Maleda Media
IGNITING CIVIC ENGAGEMENT!
12/15/2025
ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) የዘንድሮው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደር በይፋ አሳወቀ።
*****
የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው የፓርቲዉ ስራ አስፈፃሚ 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ተሳትፎን በተመለከተ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከፓርቲው ቁጥጥር ኮሚሽን ጋር በጋራ ገምግሞ ውሳኔ እንዳስተላለፈው ገልጿል።
ፓርቲው ከፍተኛ አካል ያላቸዉ የፓርቲዉ አመራር ጋር በጋራ በመሆን ፓርቲው በ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ በሚሳተፍበት ሁኔታ እና በፓርቲው አሁናዊ ቁመና ላይ ጥልቅ ግምገማ ያካሄደ መሆኑን በመግለጽ፤ በምርጫው ለመወዳደር ዝግጁ እንደሆነና በክልሉ ባሉት አስራ ዘጠኙም የምርጫ ክልሎች የሚወዳደሩ እጩዎችን መልምሎ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርብ አቅጣጫ ተቀምጧል ብሏል።
በግምገማ ወቅት ፓርቲው ከምርጫ ቦርድና ከመንግስት አካላት እየደረሰበት ስላለው ተግዳሮትና እና ወደፊት ሊደርስበት ስለሚችሉ መሰናክሎች በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ችግሩን በውይይትና በንግግር ለመፍታት እንደሚሞክር አቅጣጫ አስቀምጧል ተብሏል።
አክሎም በዋናነት የምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት የተሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ባለመፈፀምና በተለያዩ ጊዜ ፓርቲው በደብዳቤ የጠየቀውን ጥያቄዎችን በጊዜ ምላሽ ባለመስጠት ለዝግጅት መሰናክል እየሆነበት መሆኑን አንስቶ በሰፊው መወያየታቸውን በመግለጽ፤ ጉዳዩን ተከታትሎ የደረሰበት ደረጃ ለህዝብና ለአባላቱ ይፋ እንደሚደረግ አፅኖት ሰጥቷል።
በመጨረሻም ፓርቲው በሀገራዊ ምርጫ ተሳትፎ ዙሪያ የደረሰበት ደረጃና ሁኔታ ለመላው ሲዳማ ህዝብና ለአባላቶቹ ይፋ እንደሚያደርግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል ስል በማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገጽ አስነብቧል።
ማለዳ ሚዲያ
12/10/2025
በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬትና መሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ሙስናና ሌብነት መንሰራፋቱ ተጠቆመ።
******
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በብልሹ አሰራር ውስጥ ተዘፍቀው በተገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ብሏል። ህብረተሰቡም በ7079 ነፃ የስልክ መሥመር ተጨባጭ ጥቆማ ይስጠኝ ብሎአል።
ቢሮው የሰነዳቸው መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በ2017/18 በጀት ዓመት በብልሹ አሰራር ውስጥ ተዘፍቀው የተገኙ 138 አመራርና ሠራተኞችን በመለየት 66ቱን ከስራ ማሰናበትን ጨምሮ በከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የተቀሩት ደግሞ በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እንዲቀጡ ማድሰጉን አስታውቋል።
ቢሮው ምንም እንኳን እርምጃ እየወሰድኩ ነው ቢልም ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ እንደሆነ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይናገራሉ። “ሙስና ካልሰጠህ፣ ካልተጠቃቀምክ ሕግና ሥርዓት ሰለተከተልክ የሚያልቅልህ ጉዳይ የለም። ኢንቨስትመንትና ትላልቅ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተተፍ ከደላላ እስከ ቢሮ ኃላፊዎች ቀድመው በፐርሰንት ይቀባበሉሃል። በትንሹ መታወቂያ ለማውጣትና ያገባ/ያላገባ የድጋፍ ደብዳቤ ብትፈልግ ከ15 -20 ሺህ ብር ጉቦ መክፈል የተለመደ አሠራር እየሆነ መጥቷል “ ይላሉ።
ብዙዎች በአዲስ አበባ በዘመድ አዝማድ ትሥሥር ወይም በጉቦ ካልሆነ የመንግሥት አገልግሎት ማግኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱ ላይ ይስማማሉ።
ማለዳ ሚዲያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Seattle, WA
98134