RN05

RN05

Share

ከኢትዮጵያ እና ዲያስፖራ የሚተላለፍ ሚድያ!
አዲሱን ዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://www.youtube.com/c/RN05channel

https://t.me/RNZeroFive

https://rnzerofive.com/

06/04/2026

ይድረስ ለ Moges Zewdu Teshome እዉነቱን ከተነጋገርን ዘመኑ እንዳልከዉ የዳግማዊ ግራኝ አህመድ ቢሆን ኖሮ #አርሲም ሆነ #አክሱም ፣ ሆነ #መስጂድ ፣ #ክርስትያኑም ሆነ #ሙስሊሙ ምዕመን ደህንነታቸው በተጠበቀ ነበር፡፡ ይህንን የምንለው በስሜት ሳይሆን በመረጃ ነው፡፡ ባይሆን ዘመኑ የ #አጼዎቹ አይነት ሆኖ እንደሁ መርምር!
አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኤሊቶች ምንም ሞደሬት ቢመስሉም የከፋ እለት ከተለመደው የልምድ አስተሳሰብ መላቀቅና ሚዛን መጠበቅ እጅግ ያዳግታቸዋል፡፡ ለዚህም ልዩ ኮርስ መዉሰድ ሳይጠበቅባቸው አይቀርም!

እናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ?
የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!
=============
ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ
https://t.me/RNZeroFive
ፍትህ ለ ፣ ፍትህ ለ ፍትህ

06/03/2026

የመንግስት ዋና ኃላፊነት የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ከሆነ ቢያንስ ይህንን በተደጋጋሚ ማድረግ አልቻሉምና ስልጣናቸዉን ሊለቁ አልያም ሊጠየቁ ይገባል!

05/26/2026

⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐
ወድ ተከታታዮቻችን - ኢድ ሙባረክ - እንኳን አደረሳችሁ
⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐🌙⭐

እንኳን ለዒድ አል-አድሐ በዓል
አደረሳችሁ!
ይህ በዓል የኡማው አንድነት
የሚጠናከርበት፣ በአጠቃላይም ህዝባችን
በፍቅርና በሰላም የሚኖርበት
እንዲሆን ምኞታችን ነው።

