Sodere

Sodere

Share

Sodere is Ethiopian film streaming service, website, application and online store. Sodere Media produces and owns the largest Ethiopian movies library.

Photos from Sodere's post 07/15/2026

አርጀንቲና እንግሊዝን በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ አለፈች

እንግሊዝ በአንቶኒ ጎርደን ግብ እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ ዐ እየመራች ብትቆይም አርጀንቲና በኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ ግቦች ጨዋታውን አሸንፋለች።

ሊዮኔል ሜሲ ለሁለቱም ግቦች ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ቁልፍ ተጫዋች መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

አርጀንቲና በፍጻሜው ከስፔን ጋር ትፋለማለች፡፡

Photos from Sodere's post 07/14/2026

ካምፓስ ተከታታይ ድራማ በፋና ቴሌቪዥን እየተላለፈ አንድ ምዕራፍ ማገባደዱ የታወቀ ነው።

(አሌክስ ዘ መላዕክ )

የስራው የፕሮዳክሽን ጥራት አስደማሚ ቢሆንም የታሪኩ ጥልቀት ደግሞ ምን ሲል አሰበው የያስብልና ዓለማችንን በልዩ አይን እንድንቃኝ የሚያስጠነቅቅም ጭምነር ነው፡፡ አሁን ሁለተኛውን ምዕራፍ ለመጀመር ያኮበኮበበት ጌዜ ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል። ይህ እንዳለ ሆኖ ከምዕራፍ 1 ምን ታዘብን የሚለውን ሀሳብ በይዘት እና አቀራረብ ከፍለን በሁለት መንገድ እንቃኘው ዘንድ በአጭር ጥንቅር እንወያይ።

ይዘት
ካምፓስ ሆራይዘን በተባለ ዩንቨርሲቲ በኛ ገሃዳዊ አለም የሌለ ግን ደግሞ እውናዊ አሳማኝነቱነ (Verisimilitude) በጠበቀ መልኩ የተፈጠር ዩንቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆኑ ወጣቶች ህይወት ላይ ያተኮረ ሆኖ በተለየ ደግሞ የዋና ገጸ-ባህሪትዋን (መስከረምን) የህይወት ምስቅልቅል ያስቃኘናል። በምዕራፉ ሂደት ውስጥ ወጣትነት ሲፈተን አላማ፣እቅድ፣በራስ ላይ የነበረ መተማመን በከባድ የህይወት ጥያቄ ሲነቀነቅ፣ጓደኝነት፣ሀቀኝነት፣ፍትወት፣የገንዘብ ኃያልነት ሲፈተሹ እናይበታለን። ተራ የማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚመስል ግን ወጣቶችን ወዳልተፈለገ የወሲብ ንግድ የሚመራ ወጥመድ ምን ያህል በተማሪዎች የለትለት እንቅስቃሴ የሚያሳድረውንተጽዕኖ በጉልህ ማሳየት ችሏል!
በገሃድ አይወጣ እንጂ በሀገራችን ቀስበቀስ እየተንሰራፋ የመጣው ስልጣኔ መሰል በወጣቶች አካባቢ የሚታይ የዝንጋኤ አባዜ በፊልማዊ ለዛ ለመዳስ ተሞክሯል።

አቀራረብ
በፊልም አቀራረብ የሚወሰነው በፕሮዲውሲንጉ ትክክለኛ ውጥን እና ትልም አማካኝነት ይሆናል።
"Producers wear more hats than a haberdasher... hold the vision while dealing with the reality keep their cool when the ship is sinking." Maureen Ryan,Producer to Producer(2023)

"ፕሮዲውሰሮች ከባርኔጣ ሻጭ በላይ ብዙ ኮፍያዎችን ይደፋሉ... እውነታውን እየተጋፈጡ ራዕዩን ሙጥኝ ብለው ይይዛሉ፣ መርከቧ እየሰመጠች ባለችበት ወቅት እንኳ መረጋጋታቸውን አይጡም።"

