Sidama Media Network-SMN
Nearby non profit organizations
1620 Elton Road #204
Sidama Media Network
03/22/2026
የግሎባል ሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር (GSDA) ሥራአስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ።
**************/***************
SMN, ዲሲ
ማርች 21 2026
ላለፉት ወራት ሲካሄድ የቆየው የግሎባል ሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር(GSDA) የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆልኗ።
ምርጫውን ሲያከናውን የቆየው፣ ሶስት አባላት ያለው አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ በተካሄደው የካውንስሉ ስብሰባ ላይ፣ ከቀረቡት ስምንት ዕጩዎች መካከል በየፖዚሺኑ አብላጫ ድምጽ ያገኙትን አምስት አሸናፍዎች ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት የተመረጡ ግለሰቦች
1ኛ. ዶ/ር ጸጋዬ ግንቦ:- ፕረዚዴንት
2ኛ አባ ሙሴ ዮሀንስ:-ም/ፕሬዚዴንት
3ኛ. አቶ ነጋ ጠይቀ:- ፋይናንስ ኦፍሴር
4ኛ. አቶ ከበደ ካቻራ:- የፕላንና ፕሮግራም ኦፍስር
5ኛ. አቶ ፋና አለማዬሁ:- የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩንኬሺን ኦፍሴር
ናቸው።
ይህንንም ተከትሎ የካውንስሉ አባላት አስመራጭ ኮሚቴው ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት፣ ላደረገው በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ግልጽ፣ ነጻና ገለልተኛ ምርጫ፣ የኮሚቴውን አባላት አመስግኖ ውጤቱን ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ አጽድቋል። ለተመረጡትም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፎአል።
የተመረጡ የስራአስፈጻሚ አባላትም ውጤቱን ተቀብለው ወደፊት ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ስላሉ የሁሉም ትብብር ከጎናቸው እንዳይለያቸው ለአባላቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የካውንስሉ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ማርቆስ ዋሬ ለአስመራጭ ኮሚቴዎች የምስጋና ሰርቴፊኬት አበርክቶ ስብሰባውን አጠናቋል።
የአውሮፓ ሲዳማ ኮሚዩኒቲ በጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚያከብረው ፍቼ-ጫምባላላ በዓል እንዲገኙለት የአውሮፓ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ግብዣ አቀረበ።
****************//****************
ማርች 18, 2026
SMN, ዲሲ
"ፍቼ ጨንበላላ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች የተመዘገበ የሲዳማ ብሔር የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት ነው" ያለው ማህበሩ ይህን ደማቅ እና ተወዳጅ በዓል ከዚህ ቀደመ ባልተለመደ መልኩ እና ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት እና በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በአውሮፓ ላሉ የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት እና ኢትዮጵያውያን በጀርመን ፍራንክፈርት አፕርል 25/04/2026 ለማክበር ጥሪ አቅቧል።
ዝግጅቱን ከደቡብ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን ጠቅሶ "በአውሮፓ በተለያዩ አቅጣጫዎች ያላችሁ የሲዳማ ክልል ተወላጆች፤ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ደማቅ እና ተናፋቂ በዓል ላይ እንዲትገኙ በአክብሮ ተጋብዛችኋል" ብሏል።
የዝግጁቱ አድራሻ Mannheimer Str. 15, 60329 Frankfurt am Main መሆኑንም ጠቁሟል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
DMV
Silver Spring, MD
20902