🔺 መልካም የዒድ በዓል ይሁንላችሁ!🔺

Photos from RN05's post 05/23/2026

~የአቡ ፍርድስ ማስታወሻ እና ራድዮ ነጋሺ ትዝታዎች !❤️🙏
~ የእህቶቻችን እና ወንድሞች የዋትሳብ ትግል ድምፅ ሲታወስ!❤️🙏
~~~~~~~ #አቡፍርደዉስ እንደፃፈው

​ራድዮ ነጋሺ፦ ከማይክሮፎን ባሻገር የተገነባው የ20 ዓመታት ሕያው ማኅበረሰብ እና ታሪካዊ ገድል
​በሳውዲ ዓረቢያ የስደት ቆይታዬ ወቅት በጋዜጠኝነት ያሳለፍኳቸው ዓመታት እና ከራድዮ ነጋሺ (Radio Negashi) ጋር የነበረኝ ትስስር በሕይወቴ ውስጥ እጅግ ጥልቅና የማይረሳ ትዝታን ጥሎ ያለፈ ትልቅ የታሪኬ ምዕራፍ ነው።
​ራድዮ ነጋሺ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ድምፅ ሆኖ ሲነሳ "ከድምጻችን ይሰማ" ታሪካዊ ንቅናቄ አስር ዓመታት ቀድሞ ነበር። ከስዊድን (ስቶክሆልም) እየተቀነባበረ በየሳምንቱ ማክሰኞ ማክሰኞ ወደ አድማጮቹ የሚደርሰው ይህ ጣቢያ፣ ለሁለት አስርተ ዓመታት (ለ20 ዓመታት) ሙሉ ለሕዝቡ ተደራሽ በመሆን ታላቅ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት አበርክቷል።
​እኔ ይህንን ተቋም በአድማጭነት አውቀውና እወደው የነበረ ቢሆንም፣ በባልደረባነት የተቀላቀልኩት ግን ጣቢያው ከተመሠረተ ከ10 ዓመታት በኋላ—ያንን ታላቅና ታሪካዊ የ"ድምጻችን ይሰማ" የመብት ትግል ተከትሎ ነበር። ራድዮ ነጋሺ በወቅቱ የሕዝቡን ብሶትና የትግሉን እንቅስቃሴ በአግባቡ በማስተጋባት ረገድ ግንባር ቀደም የነበረ እውነተኛ የሕዝብ ልሳን ነበር። እኔ ጣቢያውን ከተቀላቀልኩ በኋላ፣ ተቋሙ ከወትሮው የሚዲያ አሠራር ወጣ ባለ መልኩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞችን ልብ ያገናኘባቸውና አዳዲስ አብዮቶችን የፈጠረባቸው ድንቅ ማኅበረሰባዊ ተግባራት ተጀመሩ
​1. የዕለት ተዕለት የመጽሐፍ ትረካዎች በዋትስአፕ (WhatsApp)
​ሚዲያው ከሳምንታዊ ከአየር ሰዓት በተጨማሪ በዋትሳብ ወደ እያንዳንዱ ሰው ስልክ ዘልቆ መግባት የቻለበት አንዱ ትልቅ ስኬት በዋትስአፕ የተጀመረው መድረክ ነበር። በየዕለቱ በርካታ እህቶችና ወንድሞች ድምፃቸውንና ጊዜያቸውን መሥዋዕት በማድረግ፣ ጠቃሚ ኢስላማዊና ማኅበራዊ መጻሕፍትን በድምፅ እየተረኩ ለሺዎች ያደርሱ ነበር።
ይህ ጥረት ስደት ላይ ሆኖ መጻሕፍትን ለማግኘትና ለማንበብ ጊዜና ዕድሉ ለሌላቸው ወገኖች ትልቅ የእውቀት አምባ መሆን ችሎ ነበር።
​2. የዙም (Zoom) ስቱዲዮ የጋዜጠኝነት ሥልጠናዎች
​ተቋሙ ትግሉን በእውቀትና በጋዜጠኝነት ስነ ምግባር የታነፀ ትግል እንዲሆን ለማድረግ ስልጠና መስጠት ግድ ነበር ።
አዳዲስ አቅሞችን የሚፈጥር ማዕከልም ነበር በዘርፉ በሳልና ስመ-ጥር በሆኑ የሚዲያ ጋዜጠኝነት ባለሙያዎች አማካኝነት፣ በዙም ስቱዲዮ (Zoom Studio) አማካኝነት ጥራት ያላቸው የጋዜጠኝነት ሥልጠናዎች በየጊዜው ይሰጡ ነበር። ይህ ሥልጠና ከማንበብና ማዳመጥ ወደ ተግባር የተሻገሩ፣ እንደ እኔ ያሉ በርካታ አድማጮችን ወደ ንቁ የሚዲያ ባልደረባነትና የሕዝብ ድምፅነት ያሻገረ የዕውቀት ብርሃን ነበር።
​3.አቡ ሾዎ በሚል ዓለም አቀፍ የግጥም ውድድሮች እና የኪነ-ጥበብ መነቃቃት
​ራድዮ ነጋሺ የኪነ-ጥበብና የስነ-ጽሑፍ ማዕከልም ነበር። በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሙስሊም ገጣሚዎች መካከል በየጊዜው ታላላቅ የግጥም ውድድሮችን ያዘጋጅ ነበር። ይህ መድረክ በርካታ ድንቅና ስውር ተሰጥኦ ያላቸውን ገጣሚዎች ለዓለም ያስተዋወቀ ከመሆኑም በላይ፣ ለደረጃው የሚመጥኑ ማበረታቻዎችንና ሽልማቶችን በማበርከት በዓይነቱ ብቸኛና አርአያ የሚሆን የሚዲያ ተግባር ነበረው።
​4. የልበ ብርሃን ድምፅ፦ ማየት ለተሳናቸው ወገኖች የተደረገ ተደራሽነት
​ከሁሉ በላይ የራድዮ ነጋሺን የሰብአዊነት ልክ የሚያሳየው ማየት ለተሳናቸው ሙስሊም እህቶችና ወንድሞች ያደረገው ልዩ ድጋፍ ነው። የዕውቀት ብርሃን ለሁሉም እኩል መድረስ አለበት በሚል እምነት፣ የተለያዩ ኢስላማዊ መጽሔቶችንና ጽሑፎችን በድምፅ በመተረክና በማዘጋጀት እውቀቱ በቀላሉ እንዲደርሳቸው ይደረግ ነበር። ይህ ተግባር በጨለማ ውስጥ ላሉ ወገኖች የእውቀትና የእምነት ብርሃን የፈነጠቀ፣ ታላቅ የበጎ አድራጎት ገድል ነበር።
ከስቶክሆልም ማክሰኞ ማክሰኞ ይተላለፍ ከነበረው የ20 ዓመታት ታሪክ ጀምሮ፣ በ"ድምጻችን ይሰማ" ወቅት የነበረው ግንባር ቀደም ተጋድሎ፣ ከዚያም በዋትስአፕ፣ በዙምና በሰብአዊ ተግባራት የዘለቀው የራድዮ ነጋሺ ጉዞ ቀላል የሚባል ታሪክ አይደለም። እኔም መጀመሪያ በአድማጭነት፣ በኋላም በትግሉ ማግስት በታሪካዊ አጋጣሚ የሥራው ባልደረባ በመሆን ያሳለፍኳቸው የሳውዲ የኑሮ ዓመታት ዛሬም ድረስ በኩራትና በትዝታ የምመለከተው ታላቅ የሕይወቴ አሻራ ነው።

Want your business to be the top-listed Media Company in St. Louis?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


St. Louis, MO