AbichoEthio
Ethiopian Brodcasting Media��
06/07/2023
ለክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት
ፊንፊኔ
---------
በሸኖ ከተማ በዎላይታ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ የሚገኘዉን አፈሳና ማፈናቀል እንዲያስቆሙልን ስለመጠየቅ
----------
ክቡር ሆይ--በሸኖ ከተማ ዉስጥ በጉልበት ስራ ፣ በችርቻሮ እና ሌሎች underpaid businesses በመሰማራት ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ሕይወት የሚመሩ የዎላይታ ተወላጆችን በማንነታቸዉ መነሻ የከተማዉ ጸጥታ አካላት በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸዉ ቀን ከስራ ቦታቸዉ እያፈሰ በእስር ቤት አጉሯል ።
-------
በሌላ በኩል ትንንሽ ሕጻናትን(ለማሰር ዕድሜያቸዉ ያልደረሱትን) አፍሶ በመሰብሰብ በከተማዉ የትራፊክ ፖሊሶች አማካኝነት ወደ ፊንፊኔ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ጭነዉ በመዉሰድ በፊንፊኔ -አዲስአበባ ከተማ ጎዳናዎች እንዲጥሏቸዉ ተደርገዋል።
----------
እስር ቤት ታጉረዉ ከቆዩት መካከል አብዛኛዎቹ ዛሬ ከሰዓት በፊት "ከተማዉን ከስምንት ሰዓት በፊት ለቀው ለመሄድ፣ ዳግም በከተማዉ ላለመገኘት እያንዳንዳቸዉ ፈርመዉ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ምናልባት ዳግም በከተማዉ የሚገኝ ግለሰብ እስራት ሳይሆን እስከ መግደል ድረስ እርምጃ እንደሚወሰድበት በማስጠንቀቅ፣ ከእስር ቤት ከመለቀቃቸዉ በፊት እያንዳንዳቸዉ አስቸኳይ ፎቶግራፍ ተነስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
--------
ክቡር ፕሬዚዳንት ሆይ;- ከእስር ቤት ፈርመዉ ከወጡት መካከል አንዳንዶች ለከተማዉ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቤቱታ አሰምተዉ ነበር። ሃላፊዉም" ሰርታችሁና ለፍታችሁ መኖር የሚከለክላችሁ የለም። ለማንኛውም የከተማዉን ጸጥታ ሃላፊ አናግሩት።" ባለዉ መሠረት ለጸጥታ ሃላፊዉ ቢሮዉ ድረስ በመሄድ እሮሮአቸውን ነግረዉታል።
ይሁንና የጸጥታ ሃላፊዉ " ዛሬ ከእስር ቤት ፈርማችሁ የወጣችሁ የወላይታ ብሔር ተወላጆች ከከተማዉ ዛሬ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ መዉጣት አለባችሁ።
ከስምንት ሰዓት በኋላ በከተማዉ ከተገኛችሁ በራሳችሁ ላይ ፈርዳችኋል።" ቤተሰብ +ልጆች ያለን እና ቋሚ ንብረት ያፈራን ሰዎች አለን። ለእኛ ምን ይሻለናል ብለዉ ሲጠይቁት፦ ኃላፊዉ "አያገባንም። ከከተማዉ ለቃችሁ እንድትወጡ በከተማ አመራር ደረጃ ተወስኗል።ያልተያዙ የዎላይታ ተወላጆችን ዛሬና ነገ በተለይም ከገበያ ለቃቅመን በመያዝ አስረን ፈቃደኛ ከሆኑ ዳግም በከተማዉ ላለመታየት አስፈርመን እንለቃቸዋለን።" የሚል ኃላፊነት የጎደለዉን ምላሽ ሰጥቷል።
--------
በመሆኑም በዚች ከተማ በወላይታ ተወላጆች ላይ በማንነታቸዉ መነሻ እየተፈጸመ ያለዉን ሕገመንግስታዊና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆምና አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በተለይም ከሸኖ ከተማ forcefully deport ተደርገዉ ፊንፊኔ-አዲስአበባ ከተማ ወርዉረዉ ለአደጋ ለተጋለጡት የዎላይታ ተወላጅ ሕጻናት ተገቢ የመፍትሔ እርምጃ ይፈለግላቸዉ ዘንድ ትዕዛዝዎ ለሚመለከታቸዉ አካላት ያስተላልፉ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለሁ።
Justice to ethnic Wolaita migrants!
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
አሰፋ ወዳጆ ኦያቶ ነኝ።
share share to all concerned.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Rustenburg