶች ለጊፋታ::

ለ"ጊፋታ" በዓል ቅድመ ዝግጅት ወጣት ሴቶች በእናቶቻቸው ጎን በመሆን ሁሉንም የቤት ስራ ሳይመርጡ የመስራት ግደታ አለባቸው፣ ምክንያቱም ሙያ ያላት ሴት ሆና ማደግ እንዳለባት ይታመናል:: ልጃገረዶች ለ"ጊፋታ" በዓል ተውቦ እና ደምቆ አደባባይ የሚወጡበት የነጻነት በአል መሆኑ ለትዳር የደረሱ ሴቶች በ"ጊፋታ ጋዜ" ጫወታ የሚተያዩበት በዓል በመሆኑ "ጊፋታ" ለሴቶች ለየት እንደሚል ይነገራል::

የ "ጊፋታ" በዓል መቃረቡን የሚያበስሩና በህዝቡ ዘንድ እጅግ የሚታወቁ በእንቅስቃሴያቸው ከወትሮ የተለዩ ገበያዎችም ያሉ ሲሆን እነሱም "ሃሬ ሀይቆ"፣ "ቦቦዶ"፣ "ጎሻ" በመባል የሚታወቁ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ "ቃኤ ጊያ" ይባላል::

ይቀጥላል...

11/09/2025

YOO YOO GIFAATAA ❤💛🖤

Want your business to be the top-listed Photography Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Sodo