Awramba Times
Awramba Times is an online media outlet providing latest news and analysis about Ethiopia & the horn
የደብረጽዮንና የአብይ የአራት ሰአታት ውይይት
----------
ብዙዎቹ የህወሓት መሪዎች ጓደኞቼ ናቸው። እናም በሚዲያ ቃለምልልስ ላይ ስነሱ ስጠየቅ ክፉ ላለመናገር እጠነቀቃለሁ።
ዛሬ ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ። ቅድም ጌታቸው የጠቀሰው ሰው (ዶ/ር ደብረጽዮን መሆናቸው ልብ ይሏል) እኔ ባለሁበት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለብቻቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ለአራት ሰአታት የፈጀ የእግር ጉዞ እያደረጉ ሰፊ ውይይት አድርገው ነበር ከዛ በኋላ እኔና ዶ/ር ደብረጽዮን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ውይይት አደረግን። ከዛ ምን ተፈጠረ?
ዝርዝሩን ከአቶ ዘሪሁን ተሾመ አንደበት!
ኮነ ኢሉ ናይ ስድራ መለስ ሹም ንኽጠፍእ ዝገብር ዘሎ ጌታቸው ኣሰፋ እዩ። እዙይ ድማ መለስ ብሂወት እናሃለወ ዝተጀመረ ናይ 20 ዓመት ፕሮጀክት እዩ። ካብ ጌታቸው ብተወሳኺ ፈትለወርቅ ብ1979 ዓ.ም ገምጊሙኒ ነይሩ ኢላ ኣይትፈትዎን። ደብረፅዮን እውን ብ1993 ዓ.ም ናብ ማይጨው ደብርዩኒ ብዝብል ፅልኣት ኣለዎ!
-----
ሙሉእ ትሕዝቶ ናይቲ ኣብ ላንዳ ሪፖርት ዝወፀ ቃለመሕትት ንምክትታል ሊንክ ኣብ ኮመንት ተቐሚጡ ኣሎ።
04/07/2026
ፈትለወርቅ ዲፕሎማሲ ምን እንደሆነ አልገባትም ስትል
ሰምሃል መለስ ገለጸች
------
አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ፣ ሰምሃል መለስ ዜናዊ በቅርቡ በትግራይ የወጣውን አዲስ አዋጅ "የደርግን ስርአት የሚያስታውስ አዋጅ" ስትል የሰላ ትችት አቀረበች።
ከ #ትግሃት ሚዲያ ጋር በቅርቡ ቃለምልልስ ያካሄደችው ሰምሃል መለስ፣ አዲሱ አዋጅ ህግ በሚያውቁ ሰዎች ይቅርና ማንበብና መጻፍ በሚችሉ ሰዎች እንኳን ተጽፏል ብላ ለማመን እንደምትቸገር ገልጻ "ብዙ ችግር ያለበት አዋጅ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ሀሜትን እንኳን የማይፈቅድ የደርግ ዘመን ህግ ነው" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
የህወሓት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸውን አስተያየቶች በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላት ሰምሀል፣ የፈትለወርቅ መግለጫ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንዴት እንደሚታረም የመፍትሄ አቅጣጫ ከማቅረብ ይልቅ የሷና የቡድኗን ስልጣን ማጠናከርን ብቻ ታሳቢ ያደረገ አሰልቺ ዲስኩር ስትል ገልጻዋለች። አሁን ያለው የአለም ሁኔታም ሆነ ዲፕሎማሲ እንዴት እንደሚሰራ ፈትለወርቅ ጨርሶ አልገባትም ስትል የምትሟገተው ሰምሃል፣ ዲፕሎማሲ ማለት ለሚወጡብህ የተቃውሞ መግለጫዎች መልስ መስጠት ማለት አይደለም ከዛ ይልቅ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተገንዝቦ የማሻሻያ እርምጃዎችን ይዞ መቅረብ ነው ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
ቀደም ባሉ ጊዜያት በህወሓት ዙሪያ ብዙ ምሁርና አሰላሳይ ልሂቅ ነበር የምትለው ሰምሃል አሁን ግን ያ ሁሉ አቅም ተበትኖ ፓርቲው እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ማየት እንደሚያሳፍራት በቁጭት ገልጻለች።
"ኣብቲ ሽዑ እዋን ጌታቸው ኣሰፋ ዝኾነ ኣጋጣሚ እንተረኺቡ ክርሽነኒ እዩ ይሓስብ ነይሩ። ስብሓት ግን ከምኣ እንተጌርካ ክትእሰር ኢኻ ኢሉ!"
ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ ምስ ቲቢኤስ ኣብዝነበሮ ፃንሒት ዝተዛረቦ!
ምኽሪ ንዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
------
ናትካ ፕረዚደንትነት ንዓና እንታይና እዩ? ንስኻ ፕረዚደንት ንኽትኮን ተባሂሉ ትግራይ ናብ ኩናት ካብትኣቱ፣ ወዲ ውለድ እሞ ሹሙ "ፕሬዚዳንት" በሎ!
13/06/2026
የኤርትራ መንግስት ለአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ለአቶ ጌታቸው ረዳ ምላሽ ሰጠ
---------
አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠ/ሚ አብይ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን በኤርትራ መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ክስ በአልጀዚራ ማስነበባቸውን ተከትሎ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ሬድዋን እና አቶ ጌታቸው በዚሁ መጣጥፋቸው በህወሓት እና በኤርትራ መካከል አዲስ ትብብር መጀመሩን በመጥቀስ ይህ ትብብር ደግሞ በጥቂት ቀናት ውስጥ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ አዲስ ጦርነት ለመክፈት ያለመ መሆኑን ጠቅሰው ነበር።
ይህንኑ የሁለቱም ኃላፊዎች ክስ ተከትሎ የኤርትራ የዜና ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ምላሽ የባለሥልጣናትን ንግግር "በሐሰት፣ በማታለልና በተሳሳተ መረጃ የተሞላ" ሲሉ አጣጥለውታል። አቶ የማነ ምላሻቸው በመቀጠል ይልቁንም ዛሬ ክስ እያቀረቡብን ያሉት አካላት "የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ ከጥቂት ወራት በፊት በጅቡቲ እና ሲሸልስ በሚስጥር ተገናኝተው በኤርትራ ላይ የጋራ ወረራ ለመፈጸም ሲዶልቱ ነበር" በማለት ከዚህ በፊት ያልተሰማ ሌላ አዲስ ትርክት ይዘው መጥተዋል።
ይህንኑ ኤርትራን ለመውጋት ያለመ ምስጢራዊ ምክክር አቶ ጌታቸው ረዳ ራሳቸው ከዚህ ቀደም ተናግረውት ነበር የሚሉት አቶ የማነ በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ለሚታየው አለመረጋጋት መንስኤው የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ እያራመደው ያለው የባሕር በር መሻት የወለደው የጠብ አጫሪነት ንግግር ነው በማለት አሁን አሁን በኛ ላይ የቀረበው ክስ ይሄንኑ “የራሳቸውን” የጦርነት አጀንዳ ለመሸፈን የታለመ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው ሲሉ ምላሻቸውን አሳርገዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
700 Bellevue Way NE
Addis Ababa
98004