በቅድሚያ በራስ ተነሳሽነት ከትልቅ ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረም አስቀድሞ በራስ ወጪ አንድ ምዕራፍ ወይንም 20 ክፍላት አካባቢ ቀርጾና አቀናብሮ ለእይታ ማብቃት ትልቁ ተግዳሮት ነው። በዚህ ወስጥ ደግሞ ኪስ ላይ ፈርዶ ተረጋግቶ ስለ ምስል ቅንብር ወይንም ኮምፖዚሽን በመጨነቅ ታሪክ ነጋሪ ምስሎችን ከማስቀረት ባለፈ ሲኒማቶግራፊው ታሪኩን እንዲያወራ ነጻነት መስጠት ለህልም የተከፈለ ታላቅ መስዋዕትንት ነው ሊያስብለው ይችላል። ዝግጅትን በተመለከተ አዘጋጁ በምናቡ የሚከሰቱትን ምስሎች ለተመልካች ዓይን እንዲመጥን አልያም ደግሞ የሱን ፈጠራ አቅም በሚገልጥበት መንገድ ተጠንቅቆ መስራት አለበት። የፊልም ተመራማሪዋ ክላውዲያ ጎርብማን እንደምትገልጸው Cinema The concept of the director as an 'auteur' suggests that a film reflects the director's personal creative vision. በሲኒማ ጥበብ ውስጥ ዳይሬክተርን እንደ ‘ኦተር’ (auteur - ዋነኛ ፈጣሪ) አድርጎ የመውሰዱ እሳቤ፤ አንድ ፊልም የዳይሬክተሩን የግል የፈጠራ ራዕይ እንደሚያንጸባርቅ ያመለክታል።"

ፊልም የአዘጋጁ የውስጥ ፍላጎት እና ተምኔት ውጤት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። እዚህ ጋር አዘጋጁ በምን ያህል መጠን የሀሳቡን በምስል አሳይቶናል የሚለው ነው ቁምነገሩ። ከብርሃን አጠቃቀም ጀምሮ እያንዳንዱ ካሜራው በአራት መዓዘን ቅርጹ የሚያካትታቸው ነገሮች በተቻለ መጠን ታሪክ ነጋሪ ሆነው ቀርበዋል። ሴንተር ኮምፖዚሽን ወይንም መሃከልን መሰረት ያደረገ የምስል ቅንብር በቀላሉ የገጸባህሪያትን ስሜት ከተደራሽ ጋር ለማዋሃድ በሚረዳ መለኩ ከሚወሰዱበት አላማ አንጻር ጥሩ አጠቃቀም ላይ ውለዋል ብሎ ማለት ይቻላል።ሥዕላት፣ቅርጻ ቅርጾች በበኩላቸው የስራ ፈጣሪዎቻቸው ከተለሙላቸው ጥበባዊ ትርጓሜም ዲ ኮንስትራክት በማደርግ ለድራማው ገጸባህሪያት ውስጣዊ ስሜት እና በሰዓቱ የሚገኙበትን ሥነ ልቡናዊ ውጥረትመግለጫ ሆነው ቀርበዋል።

በተጨማሪ አብዛኛዎቹ በፊልሙ ላይ ዋና እና ወሳኝ ንዑስ ሚናን በመያዝ የሚጫወቱት ተዋንያን በቴሌቪዥን መስኮታችን እምብዛም ያልተላመድናቸው መሆናቸው ደግሞ አብሮ ማደግ አቋም ሲሆን እስከመጨረሻዋ ህቅታ ድረስ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚጋረጥና መገዳደርም ማሽንፍም እንደሚቻል አሳይተዋል ማለት ይቻላል። በተከታታይ ፊልም ላይ የሀሳቡ አመንጪ የሚሆነው ሙያዊ ስያሜ “የስራው ፈጣሪ(Creater) ከመሆን ባለፈ ዋና ጸሃፊ ሆኖ ከመጻፍ ባለፍ የመራሄ ፊልምነት (አዘጋጅነት) ጥሙን እስከመወጣት በፈጠራው ሲሳተፍ ፊልሙንም ፕሮዲውስ አድርጎ እዚህ ያደረሰው አብይ ጌታሁን ይባላል። አብይ በፊልም ሙያ ላይ ዘለግ ያለ ዓመታት ልምድ ያለው በሳል ፊልም ሰሪ ከመሆኑም ባሻገር ሙያውን በእውቀት በመደገፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ ዲግሪ በጥሩ ውት መጨረሱ ለሙያው ያለውን ታማኝነት የሚያሳይ ነው፡፡ ምዕራፍ ሁለት በሽልም ይወጣ ከሚል ምርቃት ጋር የመጀመሪያውን ምዕራፍ ጥንካሬ የሚያስቀጥል እንደሚሆን እጠብቃለሁ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Santa Monica?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


312 Arizona Avenue
Santa Monica, CA
90401