Christ Embassy DMV Amharic Service
Believers LoveWorld Incorporated, (a.k.a Christ Embassy) is a global ministry with a vision of taking God’s divine presence to the nations of the world
የእሁድ 05/31/26 ቀጥታ ስርጭት ክሪይሰት ኤምባሲ ዲ. ኤም. ቪ. የአማሪኛ ፕሮግራም
የክርስቶስ የማዳን መልዕክት
📖 ════════
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። (ማቴዎስ 24:14) ።
ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
የክርስቶስ የማዳን መልዕክት በዓለም ላይ ላለው ጨለማና ግራ መጋባት የእግዚአብሔር መልስ ነው። ጌታ ዳግመኛ ከመምጣቱ በፊት ሁሉም ሰው ይሄን ወንጌል እንዲሰማና እንዲቀበል ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው። ጌታ ወንጌል በዓለም ሁሉ ለምስክርነት እንደሚሰበክ ተናግሯል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።
ይህ ማለት የጊዜው ቀመር የተዘጋጀው ቤተክርስቲያን ሥራውን እንድትጨርስ ታስቦ ነው። እናንተ ዘመኑን ለመጨረስ ከተመረጠው ትውልድ አካል ናችሁ። ዝም ብላችሁ ሌሎች ሲሰሩ አትመልከቱ። በምልጃ ጸሎት፣ ወንጌልን ለመስበክ በሚደረግ እንቅስቃሴ፣ በገንዘብ አብሮ ሰራተኛ በመሆን እና በድፍረት በመመስከር በንቃት ተሳተፉ።
የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዓለማችሁን እንድትደርሱ መሳሪያውን አስታጥቋችኃል። 2ኛ ቆሮንቶስ 3:5-6 እንዲህ ይላል "ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤ እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን . . ." የሐዋርያት ሥራ 1:8 እንዲህ ይላል "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።"
አስታውሱ፥ ተልዕኮው ይቀጥላል። የመንፈስ ትዕዛዝ እና አስቸኳይነት ግልጽ ነው፤ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ፥ አንድ አምላክ ብቻ እንዳለን እና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ የሰጠው ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ እንዲያውቁ ይፈልጋል። (1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5-6)።
ለችግር ሁሉ መልስ እርሱ ነው፣ በዓለም ውስጥ ላለ ህመም፣ መከራ፣ መበስበስ እና በሽታ መፍትሔ እርሱ ነው። እርሱ ሕይወት ሰጪ ነው። እርሱ እውነተኛው አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው "የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው" (1ኛ ዮሐንስ 5:20) ።
ጸሎት / የእምነት አዋጅ
━━━━━━━━━
ውድ አባት ሆይ፣ የወንጌልን ኃላፊነት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ። የክርስቶስን ፍቅር፣ ኃይልና ጽድቅ ለዓለሜ ለማድረስ በመንፈስህ ኃይል አግኝቻለሁ። በእኛ በኩል ጸጋህና እውነትህ በሁሉም ሥፍራ ይገለጣል እንዲሁም በዓለም ሁሉ ያሸንፋል። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት:
የማርቆስ ወንጌል 16:15;
ሮሜ 1:16;
የማቴዎስ ወንጌል 28:19-20
━━━━━//━━━━━
RHAPSODY OF REALITIES(Amharic)
(ዓርብ - ታህሳስ 24 - 2018)
12/07/2025
እግዚአብሔርን በቅንነት እና በደስታ አገልግሉ
📖 ════════
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ (1ኛ ቆሮንቶስ 15:58) ።
ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
የክርስትና ሕይወታችን ጨዋታ አይደለም፤ ዋና ነገር ነው እንዲሁም በመንፈሳዊ መርሆች ላይ የተመሰረተ ነው። እየኖርን ያለነው መንፈሳዊ ሕይወት ነው። የቤተክርስቲያን ንጥቀት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ ቀርቧል። ስለዚህ፣ በየቀኑ፣ ንጹህ አእምሮአችሁን ማንቃት፣ እራሳችሁን መገምገም እና የክርስትና ሕይወታችሁ ከቃሉ ጋር የሚስማማ መሆኑን ማረጋገጥ አለባችሁ።
ትኩረታችሁን በቃሉ ላይ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ". . . በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል" (ኢያሱ 1:7) ። ቃሉ በአእምሮአችሁ እና በመንፈሳችሁ ላይ፣ በሃሳባችሁ እና በአመለካከታችሁ ላይ እንዲገዛ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው ይላል (መዝሙር 119:105) ። በጨለማ ጎዳና ስትጓዙ፣ መንገዱ እንዲታያችሁ መብራት ትጠቀማላችሁ። ያም ቃሉ ነው፤ የሕይወትን መንገድ ያሳያችኋል እናም በጽድቅ መንገድ ይመራችኋል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡3 " . . . ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና" በማለት ያስጠነቅቀናል። ቀጥሎም በማቴዎስ 24:12 ጌታ እንዲህ አለ "ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።” ስለዚህ፣ ለጌታ ባላችሁ ፍቅር እንደተቀጣጠላችሁ ቆዩ። ለመንፈሳዊ ነገሮች ያላችሁን እምነት እና ቅንዓት ምንም ነገር እንዲቀንስባችሁ አትፍቀዱ።
ጌታን የእውነት በሚወዱት፥ በትክክል እርሱን በሚያገለግሉት እና በማያገለግሉት መካካል ልዩነት ሊኖር ይገባል። እራሳችሁን መመልከት አለባችሁ። ልባችሁን መርምሩ። መንፈሳችሁ ጠብቁ። በዮሐንስ 13:35 "እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ" ብሎአልና በፍቅር ተመላለሱ።
የክርስትና ሕይወት ጉዞ ነው። እያንዳንዱ ቀን በፍቅር ለመመላለስ አዲስ ቀን ነው። እያንዳንዱ ቀን ጌታን በደስታ ለማገልገል አዲስ ቀን ነው። እርሱ ብርሃን እንደሆነ በብርሃን ለመመላለስ እያንዳንዱ ቀን አዲስ ቀን ነው (1ኛ ዮሐንስ 1፡7)። እያንዳንዱ ቀን የጽድቅ ፍሬ ለማፍራት እና የጽድቅን ሥራ ለመግለጥ አዲስ ቀን ነው። ስለዚህ ጌታን በጽናት እና በደስታ በማገልገል እያንዳንዱን ቀን ውጤታማ አድርጉ።
ጸሎት / የእምነት አዋጅ
━━━━━━━━━
ውድ አባት ሆይ፣ አንተን የማወቅ እና የማገልገ እንዲሁም በአንተ ስም ስለመጠራት እድል እና በረከት አመሰግንሃለሁ። በጌታ ሥራ ሁልጊዜ የበረታሁ፣ የተቀጣጠልኩ እና የማልነቃነቅ ሆኔ እቆማለሁ። በደስታ ልብ፣ በመሰጠት እና በዓላማ ሳገለግልህ ለአንተ ያለኝ ፍቅር ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ ነው። ክብርህን በመግለጥ እና ጽድቅህን በማሳየት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የበለጠ አበራለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት:
ዕብራውያን 12:1-2;
ዕብራውያን 6:10-12;
ገላትያ 6:9
━━━━━//━━━━━
RHAPSODY OF REALITIES(Amharic)
(እሁድ - ህዳር 28 - 2018)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Website
Address
8777 Georgia Avenue
Silver Spring, MD
20910
Opening Hours
| Wednesday | 10am - 1:30pm |
| 8pm - 9:30pm | |
| Sunday | 10am - 1:30pm |
| 8pm - 9:30pm |